ዋሂራ ላቤሌ – የጥንካሬነት መገለጫ

ዋሂራ ላቤሌ በአሜሪካ የምትኖር የምስራቅ አፍሪካ አብዮተኛ ናት:: በማህበረሰብ ትራንስ ጠልነት ምክንያት ከሃገሯ የተሰደደች ሲሆን በእንቅስቃሴዎቿ ላይ እና ትራንስ ማንነት ዙሪያ ላቀረብንላት ጥያቄዎች ጊዜ ወስዳ መልሳልናለች:: 

እስቲ ራስሽን አስተዋውቂ

የሶማሌ ተወላጅ ትራንስ ፌም ኩዊር ነኝ:: የተወለድኩት በሶማሊያ ነው:: አሁን ያለሁት ካሊፎርንያ ሲሆን በጥቁር ኩርዊ ስደተኞች ዙሪያ ፕሮጀክቶች ላይ እሰራለሁ እንዲሁም የብላክ ትራንስ ማይግራንትስ ዩናይትድ (BTMU) መስራች ነኝ::  

ከፃታ ማንነትሽ ጋር መቼ ተስማማችሁ?

በጣም በልጅነቴ:: ነገር ግን አስጊ ያልሆነ ቦታ ላይ እስክሆን ድረስ ጠበኩኝ ይህም ከሃገር እንድሰደድ አስገደደኝ::

ራስን የማወቅ ጉዞሽ ምን ይመስል ነበር?

አክራሪ የእስልምና ተከታይ በሆነችው ትንሽዬ የሶማሊ መንደው ውስጥ ባድግም ገና በልጅነቴ የተለየሁ እንደሆንኩ አውቄ ነበር:: ከብዙ ውስብስብ ስሜቶችና ራስን የማወቅ ፍላጎት በኋላ ወደ ኬንያ ስደተኞች ካምፕ ለመግባት ወሰንኩ:: እዛም ብቻዬን እንዳልሆንኩ አወኩ:: እንደኔ በአለም ላይ ሌሎች ትራንስ ሰዎች እንዳሉ በማወቄ የኔ ልዩነት ተጨባጭ እንደሆነ እና የሌሎችም እውነታ እንደሆነ፣ ልረዳው እና ላከብረው እንደምችል ገባኝ:: ያኔ ነው ራሴን የተቀበልኩት ምንም እንኳን የተለየ ማንነት ስጋት ቢኖረውም::

ነገሮች ይሻሻላሉ! ልክ ናችሁ! ተስፋ አትቁረጡ! ታስፈልጋላችሁ! አንድ ቀን ወደኋላ ታዩ እና በራሳችሁ ትኮራላችሁ::

ዋሂራ ላቤሌ

ከምስራቅ አፍሪካ መሆንሽ ማንነትሽ ላይ ያመጣው ተፅዕኖ ምን ይመስላል? 

ጥንካሬ! ዛሬ ላይ ጠንካራ ሰው እንድሆን አድርጎኛል:: ትራንስ ጠልነትን ምስራቅ አፍሪካ ላይ ከተቋቋምኩኝ ማንኛውንም ነገር የትም መቋቋም እችላለሁ እንድል አድርጎኛል:: 

በትራንስ ሰዎች ዙሪያ ምስራቅ አፍሪካ ላይ ትልቁ ተግዳሮት እና የመረዳት ችግር ምንድነው ትያለሽ?

ትራንስ ጠልነት! ምስራቅ አፍሪካ ላይ መኖራችን ወይም ማንነታችን ሙሉ በሙሉ የተወነጀለ ነው:: መረጃ ባይኖርም ብዙ ትራንስ የሆኑ ሰዎች ጥቃት ይደርስባቸዋል፤ይገደላሉም:: 

በአሜሪካ በጥቁርና ላቲ ትራንስጀንደር ሴቶች ላይ ጥቃቶች ይደርሳሉ፤ ይህ አንቺ ላይ ምን አይነት ተፅዕኖን ያሳድራል? 

በጣም ትልቅ ተፅዕኖ አለው:: ጥቁር መሆን ብቻ ራሱን የቻለ ተግዳሮት አለው:: እዚህ ላይ ሴት፣ ትራንስ እና ስደተኛ መሆንን መጨመር ነው:: እነዚህ የተለያዩ ማንነቶች ዒላማ ውስጥ ይከቱኛል::

በምስራቅ አፍሪካ የትራንስ ሰዎች ሁኔታ ምን ይመስላል?

ስጋት፣ ፍራቻ፣ አደጋ እና መፈናቀል(መሰደድ) 

አለም ላይ የትራንስ ሰዎች ሁኔታ እየተቀየረ ነው ብለሽ ታስቢያለሽ – በይበልጥ ደግሞ በምስራቅ አፍሪካ?

አለም ላይ አዎ! በምስራቅ አፍሪካ ግን አይደለም:: ልዩነቶታችንን በመቀበል ረገድ ገና ብዙ ይቀረናል::

ለለውጥ ትልቁ ተግዳሮት ምንድነው? ለውጥ ለማምጣትስ እንዴት መንቀሳቀስ አለብን? 

ትልቁ ተግዳሮት ግንዛቤ አለመኖር ነው:: አለም እኛ እንዳለን እና ያለስጋት የመኖር መብታችንን እንደምንጠይቅ ማወቅ አለበት:: ስለማንነታችን ይበልጥ መናገር አለብን:: እናም ለሰብዓዊ መብታችን ትግላችንን መቀጠል ነው::

አሜሪካ ላይ ከምታደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ምን ልምድ መውሰድ እንችላለን? እንደ BLMP አባልነትሽ በአፍሪካ ውስጥ እየተንቀሳቀስን ላለን ሰዎች የምታካፍይን ነገር ካለ?

ሙሉ ለሙሉ የእኔነት ስሜት በማይሰማን የባዕድ አገር ላይ የራሳችንን ጎሳ መፍጠር ድርብርብ ማንነቶቼን (ሴት፣ጥቁር፣ ትራንስ) ሳልተው ለማህበረሰቤ እንድቆም ረድቶኛል:: ራሴን ያገኘሁት BLMP በማግኘት ነው (ይሄንን ስፅፍ እንባ እየተናነቀኝ ነው) BLMPን ከማግኘቴ በፊት የእኔነት ስሜት አይሰማኝም ነበር::

ምን ያስደስትሻል? 

ከውይይት እና አጀንዳ ውጪ በሚያደርጉን ቦታዎች ላይ ማይክ ተቀብሎ ለጥቁር ስደተኛ LGBTQIA ሰዎች ድምፅ መሆን፣ በትልቁ በተከፈተው የቤቴ መስኮት ጎህ ሲቀድ እያየሁ የእርድ ወተት ሻይ መጠጣት ያስደስተኛል ሃሃ እንዲህ አይነት ትንንሽ ነገሮች ያስደስቱኛል::

በምስራቅ አፍሪካና ባሻገር ላሉ ወጣት ትራንስጀንደሮች ምን ምክር አለሽ? 

ነገሮች ይሻሻላሉ! ልክ ናችሁ! ተስፋ አትቁረጡ! ታስፈልጋላችሁ! አንድ ቀን ወደኋላ ታዩ እና በራሳችሁ ትኮራላችሁ::

Leave a Reply