ራስን ለመቀበል እና የስሜት ቀውስን ለማሸነፍ መማር

ፍራቻ፣ ስጋት እና ድካም…….ኩዊር እንደሆንኩ ሳውቅ የተሰሙኝ ስሜቶች ነበሩ። ወግ አጥባቂ እና ሀይማኖተኛ የሆነ ኢትዮጲያዊ ማህበረሰብ በዛው ልክ ደግሞ ብዙም ወግ የማያጠብቅ ሆኖ ኩዊርነትን የሚጠላ አሜሪካዊ ማህበረሰብ ውስጥ ማደግ ኩዊርነቴን ማወቄ ሊሰጠኝ የሚችለውን ደስታ አልሰጠኝም። ለመጀመሪያ ጊዜ የነገርኩት ሰው በቅርቡ ያወቅኩትን ማንነቴን ሳውቅ ምን እንደተሰማኝ ጠየቁኝ፤ “የተጨቆነ ፖክማን ጎ እየተጫወትኩ እንደሆነ ይሰማኛል ፟ ሄጄ ሁሉንም የተጨቆኑ ማህበረሰቦች ጥቁር ሴቶች፣ ስደተኞች እና አሁን ደግሞ ኩዊር መያዝ እንዳለብኝ በጣም ይሰማኛል”

ለብዙ ፆታዎች ስሜት እንዳለኝ ለመረዳት 22 ዓመታት እና ቋሚ ድብርት መከላከያ መድሃኒት መውሰድ ነበረብኝ። ይህ ራሴ ላይ የነበረኝን እና ውስጤ ያስገባሁትን ኩዊር ጥላቻ ለመታገል የመጀመሪያው እርምጃ ነበር።

ልጅ ሆኜ በእኔም በማህበረሰቤም ውስጥ መቀበል አልነበረም። እንደ ሴት ልጅ ፍቅር እና መወደድን ለማግኘት በሁሉም መልኩ እራሴን ቤተሰቦቼ ባመኑበት መንገድ መግፋት ነበረብኝ። ይህ ለፍቅር ያለኝን አረዳድ ከማዛባት አልፎ በውስጤ ለረጅም ጊዜ የቆየው እኔነቴን ጥርጣሬ ውስጥ ከቶት ነበር። ሁሌም ግልፅ የነበረልኝ ነገር የሚሰማኝ እና የማደርገው ትክክል እንዳልሆነ እና በመፅሀፍ ቅዱስ ህጎች አንድ በማህበረሰቡ መሰረት መስተካከል እንዳለበት ነበር። ለብዙ ፆታዎች ስሜት እንዳለኝ ለመረዳት 22 ዓመታት እና ቋሚ ድብርት መከላከያ መድሃኒት መውሰድ ነበረብኝ። ይህ ራሴ ላይ የነበረኝን እና ውስጤ ያስገባሁትን ኩዊር ጥላቻ ለመታገል የመጀመሪያው እርምጃ ነበር።

የህይወቴን አብዛኛውን ጊዜ ራሴን በመቆጣጠር ወይም ከተጠመቅኩበት አስተሳሰብ የተቃረነ ሃሳብ ሲኖረኝ እራሴን በመተቸት ነው ያሳለፍኩት። አንዴ ቤተሰብ መሀል ሁሉንም በውስጤ ለመያዝ ትንፋሼን ከመያዜ የተነሳ ራሴን አዙሮኝ ያውቃል። ራሴን አፍኜ ነበር። በተወሰነ መልኩ እውቅናን፣ ፍቅርን፣ ክብርን እና መወደድን በመፈልግ እየታገልኩ ነበር ግን ደግሞ የሴትነቴን አመለካከት እና ኩዊር ማንነቴን መግለፅ ደህነቴን አደጋ ላይ ይጥለው ነበር። በአካል፣ በአዕምሮ እና በመንፈስ ሙሉነትን እየፈለግኩ ነበር/ነው።

ይህ እራሳችንን ከፋፍሎ የመግጠም ሂደት በጣም የሚጎዳ ሲሆን በደህንነት፣ ግንኙነት እና እውነተኝነት መካከል አጣብቂኝ የሆነ ምርጫ እንድንመርጥ ያስገድዳል።

ማህበረሰባችን ውስብስብ የሆነውን የኛ አካል ክፉ ጥላቻ እና መግፋት ሲያደርስብን ምን እናተርፋለን? በተደጋጋሚ እራሳችንን በመክዳት ከእራሳችን እንለያለን። ወደ እውነተኛ ማንነታችን ስንሳብ በሚያም መልኩ ያደግንበት ማህበረሰብ እንዲቀበለን መፈለጉን እንገፋዋለን። ኩዊርነታችንን በመውሰድ እና በመተው በጥንቃቄ የተቀረፀው ውጫዊ ማንነታችንን ብቻ ቦታ እንሰጣለን። ይህ እራሳችንን ከፋፍሎ የመግጠም ሂደት በጣም የሚጎዳ ሲሆን በደህንነት፣ ግንኙነት እና እውነተኝነት መካከል አጣብቂኝ የሆነ ምርጫ እንድንመርጥ ያስገድዳል።

ደህንነታችንን ከእውነተኛነታችን እንድንመርጥ ለሆንን በሙሉ የሚያመጣው አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጫና አድካሚ ነው። ብዙዎቻችን ይህንን ህመም ተሸክመን እንኖራለን። ይህንን ህመም ለመሸከም፣ ለማስታመም እራስን ለመቀበል ያለው ውስጣዊ እና ውጫዊ ትግል ወደ የተለያዩ መንገዶች ይወስደናል። ይህ መንገድ የተለመደው በማውራት መታከም፣ ሱስ፣ የቆየና የምናውቀው ግንኙነቶች እና እርስ በእርስ ሊሆን ይችላል። ኩዊርነቴን በማወቄ ደስታ ባላገኝም፤ ስለወደፊቱ ተስፋ ባይሰማኝም ከሌሎች ጥቁር ኩዊር ሰዎች ጋር በኢንተርኔት እና በአካል የፈጠርኩት ትውውቅ በተወሰነ መልኩ መድሀኒት ሆኖልኛል። እነዚህ ትውውቆች እራሴን ስለመውደድ እና ስለማህበረሰብ አስተምረውኛል ለዚህም ብሎም ለጋራ እና ለየግል ነፃነታችን ለሚያደርጉት ሁሌም ምስጋና ይሰማኛል። በዚህ ጥልቅ በሆነ፣ በሚታይ እና በማንኛውም ቦታ ወይም ሁኔታ በሚሰፋ መልኩ ደስታችን ከሀዘን በተደባለቀበት አለም እነዚህ ትውውቆች እንዳልም ረድቶኛል።

Leave a Reply