“ከሴቶች ጋር ወሲብ የሚፈጽሙ ሴቶችም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ለሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች ሊጋለጡ ይችላሉ”

“ይህ ጥያቄ ከሆነ ዓመታት በፊት የነበረኝን አንድ ልምድ አስታወሰኝ”ትላለች ህሊና ከጾታዊ አጋሮች ጋር ስለ ደህንነቱ የተጠበቀ ወሲብ ስትጠየቅ፡፡ “በመጀመሪያ ሳንመረመር ነበር አብረን የተኛነው፣ በሁዋላ ላይ ግን የሽንት መሽኚያ ኢንፌክሽን ህመም ገጠመን አጋጣሚው የሚያስደነግጥ እና የሚያስፈራ ነበር፡፡ በኋላም ላይ ሁለታችንም ለUTI ፣ ለ STI እና የመሳሰሉት ምርመራ መውሰድ እንዳለብን ተወያይተን ወሰንን”፡፡

የህሊና ተሞክሮ በጾታ ግንኙነት ወቅት ከሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች (እንደ STIs እና HIV), ጋር ተያያዥነት
ያላቸውን አደጋዎች የመመርመር እና ማወቅን ልምድ ይናገራል፡፡

በሴቶች መካከል ወደ ወሲብ ሲመጣ በጣም ከተለመዱት ስህተቶች አንዱ በሴቶች መካከል የሚደረግ የፆታ ግንኙነት ምንም አይነት አደጋ የለውም የሚለው ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ፣ ከሴቶች ጋር ወሲብ የሚፈጽሙ ሴቶች ምንም ስጋት ስለሌለው ደህንነቱ የተጠበቀ ወሲብን መለማመድ አያስፈልጋቸውም፡፡ ይህ አደገኛ እና የተሳሳተ ግንዛቤ ነው፡፡

“በሴቶች መካከል ደህንነቱ የተጠበቀ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ልክ በተቃራኒ ፆታ መካከል ደህንነቱ የተጠበቀ  ጤናማ የወሲብ ግንኙነት ጠቃሚ ነው እንደምንለው በእኩል ያስፈልጋል” ትላለች አዲስ አበባ ውስጥ ነዋሪ የሆነችው ሌዝቢያን ፌቨን በበኩሏ፡፡ “ከሴቶች ጋር ወሲብ የሚፈጽሙ ሴቶችም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ለሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች ሊጋለጡ ይችላሉ”፡፡

በአባላዘር በሽታዎች (STI) ወይም በኤች.አይ.ቪ የመያዝ አደጋ የሚወሰነው በሚያደርጉት የወሲብ ዓይነት እና ከማን ጋር እንደሆነ ነው፡፡ ከሴቶች ጋር ወሲብ የሚፈጽሙ ሴቶች የተለያዩ ብዙ መንገዶች አሏቸው፡፡

በቀድሞ ግንኙነቶቼ ውስጥ ስለ ደህንነቱ የተጠበቀ ወሲብ በጭራሽ አልተወያየሁም ብዬ መጥቀስ አስፈላጊ ይመስለኛል …

ፌቨን

” ሰዎች የተለያዩ የወሲብ አጋሮች እና ልምዶች ስላሏቸው ደህንነቱ የተጠበቀ ወሲብ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ አብረዋቸው የሚሆኑዋቸው ሰዎችም ምናልባት ሌሎች ወሲባዊ አጋሮች ነበሯቸው፡፡ ስለዚህ የሰዎች ወሲባዊ ታሪኮችን ስለማናውቅ ሁልጊዜም በጥንቃቄ መኖሩ የተሻለ ነው” ስትል ህሊና አክላለች ፡፡

ኢንፌክሽኖች በበርካታ መንገዶች ሊተላለፉ ይችላሉ ፣ ለምሳሌ ከቆዳ ወደ ቆዳ ንክኪ ፣ የሴት ብልት ፈሳሾች ፣ የወር አበባ ደም እና በጋራ በሚጠቀሙዋቸው የወሲብ መገልገያ እቃዎች (Sex toys) ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ የአደጋ ኣጋላጮች በነፃነት የሚወሩ ጉዳዮች አልሆኑም ምክንያቱም በሴቶች መካከል የሚደረግ የፆታ ግንኙነት በኢትዮጵያ ውስጥ በግልፅ ልንወያይበት የምንችለው ርዕስ አይደለም፡፡

ፌቨን “ደህንነቱ የተጠበቀ ወሲብ ዙሪያ ወይም በአጠቃላይ የወሲብ ትምህርት ዙሪያ ያሉ ብዙ መረጃዎች በብዛት ያተኮሩት በተቃራኒ ፆታ መካከል ባሉት ግኑኝነቶች ነው፤ ይህም ከሴቶች ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሴቶችን የምንመለከትበት ሁኔታ ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደሩ አስባለሁ” ብላለች፡፡ “ብዙ ሰዎች የአባለዘር በሽታዎች በወንዶችና በሴቶች መካከል በግብረ ሥጋ ግንኙነት ብቻ የሚከሰቱ እንደሆኑ አድርገው ያስባሉ”፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ነገሩን በይበልጥ የሚያወሳስበው በአጠቃላይ በጾታ ጉዳዮች ዙሪያ ግልፅ ውይይት አለመኖሩ ነው፡፡በተቃራኒ ፆታ አፍቃሪያን መካከል እንኳን ይህ ውይይት የለም፡፡

