አስሮቻችን የተገናኘንበት የቪድዮ ትውውቅ ለአራት ሰዓታት ፈጅቶ የሚገርም እና ድንቅ ጊዜ አሳለፍን
ጊዜያችሁን እንዴት እያሳለፋችሁ ነው? መቼ ወደነበርንበት እንደምንመለስ አለማወቅ ይረብሻል::
አብዛኛውን የምናያቸው ንቅናቄዎች/ፕሮጀክቶች HIV/AIDS እና gay የማህበረሰባችን ክፍሎች ላይ ያተኮረ መሆኑ አዲስ አይደለም:: በተካፈልኩባቸው የኢትዮጲያ LGBTQIA ዝግጅቶች ላይ በሚደንቅ ሁኔታ የሴቶች ቁጥር አንሶ አገኘዋለሁ:: የመወያያ ርዕሶቹም በወንዶች ዙሪያ ይሆንና በስተመጨረሻ ላይ የእኛ የlesbian ጉዳዮች ይነካሉ:: ለምን እንደሆነ ብዙ ጥናት ቢፈልግም…የወንድ ገደኝነት (privilege) በstraight ወንዶች ላይ ብቻ ሳይሆን gay ወንዶችም ላይ የሚንፀባረቅ ነው:: አንድ ሰው ወንድ ስለሆነ ብቻ የሚያገኛቸው ገዶች…
በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ 9 queer/lesbian ሴቶች ጋር አንድ ውይይት ላይ ስገኝ! ሌላ ጊዜ እንዳልኳችሁ ወይ የወንዶች ቁጥር ይበዛል፣ ወይ የውይይቱ ርዕስ የወንዶች ጉዳይ ላይ ያተኩራል::

በዚህ ዙሪያ lesbian ከሆኑ ጓደኞቼ ጋር በጣም እንወያያለን:: Covid19 ደግሞ ክፉ ነገሮቹ እንዳሉ ሆነው ከጓደኞቻችን ጋር በስልክ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ይበልጥ እንድንገናኝ አድርጎናል:: በማህበራዊ ሚዲያው የማውቃቸውን lesbian/queer ሴቶች ለምን በቪድዮ ቁጭ ብለን የምናወራበትን ፕሮግራም አላስብም ብዬ ለፍቅር አጋሬ አወያየኋት፤ ሃሳቡን ወደደችው እና እንዴት ማድረግ እንዳለብን ተወያየን:: በአካል ተገናኝተን ባናውቅም ኢንተርኔት ላይ በደንብ የማውቃትን አንደኛዋን የኢንተርኔት ጓደኛዬ ሃሳቡን አካፈልኳት፤ ስልክ ተለዋውጠን ስለሃሳቡ እንድናወራበት ተነጋገርን:: የምንቀርባቸው፣ የምናምናቸውም የኢንተርኔት ጓደኞቻችን እነማን እንደሆኑ ዘረዘርን፣ እንደመጀመሪያ ትንሽ እንሁን ብለን እኔና እሷን ጨምሮ አስር queer/lesbian ጋበዝን:: በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ 9 queer/lesbian ሴቶች ጋር አንድ ውይይት ላይ ስገኝ! ሌላ ጊዜ እንዳልኳችሁ ወይ የወንዶች ቁጥር ይበዛል፣ ወይ የውይይቱ ርዕስ የወንዶች ጉዳይ ላይ ያተኩራል::
የትም ብንወለድ፣ የትም ብንኖር እንዴት የሁላችንም አመጣጥ አንድ እንደሚያደርገን ሳይ ተገረምኩ::
ቀኑ ደርሶ ስንገናኝ ሙሉ ስማችንን፣ የምንሰራውን እና የምንጠራበትን ተውላጠ ስም(pronoun) ተነጋገርን:: ግማሾቻችን ኢትዮጲያዊ፣ሌሎቻችን ኤርትራዊያን፣ በእድሜም የተለያየን፣ በሃይማኖታችንም ከተለያየ ሃይማኖት የመጣን ልጆች ተገናኘን:: በፊት በፊት እንደኢትዮጲያዊ ውጪ የሚኖሩት ኢትዮጲያዊያን LGBTQIA እንዴት የታደሉ ናቸው እል ነበር፣ ፎቷቸውን ለቀው፣ የፈለጉትን ሆነው እና ለማንም ግድ ሳይሰጣቸው ይኖራሉ እያልኩ በራሴ ሁኔታ(ነፃነት አለማግኘት) አዝን ነበር::
አስሮቻችን የተገናኘንበት የቪድዮ ትውውቅ ለአራት ሰዓታት ፈጅቶ የሚገርም እና ድንቅ ጊዜ አሳለፍን:: የትም ብንወለድ፣ የትም ብንኖር እንዴት የሁላችንም አመጣጥ አንድ እንደሚያደርገን ሳይ ተገረምኩ:: አንደኛዋ ትውልደ አሜሪካዊ ኢትዮጲያዊ ቤተሰቦቿ ምን ያህል homophobic እንደሆኑ እና መቼ ራሷን ነፃ እንደምታወጣ ግራ መጋባቷ፣ ሌላኛዋም ኤርትራዊ ስለራሷ ከነገረቻቸው ጊዜ ጀምሮ ከቤተሰቦቿ ጋር ያላትን ችግር፣ ሁላችንንም የሚያስተሳስር ተመሳሳይ ታሪክ እንዳለን እንድረዳ አድርጎኛል:: በአካል የማንተዋወቅ queer ኢትዮጲያዊ እና ኤርትራውያን ለአራት ሰዓታት ታሪካችንን ተወያየንበት፣ ሃይማኖታችን ላይ ያሉንን ጥያቄዎች ተነጋገርን (አብዛኞቻችን የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ነን) እንዴት ስለራሳችን እንዳወቅን ወይም በልጅነት የወደድናቸውን የHollywood ታዋቂ ሰዎች እያነሳን እንደሳቅነው ሁሉ ባሳለፍናቸው ራስን የመቀበል ትግልም ተላቀስን:: እርስ በእርስ ልንደጋገፍ እንደሚገባ ተነጋገርን፣ ሩቅ ለሩቅ ብንሆንም በቻልነው ሁሉ አብረን መሆን እንዳለብን፣ ከመቼውም በላይ ጓደኝነታችንን ልናጠናክር ተስማማን::

እነዚህ በአካል የማላውቃቸውን queer ኢትዮጲያውያን እና ኤርትራውያን በማግኘቴ የመንፈስ እርካታን ሰጥቶኛል:: ለካ ሁላችንም ከምንም አይነት ቤተሰብ ብንመጣ የሚያመሳስል ብዙ ማንነት እና ታሪክ አለን:: የአንድ ኤርትራዊ ዳያስፓራ እናት “አንቺ እንደዚህ ከሆንሽ ራሴን ነው ማጠፋው” ማለቷን ስንሰማ…ምንም ያህል ቤተሰቦቻችን የተለያየ ቦታ ቢሆኑ ለነገሮች ያላቸው መረዳት ከጥንት የተቀበሉት አረዳድ መሆኑ ነው:: ነገሮች ለመቀየር ብዙ አመታትን ስለሚፈጁ ምናልባትም በእኛ እድሜ ስለማይቀየሩ፣ እኛ እርስ በእርስ አለሁልሽ በመባባል እውነታችንን መኖር ዋነኛው መፍትሄ ነው::