የፆታ ተማርኮዬን ገና ሙሉ በሙሉ ለመፈተሽ(ለማወቅ) እድሉን ያላገኘሁኝ ባይሴክሹዋል ነኝ::
ላስረዳችሁ
በተደጋጋሚ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ የምገባ ተስፋ ቢስ አፍቃሪ ነኝ:: እስከማስታውሰው ድረስ በጣም ለረዥም ጊዜ ከወንዶች ጋር የፍቅር ግንኙነት ኖሮኛል::
ነገሩ እንዲህ ነው፥ ከጉርምስና እድሜዬ ጀምሮ ለሴቶች ያለኝ ተማርኮ ሁሌም በጣም ግልፅ ነው:: እነዚህ ስሜቶች ባደጉ ቁጥር የማወቅ ጉጉቴ ጠነከረ:: የወሲብ ግንኙነቴ በጨመረ ቁጥር ምኞቴንም ለመመርመር ቻልኩ::
በሚያሳዝን ሁኔታ እድገትን የሚያበረታታ እድልን ያገኘሁት በጣም ትንሽ ቦታ ነበር:: ይሄ የሚሆነው ፓርቲ ላይ ወይም ከከተማ ውጪ ነገር ግን ሁሌም ከሆነ ያህል መጠጥ በኋላ ነው::
በኩዊር ጓደኞቼ መሃል እንኳን የኩዊር ደጋፊ ተደርጌ ነበር የምታሰበው::
አሁን ያለሁበት የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ከመግባቴ በፊት ኩዊር ሴቶችን አግኝቶ ለማዋራት፣ ለመወያየት፣ ግንኙነት ለመፍጠር ሞክሬ ነበር:: ሙከራዬ ተሳክቶልኝ ብዙ ሴቶች ቴክስት ያደርጉልኝ ነበር፣ ይዳሩኝ እና እንገናኝ ይሉኝ ነበር:: በዚህ ሰሞን አለባበሴ እና አቀራረቤ – ነበር:: ምናልባት ይሄም ረድቶ ይሆናል::
በዛ ጊዜ ሌላ ያየሁት ነገር እነዚህ ኩዊር ቦታዎች ለቋሚ ወይም ዘላቂ የፍቅር ግንኙነት እምብዛም አልነበሩም:: ሳይታሰብ ግን አሁን ካለኝ የፍቅር አጋሬ ጋር ግንኙነት ጀመርን::
አሁን ላይ ቤተሰብ መስርተን እየኖርን ነው ነገር ግን ሁሌም ያልመረመርኩት ማንነቴን ምን ይሆናል አስባለሁ:: እንደዚህ ሩቅ እስኪመስለኝ ድረስ አፈላጊ ነው ብዬ አላሰብኩም ነበር::
አሁን ላይ ሁሌም ከኩዊር ጓደኞቼ ጋር ስለማሳልፍ ስለጋራ ማንነታችን እና ስለራሴ ማንነት አረዳዴን ለመሞገት እድሉ ተከፍቶልኛል:: ከዛም ወዲህ በአዕምሮዬ ብዙ ጥያቄዎች ተነስተዋል::
ከነዚህ ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ “የፆታ ተማርኮዬ ምንድነው?” የሚለው ነው:: ይሄን የጠየኩበትን ቀን በደንብ አስታውሰዋለሁ፣ ከጓደኞቼ ጋር ፓርቲ ላይ ነበርኩ፣ በግሩፕ ተቀምጠን እያለ አንድ የማውቀው ሰው “ራስሽን ምንድነኝ ብለሽ ታስቢያለሽ?” አለኝ:: ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ጥያቄ ተጠይቄ ባላውቅም ዳሩ ግን ታማኝ ለመሆን ወሰንኩና ባይ ነኝ አልኩኝ:: የተደነቀ አይመስልም ነበር፤ ደስ አለኝ::
ይሄ አጋጣሚ በጣም ወሳኝ ነበር ምክንያቱም ከጥቂት የቅርብ ጓደኞቼ ውጪ ሁሌም ኩዉር ሰዎችን እንደሚደግፍ ሰው ብቻ ነው የምታየው::
