በወንዳዊ መለያዎች የሚገለጽ ስብዕናን እንደተላበሰኝ ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ሴት ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር

‘ሴታሴት’፥ እናት እና ሚስት ናት። ስለዚህም ለኢትዮጵያውያን እይታ አለምንም ጥርጥር በምዕላት የተቃራኒ ጾታ አፍቃሪ ናት። እኔ ደግሞ ተምሳሌታዊ ተደርጌ ልሳል የምችል የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ሴት፥ ጾታዊ መገለጫዬ በተለምዶ ወንዳዊ ወደሚባለው የሚያደላ በመሆኑ በህይወት እመለሳለሁ ብዬ አልጠበቅሁም ነበር። በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ስለ ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እና 666 (በእነሱ አስተሳሰብ እነዚህ ሁለት ነገሮች አንድ ናቸው) ጠንቅቀው እንደሚያውቁ እርግጠኞች ነበሩና የነበርንበት ሁኔታ አደገኛ ነበር። ወንዳዊ በሚባል መልክ እራሴን ከምገልጸው እኔ ጋር በመሆኗ ለእርሷም ክፉ ጦስ እንዳልሆንባት ሰጋሁ። 

ብዙ ዝርዝር ሳላበዛ፥ አንዳችም ብለን አካላችን ጉዳት ሳይደርስበት ተረፍን – በእርግጥ በስሜታችን ላይ በደረሰው መናጥ ከደረሰብን የመንፈስ ጉዳት ማገገም እረጅም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል አስባለሁ። ይበልጥ ‘ሴታሴት’ ብሆን ኖሮ የተለየ ነገር ይገጥመን ነበር ይሆን? በቆይታችን የተሰማኝ ጭንቀት በጣም የቀንሰ ይሆን እንደነበር በእርግጠኝነት አውቃለሁ። ኢትዮጵያ ውስጥ ጾታ ሁለት ገጽታ ብቻ ያለው ጉዳይ ነውና የእኔ በወንድ እና በሴት መካከል በደማቅ የተሰመሩትን ገደቦች ማደብዘዝ ወይም አለመከተል እዚህ የሚኖረኝን ህይወት ውስብስብ፥ አንዳንዴም አስጊ ያደርገዋል። 

የመጸዳጃ ቤቶችና ፍተሻ የዕለት ተዕለት የኢትዮጵያ ኑሮዬ ፈተና ናቸው። የህዝብ መጸዳጃ ቤቶችን ለመጠቀም የሚያጋጥመኝ ድርድር መንፈስን የሚያደክም በመሆኑ አለመጠቀሙን እመርጣለሁ። “ሴት ነኝ” በትህትና፥ በቁጣ፥ በፍጹም መታከት፥ ተስፋ በመቁረጥ እንዲሁም በሃዘን ስሜት የማወጣው ዓረፍተ ነገር ነው። የሰዎች እነዚህን ቃላቶች በአይምሮዕቸው ሴትን መምሰል አለበት ብለው ከያዙት ምስል ውጭ ለመረዳት አለመቻል አያሌ ጊዜ የአይምሮ ጤናዬን ተፈታትኖታል። ምንም ያህል ለሌሎች ዕይታ እንዳልጎረብጥ እራሴን ማሳነስና ማደብዘዝን ብለማመድም እንኳን በጣም ተፈጥሯዊና ቀላል የሚመስለው መጸዳጃ ቤትን መጠቀም ቀኔን በሙሉ ሊያጨልም አቅም ያለው ከባድ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። እነዚህ ቃላቶች ብቻቸውን ባያስከፉኝም ልቆጥረው ከምችለው ጊዜ በላይ “መጸዳጃ ቤት ተሳስተሻል” ተብዬ አውቃለሁ። በግልጽና በቀጥታ ጾታዬን ስናገር ሰዎች ቢያደምጡኝ ይህን መሰልን ማስተካከያን ለመረዳትና በቅንነት ለመቀበል ዝግጁ ነኝ። ሆኖም ግን ወደ መጸዳጃ ቤት ስገባ ተከትለውኝ መግባት እና ስወጣም ሌሎች ሰዎች እንደ ጉድ እንዲመለከቱኝ መሰብሰብ ሲበዛ ስለሚጎዳና ስለሚደክም አንዳንዴ መጸዳጃ ቤት አለመጠቀምን ያስመርጣል። የእኔ ተሞክሮ “ሴት ነኝ” ስል ሌሎች ሰዎች በሚኖራቸው ምላሽ ስለሚወሰን፥ በሚያሳዝን ሁኔታ ያለተግዳሮት ለመኖር እኔ በግሌ የማደርገው አንዳች ነገር የለም። 

