ከሴት ልጅ ጋር የመጀመሪያ መሳሳም

# 1

ትልቅ ፍርሃት…ጥልቅ ጉጉት… ድብልቅልቅ ያለ ስሜት:: ሴት ከመሳሜ በፊት ከወንድ ጋር ተሳስሜ አውቃለሁ:: ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት የሳምኩ ቀን ነው ለወንድ ልጅ ምንም ተማርኮ እንደሌለኝ የገባኝ:: ከንፈር ለከንፈር ከመነካካት በፊት ያለው የጣት ለጣት ጫፍ የመነካካቱ ግለት በራሱ ሌላ ማብራሪያ ይፈልጋል:: ልብ በአፍ ልትወጣ ያህል ትሮጣለች፤ ሰውነት ፍም ይፍምባት ይመስል ትግላለች:: የግለት ትንፋሽ…ሃፈረት ይሁን ፍራቻ ከንፈር መንቀጥቀጥ..በአናት ላይ ዘይት ሲፈስ እንዳለው ስሜት ቅልጥ ማለት…

# 2

ያን ቀን ከቤቴ ለመውጣጥ ስለባብስ እንደተለመደው ብዙ የሚያስበው እና በጣም ጠንቃቃ የሆነው ማንነቴ ቅልል ያለ እና ነፃነት ተሰምቶት ነበር:: ወዴት እየሄድኩ እንዳለሁ አውቅ ነበር፤ መላ እኔነቴም እሺ ብሎ ነበር:: 

ደስታ፣ ጉጉት ፣ መሰጠት :: ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት እየሳምኩ ነው እና ለምን አልፈራሁም?  አዲስ ነገር ግን እንግዳ ያልሆነ:: አዕምሮ ሰላም፤ ልብ ሩጫ:: ማቆም አልፈለኩም:: ለማሰብና ለማገናዘብ ጊዜ አልነበረም:: ከስሜቴና ልቤ መሻት ጋር ተዋህጄ ነበር:: ተሰማሁ፣ ታየሁ:: ለመሳም (ሲጠብቅ) በተደጋጋሚ እንደምመጣ አውቄ ነበር::

# 3

ኮሌጅ ላይ ክለብ መውጣትን ዋሽተን ስለምናደርገው፣ እንደሁልጊዜው እኔ ጋር “ለጥናት” ብለን ያደረችበት ቀን ነው:: ሁለታችንም በትንሹ መጠጥ ጠጥተናል:: ሳይጠበቅ የሚመስሉ ግን ያልሆኑ መነካካቶች ተጀመረ:: የማስታውሰው ሰውነቴ መሞቅ መጀመሩን ነው:: ጀርባዋን ሰጥታኝ ስለነበር ዞራ በደመነፍስ ሁልጊዜ የምናደርገው ይመስል ተሳሳምን:: የተሳሳምነው በትንሹ ነበር ነገር ግን የጋለ ስሜት ያለው ነበር:: ከሌላ ሴት ጋር እናደርገዋለን ብለን ባልጠበቅነው መልኩ አካላዊ ንክኪዎች ኖሩን:: በጣም ውድ ጓደኛዬ ናት፤ እና የትልቅ ጓደኛሞች ግሩፕ አባል ነን:: በነጋታው በጠዋቱ ሄደች፤እኔ ሳላስተውል ለመሄድ ሞከረች:: ሰምቻታለሁ ግን በደንብ እንኳን አላየኋትም::”ቻው” ብላ ሄደች…ነገሮች የሚያሳፍሩ ሆኑ:: ባለመተያየት፣ በቀጥታ ባለማውራት ባጠቃላይ የእርስ በእርሳችን አንድ ቦታ ላይ መኖርን እውቅና ሳንሰጥ አንድ ሙሉ ወር ቆየን:: ሁላችንም እንደገና ክለብ እስክንወጣና ትንሽ የስካር ስሜት ኖሮ እስከምናወራው፣ ስቀን ወደኋላችን ለማስቀመጥ እስክንወስን ድረስ:: አንድ ያደረግነው ነገር ሆኖ ቀረ::

Leave a Reply