ፌቨን “ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ የመረጃ እጥረት አለ እና ከሌሎች ሴቶች ጋር ወሲብ የሚፈጽሙ ወጣት ሴቶች ስለ ደህንነቱ የተጠበቀ ወሲብ የሚያነቡበት እና የሚማሩበት ቦታ እንዲኖራቸው ተስፋ አደርጋለሁ” ብላለች ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የጤና እና የሰብዓዊ አገልግሎት ቢሮ የሴቶች ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት እንደገለጸው (link) ከሴቶች ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሴቶች ከፍተኛ ተጋላጭ ከሚሆኑባቸዉ የአባላዘር በሽታዎች መካከል የተወሰኑት የሚከተሉትን ያካትታሉ ፡፡

  • ባክቴሪያል ቫኒኖሲስ፤
  • ክላምዲያ፤
  • የብልት ቆዳ በሽታ፤
  • የሰው ፓፒሎማቫይረስ (HPV) (ከቫይረስ የሚከሰት ሕመሞ)
  • የብልት በሽታ፤
  • በብልት አካባቢ ቅማል፤ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ሴቶች እራሳቸውንና ደህንነታቸውን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው የማያውቁ መሆኑ አስቸጋሪ ነው ፡፡

“ያን ያህል በቁም ነገር አለመወሰዱ በጣም ያሳስበኛል፡፡ እናም ኢንፌክሽኖችን የመሰጠት ወይም የመቀበል እድሉ
ዝቅተኛ መሆኑን የሚገልፅ መረጃ ደግሞ አያግዝም” ትላለች ህሊና፡፡

ደህንነቱ የተጠበቀ ወሲባዊ ግንኙነት ለማድረግ የመጀመሪያው እርምጃ ውይይት ነው ፡፡

“በቀድሞ ግንኙነቶቼ ውስጥ ስለ ደህንነቱ የተጠበቀ ወሲብ በጭራሽ አልተወያየሁም ብዬ መጥቀስ አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ ግንኙነቱ ያልተረጋጋ በሚሆንበት ጊዜ እነዚህ ዓይነቶች ውይይቶችን ማድረግ ለእኔ በጣም ከባድ ነበር” ስትል ፌቨን ተናግረለች ፡፡

ከወሲብ ጓደኞችዎ ጋር ግልጽ ውይይት ማድረግ አለብዎት እና እነዚህ ውይይቶች የወሲብ ጤንነት ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የወሲብ ዘዴዎችን ፣ ምን ዓይነት ግኑኙነቶችን እንደሚፈልጉ እና የበለጠ ደህንነታቸውን እንዴት እንደሚያሳድጉ ማካተት አለባቸው ፡፡

ያን ያህል በቁም ነገር አለመወሰዱ በጣም ያሳስበኛል፡፡

ህሊና

በተገቢው ሁኔታ ሁሉም ወገኖች ለመጀመሪያ ጊዜ አብረው ከመተኛታቸው በፊት ሁሉም የአካል ጤንነታቸውን እንዲያውቁ የSTIs (በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች) እና ኤች.አይ.ቪ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራል፡፡ ያ ባልተከሰተባቸው አጋጣሚዎች በብሪታንያ ብሔራዊ የጤና አገልግሎት መሠረት እራስዎን እና አጋሮችዎን የአባላዘር በሽታዎች እና ኤች አይ ቪ እንዳይያዙ ለመከላከል የሚከተሉት የጥበቃ ዓይነቶች ናቸው

  • የወሲብ መጫወቻዎችን የሚጠቀሙ ከሆነ ለእያንዳንዱ አጋር አዲስ ኮንዶም ይጠቀሙ ወይም የተለያዩ የሰውነት
    ክፍተቶች ውስጥ የሚጠቀሙ ከሆነ አዲስ ኮንዶም ይጠቀሙ፡፡ የወሲብ መጫወቻዎች በሳሙና እና በውሃ በሚገባ መታጠብ አለባቸው ፡፡
  • ማናችሁም በአፍዎ ወይም በከንፈሮቻዎ ላይ ቁስሎች ካሉ ወይም የአፍ ወሲብን ያስወግዱ፡፡ አልያም ከፈሳሽ ልውውጥ የሚከላከል ከስኩዌር ላቲክስ ይጠቀሙ፡፡ በአፍ ወሲብ ወቅት ፊንጢጣውን ወይም የሴት ብልትን ለመሸፈን ሊጠቀሙበት የሚችሉት የ 15 ሴንቲ ሜትር በ15 ሴንቲ ሜትር የሆነ የሎክስ ወይም ፖሊዩረቴን (በጣም ቀጭን ለስላሳ ፕላስቲክ) ካሬ ነው፡፡ ከአንድ ሰው ወደ ሌላው የሚተላለፉ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል እንደ እንቅፋት ሆኖ ይሠራል፡፡
  • አንዳንድ ኢንፌክሽኖች በእጆች ፣ በጣቶች እና በጋራ ብልት በማሸት ሊተላለፉ ይችላሉ ፡፡ ከወሲብ በፊት እና በኋላ እጅዎን በሚገባ ይታጠቡ፡፡ የረግረግ ጓንቶች ያድርጉ እና ለሴት ብልት እና ለፊንጢጣ ግኑኝነት ወቅት በውኃ ላይ የተመሠረተ ቅባት በብዛት ይጠቀሙ፡፡

ደህንነትዎን ይጠብቁ ፤ ይዝናኑ ፡፡

Leave a Reply