ጾታዬን ለመግለጽ ስለመረጥኩበት ሁናቴ ማብራርያ ወይም መከላከያ ማቅርብ አይገባኝም። አለምንም አለማመቻመች እራሴን በመረጥኩበት መንገድ ለመግለጥ የማደርገው ትግል የአሁኑንም ወደፊት የሚሰራውንም ማንነቴን የሚቀርጽ ነገር ነው።

አንዳንዴ አካላዊ ፍተሻዎች በሽሙጥና ተገቢ ባልሆኑ አስተያየቶች፥ ጭቅጭቅ፥ ማፍጠጥ እና አልፎ አልፎም በፍጹም ባልተጠየኩት‘አራሚ’ ምክሮች ሊጀምሩና ሊጨርሱ ይችላሉ። ሊፈትሸኝ ሲመጣ ስላስተካከልኩት “ልታታልይኝ” ሞክረሻል ብሎ አንድ ሰው ከሶኛል። “ሴት ነኝ” እያልኩ ደጋግሜ ብናገርም እንኳን ወንድ እና ሴት ፖሊሶች እርስ በእርሳቸው “አንተ ፈትሽ፥ እንች ፈትሽ” እያሉ ሲገዳደሩ ትዕግስቴ በማለቁ ከአንድ ሰዓት በላይ በአንድ መንግስት ቢሮ ውጭ ለመቆም ተገድጃለሁ። የበላይ አዛዣቸው እስኪመጣ ውጭ እንደጠብቅ ከተደረገ በኋላ ለተፈጠረው ‘መጉላላት’ ይቅርታ እንድጠይቅ ተጠየቅሁ። ለበላይ አዛዣቸው ጓዶቹ ማዳመጥ መማር እንደሚገባቸው በመናገር ይቅርታ አልጠይቅም አሻፈረኝ አልኩ። ሴት መሆኔን መለየት አለመቻላቸው የእኔ ጥፋት እንደሆነ ፖሊሶቹ ሲከራከሩኝ ለአንድ ሰዓት ያህል ጊዜዬን ካባከኑ በኋላ በእምቢታዬ በመጽናቴ በመጨረሻ ወደ ህንጻው እንድገባ ተፈቀደልኝ። በፍተሻ ጣብያዎች ላይ ጠበቃ ሆነው የሚሰሩ አያሌ ቀና አሳቢ ሰዎች ጸጉሬን በጣም በአጭሩ በመቆረጥ፥ “እንደ ወንድ በመልበስ” ወይም “እንደ ወንድ በመራመድ” “ውበቴን” እንዳላበላሽ መክረውኛል። ጾታዬን ለመግለጽ ስለመረጥኩበት ሁናቴ ማብራርያ ወይም መከላከያ ማቅርብ አይገባኝም። አለምንም አለማመቻመች እራሴን በመረጥኩበት መንገድ ለመግለጥ የማደርገው ትግል የአሁኑንም ወደፊት የሚሰራውንም ማንነቴን የሚቀርጽ ነገር ነው። አብዛኛው ሰው ወንድ መምሰል እንደምፈልግ የሚደመድሙ ሲሆን አንዳንድ ወንዶች ደግሞ ሌሎች ሴቶችን በመጨቆን ላይ የተመሰረተ (ሃሳዊ) ህብረት ልንጋራ እንደምንችል ይጠብቃሉ። እነዚህን ዕሳቤዎች ለማረም ስሞክር እና ጾታዊ መድሎ እና ሴቶችን ማኮሰስ ለወንዶችም ቢሆን ተገቢ ዕሴቶች እንዳልሆኑ ስጠቁም የማገኘው ምላሽ በአንድም በሌላም መልኩ “አንች እራስሽ ሴት መሆን ስለማትፈልጊ ሴቶችን መወከል (መደገፍ) አትችይም” የሚል እንደምታ ያለው ነው። 

