ዜማ ለቤተሰብ

“የተመኘችውን የመኖር መብት አላት” ትላለች ሳቤላ:: እንደ እህት ያላት ሚና እህቷን ሙሉ ለሙሉ መደገፍ እንደሆነ ታብራራለች፤ “ተቃራኒ ፆታ አፍቃሪ ነው ትክክለኛው ያለው ማነው?” ብላም ትጠይቃለች::

ይሄ በኢትዮኩዊር ፖድካስት በዚህ ወር የነበረው በአርባዎቹ እድሜ ያለች ኢትዮጵያዊት ሴት በግልፅ ለኩዊር እህቷ ያላትን ፍቅር እና ድጋፍ ካወራችው የተወሰደ ነው:: እንደ አንድ አዲስ አበባ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ኩዊር ሰው በሳቤላን ቀላል ነገር ግን ጠንካራ ድጋፍ አለመገረም አይቻልም::

እኔም በቤተሰብ ውስጥ ድጋፍን ካገኙ መሃል እድለኛ ነኝ::ለቤተሰቦቼ ስለማንነቴ ስነግራቸው የነበረው ሁኔታ ቢለያይም ፍቅራቸው፣ መቀበላቸው እና ድጋፋቸው አንድ ነው:: 

ለአንደኛው ወንድሜ ስለፆታዊ ተማርኮዬ የነገርኩትን ጊዜ አስታውሳለሁ:: በቅርብ አግኝቶት ስለማያውቀው የአክስታችን ልጅ ሲጠይቀኝ ሌዝቢያን ናት ብሎ ጠርጥሮ ሊያስፈራራኝና ሊጎዳኝ ስለሞከረ አዋርቼው አላውቅም አልኩት:: ወንድሜ በጣም ተቆጣ:: ፀያፍ ቃላትን ሲጠቀም አይቼ የማላውቀው ወንድሜ እንደዚህ በቁጣ ሲደረድረው ደነቀኝ “ምን አገባው?” አለ፤ “ሌዝቢያን መሆን ምን ችግር አለው ብሎ አስቦ ነው?”

ወንድሜ (ቤተሰቦቼ) የኔን የፈለኩትን የመውደድ(ማፍቀር) መብት በመደገፉ ወይም እኔን በመቀበሉ ሜዳሊያ አይገባውም፤ ይሄ በትንሹ ማንም ቤተሰብ ሊያደርገው የሚገባ ነው ብዬ አምናለሁ:: ነገር ግን በአክስታችን ልጅ ድርጊት መቆጣቱ እና ብዙ ኩዊር ጓደኞቼ ለቤተሰባቸው መናገር እንዴት ከባድ እንደሆነ በማየቴ ይበልጥ ዋጋ እንድሰጠው አደረገኝ::

እርግጥ ነው በኢትዮጵያውያን መሃል ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያንን የሚደግፉ ከተመሳሳይ ፆት ጠል ጋር ሲነፃፀር የተጣመመ ነው፣ ስር የሰደደ ለውጥ ማምጣትም ተስፋ አስቆራጭ ስራ ይመስላል:: እንደእኔ አይነት ቤተሰቦች ግን ተስፋ ይሰጡኛል:: የሚደግፉኝ እህቶች፣ ወንድሞች፣ የእህት የወንድም ልጆች እና ጓደኞች አሉኝ:: እዚሁ ኢትዮጵያ ተወልደው ያደጉና ኩዊርነት ተፈጥሮዓዊ እና ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ተብለው የተማሩ፣ የስርዓተ ፆታ እና ፆታዊ ተማርኮን ሰፊ ተፈጥሮ እንዳይቀበሉ የተማሩ፣ እንዲሁም እንደ ጀንደር ቤንዲንግ (gender blending/blurring) ኩዊር ሴት የምድር ቆሻሻ እንደሆንኩ ተደርገው የተቀረፁ ነበሩ:: ስለማንነቴ ስነግራቸው እነዚያ አፍራሽ ሐሳቦች ትርጉም መስጠት አቆሙ ምክንያቱም የግል ሃሳባቸውም መስጠት የሚችሉበት “ጉዳይ” ሳይሆን ለፆታ ዝንባሌና ተማርኮ መብት ያላት ሰው /እህት፣ ልጅ፣ አክስት፣ጓደኛ ሆነ/:: ዕጣዬ በ “ባህል” እና ሃይማኖት ድፍረት የሚፈረጅ ስርዓተ ፆታ ወይም ፆታዊ ተማርኮ ሳይሆን ይልቁንስ ውስብስብ ማንነት ያለኝ የማርቲን ሉተር ኪንግን አባባል ልዋስና “በገፀ-ባህሪዬ ይዘት” መፈረጅ ያለብኝ ሰው ነኝ::

አሁን ለLGBTQIA+ ሰው ከመቀበል አልፈው ለእኛ ተከራካሪ ሆነዋል:: አንዳንዴ ተመሳሳይፆታ ጠልነትን ፊለፊት ይጋፈጣሉ፣ አንድ ጊዜ እህቴ ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ጠል እየሆነ ያለ ጓደኛዋን LGBTQIA+ የሆነን ሰው የምትፈራው ከራስህ ተባዕታይ ጋር ስላልተማመንክ ነው ብላዋለች:: በሌላ ጊዜም ወይ ወሬ ይቀይራሉ ወይ ደግሞ “ላለመስማማት እንስማማ እና እንለፈው” ይላሉ:: አንዳንዴም በአንድ ሰው ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ጠልነት ተበሳጭተው ደውለው ሲነግሩኝ ያንን ለማፋጠጥ ከእኔ ይልቅ እንደደጋፊ እናንተ የበለጠ ሃይል አላችሁ እላቸዋለሁ::

ዕጣዬ በ “ባህል” እና ሃይማኖት ድፍረት የሚፈረጅ ስርዓተ ፃታ ወይም ፃታዊ ተማርኮ ሳይሆን ይልቁንስ ውስብስብ ማንነት ያለኝ የማርቲን ሉተር ኪንግን አባባል ልዋስና “በገፀ-ባህሪዬ ይዘት” መፈረጅ ያለብኝ ሰው ነኝ::

ይሄ ታዲያ የኩዊር ገነት ውስጥ ነኝ ማለቴ አይደለም:: ተግዳሮቶች፣ ብስጭቶች እና ከባድ ጊዜዎች አሉን ነገር ግን ቤተሰቦቼ አብረውኝ እንዳሉ አውቃለሁ:: ያለገደብ:: ቤተሰቤ የሚሰጠኝ ትልቅ ሽፋን ለዚህ አገር እንቅስቃሴዬ ወሳኝ ነው:: ቤተሰቦቼ አይቀበሉኝም ብዬ መቼም አልፈርም፤ እነሱ እንደሚቆሙልኝ እና እንደሚከራከሩልኝ ማወቅ እዚህ ቤቴ የምለው ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ጠል ሃገር ላይ እንቅስቃሴዬን እና ኑሮዬ ያስማማልኛል::

እናም ከቤተሰቤ ጋር ባለኝ ውይይት በምንችልበት ቦታ እንደኩዊር ሰው እስከሁሉ ማንነታችን የሚያዩ እና የሚቀበሉን የራሳችንን ምቹ ቦታ መፍጠር አለብን:: እኔ ማንነቴን መናገሬ እና ያለምንም ይቅራታ ኩዊር ማንነቴን መኖሬ ቤተሰቦቼ ራሳቸውንና አመለክልከታቸውን እንዲፈትሹ እና ከኔም ጋር በግልፅ ውይይት እንዲያደርጉ አበረታቷቸዋል::

Leave a Reply