ለብዙ ኩዊር ኢትዮጵያውያን የኩዊር ፊልሞች ራስን መቀበል እና ብቻዬን አይደለሁም የሚለውን ለመገንዘብ ትልቅ አስተዋፅዖ አድርገዋል:: ምንም መረጃ በሌለበት ሃገር የምዕራባውያን ፊልም ፃታዊ ተማርኮና ዝንባሌያችንን እንድንጠይቅበት አድርገውናል::
ነገር ግን የኩዊር ፊልሞች ሁሉን አካታችነት ይጎድላቸዋል፤ ሁሌም ደግሞ የተለመደ ገፀ ባህሪይን ይይዛሉ:: የኩዊር ገፀ ባህሪያት በፊልሞቹ ውስጥ በጣም ጥቂቱን ቦታ የሚይዙ ናቸው:: የፊልሙ ዳይሬክተሮች “አካታች ነን” ለማለት ብቻ የሚያስገቧቸው ይሆናሉ:: በአብዛኛው የኩዊር ፊልሞች ደግሞ ተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪ ወንድን ብቻ የያዙ ይሆናሉ:: ባይሴክሽዋል፣ ትራንስጀንደር፣ ፍናፍንት እና ሌላ ፃታዊ ዝንባሌዎች በፊልሞች ውስጥ ብዙም አይንፀባረቁም:: ሌላው ከማልወደው የተለመደ ገፀ ባህሪይ ውስጥ የሌዝቢያን የሚደጋገሙ ገፀ ባህሪያት ናቸው:: አንዷ አግብታ ሌላኛዋ እሷን ለማግኘት የሚደረግ ጥረት፥ ይሄ የአንዳንድ ሴቶች ህይወት እውነታ ቢሆንም ሌዝቢያን ሴቶች ሁሉ ህይወታቸው እንዲህ ነው የሚለውን የግርድፍ ሃሳብ የሚያበረታታ ነው:: በተጨማሪም “ሌዝቢያን ደስ ይለኛል ፡ ጌ ወንዶች ግን አይኑን እንዳላይ” የሚለው ሴትነት ለወንድ የመጣች ንብረት አድርጎ የሚያስበው አለም ትራንስጀንደር ገፀ ባህሪያትን ሁሌም በተለምዶ “ሴታሴት” የሚባለውን ባህሪይ የምታንፀባርቅ እንጂ “ወንዳወንድ” ትራንስወንድ አይታይም:: ዋናው እና ትልቁ ችግር ብዬ የማስበው ደግሞ LGBTQ+ የሆኑ አርቲስቶችን አለማካተታቸው ነው::
ገፀ ባህሪያቱን እንጂ ኩዊር አርቲስቶችን የማያካትት ፊልም “ሁሉን አካታች ነኝ” ማለት አይችልም:: ኩዊር ሰዎችን እና ታሪኮቻቸውን ለአለም የማሳየት መንገዱ መጀመር ያለበት ኩዊር ለሆኑ አርቲስቶች መድረኩን በመልቀቅ ነው:: በኬንያ እንደተሰራው “Rafiki” እና በናይጄሪያ የተሰራው “Ife” ጥሩ ጅማሬ ነው:: ምናልባት ማን ያውቃል ከእኛም መሃል ውስብስብ የሆነውን የእያንዳንዳችንን ህይወት ሁሉን አካታች በሆነ መልኩ አንድ ቀን ሰረተው ያስደምሙናል:: በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን የተሰራ የኩዊር ፊልም ማየት ትልቁ ህልሜ ነው::
ብዙ ሳላወራ ፃታዊ ተማርኮ እና ፃታዊ ዝንባሌ ላይ ገፀ ባህሪያቶቹ በደንብ ተካተዋል የምላቸውን ልጋብዛችሁ
1. Moonlight
2.Elisa and Marcela
3.The Miseducation of Cameron Post
4. Boy Erased
5. Schitt Creek
6. Hearts Beat Loud
7. Orange Is the New Black: የሶፍያ ገፀ ባህሪይ