እነዚህ ከተለያዩ ሰዎች የሚሰጡ ብዙ ያልታሰበባቸው አስተያየቶች ያበሳጫሉ። በቅርቡ፥ ከሁለት ሳምንት በፊት “ወንድም” ብሎ የጠራኝን አንድ ሰው ሳስተካክለው ሊያደምጠኝ ፈጽሞ አልፈለገም። አበክሬ ስጠይቀው “አንቺን የሚመስል ሰው ሴት ማለት ይከብደኛል” አለኝ። “የእኔ ጾታ ከአንተ ምቾት ጋር እምብዛም ጉድኝት የለውም” ብዬ የሰጠሁት ምላሽ ምንም እንኳን ተገቢ ቢሆንም የእሱ አስተያየት ግን ከእህቴ ጋር የነበረኝ የቡና ጊዜ አበላሸብኝ። እኔ እና እህቴም አብዛኛውን ሰዓታችንን አብዛኛው ኢትዮጵያውያን ጾታን ከሁለትዮሽ ገጽታዎች ውጭ ለመመልከት መሞከር አለመቻላቸውንና፥ ይህም በእዚህ ሁለትዮሽ ክፍፍል ውስጥ ስፍራ ለሌላቸው የሚያስከፍለው ከባድ ዋጋ በመወያየት አሳለፍን። አስቀድመን የተገናኘነው ስለ ጾታ ወይም ስለ እርሱ ዘለፋ ለመወያየት ባይሆንም በእዚህ አጋጣሚም የእኔና የእህቴ ውሎ ከእኔ ቁጥጥር ውጭ በሆነ ውጫዊ ሁኔታ እንዴት እንደሚወሰን ማሳያ አጋጣሚ ሆኖ አለፈ።

ምናልባትም “እንደ ወንድ ከምትሆን” ሴት የበለጠ የከፋ ነውር ሆኖ የሚታየው “እንደ ሴት የሚሆን” ወንድ ነው። ሁለቱም ለኢትዮጵያዊ ወንድነት አደጋ ናቸው። በመሆኑም የጾታዊ መገለጫችንና አቀራረባችን እጅግ ውስንና ጎጅ ከሆነው ሁለትዮሽ ገለጻ ውጭ የሆንን ሰዎች የእዚህ ማህብረሰባዊ ጦርነት ፊት ዘማቾች ነን። እንደ አለመታደልም የፍልሚያው ሜዳ የእኛው አካላት ነው።

ምንም እንኳን መጸዳጃ ቤቶች፥ አካላዊ ፍተሻዎች እና ተራ አስተያየቶች እጅግ አታካች ቢሆኑም ወንዳዊ በሚባል መልክ እራሷን የምትገልጥ ሴት ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያጋጥሟት ከሚችሉ ሌሎች ምላሾች አንጻር እዚህ ግቡ አይባሉም። 

በአዲስ አበባ ውስጥ በጣም ዓይን ውስጥ እንደሆንኩ የተሰማኝ ወንዳወንድ ከሆነች ጓደኛዬ ጋር አንዳንድ ቦታዎች በምንሄድበት ወቅት ነበር። ምንም እንኳን የእርሷም የጾታ መገለጫ በተለምዶ ወንዳ ወንድ ወደሚባለው የሚያደላ ቢሆንም እንደኔ አታሳስትም። አብረን ስንሆንም የምንስበው ትኩረት፥ ግራ መጋባት (አንዳንዴ መጸየፍም) ይበልጥ ግልጽ ነበር። አካላዊ ንኪኪ የማይከብዳት ነጻ ሰው ከመሆኗም ባሻገር በአደባባይ ይህንን ባህርያውን ሁሌም ስለማትገድበው የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች መሆናችን በቀላሉ ሊጋለጥ እንደሚችል ስጋት ይፈጥር ነበር። አንድ ወዳጄ አስጨናቂ ሆኖ ከማግኘት ብዛት ይህን ጉዳይ ጠቁመውልኛል። ቢሆንም ግን አብሬያት የሆንኩትን ሴት አካል መግፋት እጅግ ከባድ ሆኖ አገኘሁት። ሴታ ሴት ከሆነች ሴት ጋር መታየት ምን ያህል ይበልጥ ቀላል እንደነበር አሰብኩ። በተለይም ሴታሴት የሆነች ሴት ጋር ስሆን አደባባይ ላይ የተሰጣሁ ስለማይመስለኝ ያንን ነጻነት መናፈቄ አልቀረም። 

