የአመፃ ግጥሞች

ፀሀይ ማታ ዘልቃ
እዚህ ጎኔ ወድቃ
ለኔ ብቻ ደምቃ
እኔን ብቻ አሙቃ

   እንዲህ ትለኛለች

“እኔና ሙቀቴ
ክንድሽ መቀነቴ
ደረትሽ ሌማቴ
ጣይን ያክል ግለት  ይዤ በገላዬ
ቀለጥኩ ጡቶችሽ ስር  ካለም ተነጥዬ”

   እኔም እላታለሁ
  ውብ አይኗን እያየሁ 

   “እንዲህ እንደሆንን   እንደጋምኩ ካንቺጋ 
   የሰማይ ክዳኑ   ይጠርቀም ይዘጋ
   እንደተወሳሰብን   ዘላለም አይንጋ “

#የአመጻግጥሞች #theforbiddenlyrics

ግጥም እፅፋለሁ   ላንቺ ላንቺ ብቻ
ቃላት ተናጥቄ    ቤት መድፊያ ቤት መምቻ
ያለም ቅኔና ቃል     ይበቃሻል ወይ
ስጽፍ ስፅፍ ውዬ   ሲያነቡሽ እንዳይ

#የአመጻግጥሞች #Theforbiddenlyrics

ሊሊት የቃቄዋ

Leave a Reply