በማህበራዊ ሚድያ ገፆቼ ላይ ስለኩዊር ጉዳዮች ማውራት ምንም አይመስለኝም ነበር:: ይሄም ብዙዎች ላይ የፆታ ተማርኮዬን ጥያቄ ውስጥ አስገብተውት ነበር:: መጀመሪያ ላይ አልመልስላቸውም ነበር:: ነገር ግን ብዙ ባወራሁ ቁጥር ብዙዎች ወደገፄ ይመጡ ጀመር ፥ ይህም የራሱን ችግር ይዞ መጣ፤ ማስፈራራት፣ ስድብ፣ እና ኦንላይን ጥቃት::
ከሴት ጋር ሆኜ ስለማላውቅ “ማረጋገጫ” አልነበራቸውም፣ በኩዊር ጓደኞቼ መሃል እንኳን የኩዊር ደጋፊ ተደርጌ ነበር የምታሰበው:: በዚህና በብዙ ምክንያት እኔም “የኩዊር ደጋፊ” በሚለው ስያሜ ሄድኩ::
ሌላ የማስታውሰው ነገር ቤተሰብ ከመሰረትኩ በኋላ የድሮ የት/ቤት ጓደኛዬ ማህበራዊ ገፄ ላይ “እግዚአብሔር ስለጠበቃት በጣም ደስ ብሎኛል፤ ሁሌም ጌ መሆኗ ያሳስበኝ ነበር ነገር ግን አሁን እንዳልነበረች አወቅን” ብሎ ኮሜንት አደረገ።
አልነበርኩም?
ተመልከቱ እንዴት ማንነቴን መደበቅ እድል እንደሆነ፣ “የኩዊር ደጋፊ” ተብሎ መታሰብ እና ደህንነትን ማግኘት::
ባይሴክሽዋል በተቃራኒ ፆታ አፍቃሪያንም ሆነ በኩዊር ሰዎች ራስን የመመርመር ምዕራፍ ይመስላቸዋል:: አንዳንድ ያዋራኋቸው ሴቶች የተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ውስጥ እንዳለሁ ሲያዩ ወደትክክለኛው ህይወት ከመግባቴ በፊት ያሳለፍኩት መዝናናት መስሏቸዋል::
አንዳንድ ያዋራኋቸው ሴቶች የተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ውስጥ እንዳለሁ ሲያዩ ወደትክክለኛው ህይወት ከመግባቴ በፊት ያሳለፍኩት መዝናናት መስሏቸዋል::
መማረክ እና ጥቂት አስደሳች ምሽቶች ስለነበሩ ባይሴክሽዋል መባል ይችላል? መጠየቅ ጀመርኩ::
ይመስለኛል አስራ አምስት አመቴ ገደማ ነው ጉግል ላይ ሄጄ የተለያዩ የባይሴክሹዋል ገፅታዎችን የመረመርኩት:: በድጋሚ ስሜቴ ግልፅ ነበር:: እውነት ለመናገር ብዙም አላስቸገረኝም ነበር:: ሸክምን መጋፈጥ አይጠበቅብኝም፣ ሌሎች ኩዊር ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጥላቻ እኔን አያጋጥመኝም፣ በብዙ ጥቅም አለው ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ የመገፋት(ያለመካተት) ስሜት አለው::
ስለዚህ የራሴን ማንነት ሳልሰይም የተሰጠኝን “የኩዉር ደጋፊ” ስያሜ እየተከተልኩ ማነው የኔን ኩዊርነት ፍቺ የሚሰጠው እላለሁ:: ጌ ነኝ ለማለት ድፍረቱ የሌለኝ ለሚመስላቸው? አዎ ባይ ነኝ!!! በተቃራኒ ፃታ አፍቃሪያን ግንኙነት ውስጥ ብሆንም ያለኝ ስሜት እውነት ነው፤ የማንነቴ ክፍልም ነው:: በድጋሚ አዎ ባይሴክሽዋል ነኝ!