እስከ ቅርብ ዓመታት ድረስ፥ ጾታዊ መገለጫዎችን መቆልመሜ እና መስመሮችን ማደብዘዜ ሌሎችን የሚያስከፋው ሁለትዮሽ የሆነውን ጾታ በመዳፈሬ ብቻ ነበር። ከቅርብ ጊዜ በኋላ ግን ሰዎች የጾታ መገለጫዬን ከፍቅር ምርጫዬ ጋር ያያይዙታል። በፊት “ወንዳወንድ” ተብዬ እታለፍ የነበርኩት አሁን አሁን ግን አያሌ ውይይቶች ወደ ተመሳሳይ ጾታ አፍቅሮት ጉዳይ እንደሚያመሩ ታዝብያለሁ። ተያይዞም የተመሳሳይ ጾታ አፍቅሮት አጥፊ ባህሪ የሚያስረዱ ትንተናዎችን በግድ እንዳስተናገድ ሆኛለሁ። ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ላይ ክፉ ጥላቻ ያላቸው ሰዎች እነርሱም ይህን ስሜት እንደሚጋሩ በመገመት እህትና ወንድሞቼም ስለ ፍቅር ምርጫዬ ሲጠይቋቸው አሳልፈው ሳይሰጡኝ እኔን መከላከል የሚችሉባቸውን መንገዶች መለማመድ ነበረባቸው። በማይጠበቅ ሁኔታ እህቶቼ ስለእኔ በቀጥታ ባይነግሯቸውም አንዳንድ ሰዎች እነርሱም ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ የቤተሰብ አባላት እንዳሏቸው ነግረዋቸዋል። 

ምንም እንኳን የእኔ የጾታ መገለጫ ሌሎች ሰዎች በአንጻሩ ግልጽ ሊባል የሚችል ውይይት እንዲያደርጉ ማስቻሉ የሚያስደስተኝ ነገር ቢሆንም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የተመሳሳይ ጾታ አፍቅሮት ፍራቻ ወደ ሚጠበቀው ቋፍ የሚገፋ አንድ ሁኔታ ሲፈጠር ችግር ይሆናል። ለምሳሌ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከጥቂት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያን በጎበኙ ወቅት ስለ ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ሰዎች መብት በአደባባይ ግፊት ያደርጋሉ ብለው ሰዎች በመጠበቃቸው እንደዚህ ያለው የእብደት ቋፍ ታይቷል። በእንደነዚህ ዓይነት ወቅቶች ከተለመደው በላይ አስፈሪ ትኩረት እንደምስብ ይሰማኛል። ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን ማውገዝ ግድ በሚመስልባቸው ጊዜያት ሁሉም ስለ ተመሳሳይ ጾታ አፍቅሮት ያለውን ፍራቻ ከፍ አድርጉ መግለጥ እንደሚገባው ሲሰማው በማንኛውም ሰዓት ሊፈነዳ የሚችል ጥቃት ኢላማ ይዤ እንደምዞር ይሰማኛል። የምሰበው ትኩረት ያስፈራኛል። ትኩረቱና እና አስከትሎት የሚመጣው ቁጣ ወዴት ሊያመራ እንደሚችል ያስጨንቀኛል። “አስገድዶ በመድፈር ለማረም” መሞከርን፥ የደቦ ፍርድም አልያም ሌላ ዓይነት ጥቃት ሊያስከትል ይሆን? ውጥረቱ ከፍተኛ በሆነባቸው እነዚህ ወቅቶች ምንም ነገር አይሆንም ማለት አይቻልም። 

የሚገርመው ግልጽ ወንዳ ወንድ ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ከመሆን የሚመጣው የደህነነት ፍራቻ ከጥቂት ዓመታት በፊት የሚታስብ አልነበረም። ለእኔ ግርምቢጥ የሚሆነው ይኽ ነው፤ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን ተሞክሮ እንዲሻሻል አክቲቪዝም – ይህንን ጉዳይ አንስቶ መታገል – ግድ የሚል ቢሆንም እንዲህ ያለው እንቅስቃሴ በጎ እውቀት ሲኖረው አንዳንዶቻችንን የጥቃት ኢላማ ያደርገናል። ምናልባትም “እንደ ወንድ ከምትሆን” ሴት የበለጠ የከፋ ነውር ሆኖ የሚታየው “እንደ ሴት የሚሆን” ወንድ ነው። ሁለቱም ለኢትዮጵያዊ ወንድነት አደጋ ናቸው። በመሆኑም የጾታዊ መገለጫችንና አቀራረባችን እጅግ ውስንና ጎጅ ከሆነው ሁለትዮሽ ገለጻ ውጭ የሆንን ሰዎች የእዚህ ማህብረሰባዊ ጦርነት ፊት ዘማቾች ነን። እንደ አለመታደልም የፍልሚያው ሜዳ የእኛው አካላት ነው። 

ሆኖም ግን ዙሪያችንን ከከበበው ክፋትን እና አደጋ ጋር እየታገልንም ቢሆን በሐቅ እራሳችንን መሆን የምንችልባቸውን መንገዶች ማግኘት አለብን።

Leave a Reply