ኩራት (ፕራይድ) በእኛ እይታ

ግንቦት መጨረሻ እስከ ሰኔ ሶስተኛ ሳምንት ድረስ የፕራይድ ወር እንደመሆኑ ይሄንን ወር እንዴት እንደሚያሳልፉ፣ ምን ማለት እንደሆነ እና ይህንን ወር የሚገልፅላቸውን ፎቶ እንዲያካፍሉን ጥቂት ኩዊር  ኢትዮጵያውያንን ጠይቀን ነበር:: ምላሾቻቸውን እነሆ

መልካም የኩራት ወር

እንደገና ያ የዓመቱ ጊዜ ነው፤ የኩራት ወር

አዎ፥ ጌ እና ኩሩ ነኝ ነገር ግን ኩራቴ ጌ ሆኖ ከመወለድ አይደለም:: ራስን መቀበል ከመቻል እና የተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪ ጠል በሆነ ተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪነት በህግ የሚያስቀጣ የሆነ

ማህበረሰብ ውስጥ ተርፎ መኖር ከመቻል የመጣ ነው:: እኮራለሁ ምክንያት ጥላቻው እኔ ከመስበር ይልቅ ስላጠነከረኝ:: እኮራለሁ ምክንያቱም በወሲባዊ ዝንባሌዬ ምክንያት የሚያጋጥሙኝ ተግዳሮቶች ቢኖሩም የፈለኩትን ሁሉ አከናውኛለሁ፤ እቀጥላለሁም::

ምንም እንኳን ህብረተሰብ፣ ባህል እና ኃይማኖቱ ሌላ ቢሉንም በመያምኑ የኩዊር ማህበረሰባችንና የኩዊር መብት ደጋፊዎች(አጋሮች) እኮራለሁ:: ስለዚህ በዚህ የኩራት ወር ራሴንና ጥላቻን አጥብቀው የሚቃወሙትን አከብራለሁ:: እርስ በእርሳችሁ በመተባበራችሁ፣ አለሁ በመባባላችሁ እና ጠንካራ በመሆናችሁ አከብራችኋለሁ::

አዎ! ጠንካራ፣ ብቁ እና ኩሩ ሌዝቢያን ነኝ::

ፕራይድን ማክበር በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም እዚህ ያሉ ሰዎች የኔን መኖር እንዲያዩ እፈልጋለሁ፣ የኩዊር ማህበረሰቡን ጥረትና ብዙ ሰርተው ያለፉትንም ለማስታወስና ለመዘከር ጭምር ነው::

ይህ የእጅ ጌጥ ከእኔ ጋር ሶስት ዓመት ሆኖታል እናም በየዓመቱ ፕራይድ ወር ላይ አደርገዋለሁ:: አንዳንድ ሰዎች አይመቻቸውም፤ ምንም አይመስለኝም::

ራሳችሁን ሁኑ! ራሳችሁን ውደዱ፤ መልካም ፕራይድ!

የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከመላክ ውጪ ፕራይድ አክብሬ አላውቅም:: ይሄንንም የእጅ ጌጥ ኢትዮጵያ ውስጥ አድርጌው አላውቅም:: ስለብሰውም ምንም አይነት የተለየ ስሜት አልፈጠረብኝም ፍርሃቱ እንደነበረ ነው::

የምኮራው በልዩነት ከማያምን ማህበረሰብ በቅዬ አንድነት ሳይሆን አንድ አይነትነት በሚሰብከበት ዓለም እየኖርኩ ነገር ግን ራሴን በተሰማኝ እውነት ልክ ተቀብዬ በራሴ ትንሿ ዓለም ውስጥ የመኖር ብቃትን ስላገኘሁ ነው! 

በአሁን ጊዜ ጥልቅ ሃዘን ላይ ስላለሁ ፕራይድን እያከበርኩ ነው ማለት አልችልም ነገር ግን እጣን አጭሶ እነዚህን ሙዚቃዎች መስማት ለነፍሴም እና ለሰውነቴ እረፍት ይሰጠኛል:: በየስፍራው ለሚገኙ ኩዊር ስነ-ጥበብ እና ስነ-ጥበብ ባለሙያዎች ትልቅ ምስጋና አለኝ::

የተጠናከረ የኢትዮጵያ ኩዊር ማህበረሰብን ለመፍጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የበኩሌን ጥረት ለማድረግ የኮምፒውተር ላይ ኩዊር አራማጅ ሆኛለሁ:: አደገኛ ጥረት ቢሆንም ኦድሬ ሎርድ እንዳለችው “ኃይለኛ ለመሆን ስደፍር፣ ብርታቴን ለራዕዬ አገልሎት ስጠቀመው፣ ከዚያ መፍራት አለመፍራቴ አላስፈላጊ እየሆነ ይሄዳል::” ስጋት ያለውን ስራ እየሰራሁ ቢሆንም ኩዊር ማህበረሰብን ለመደገፍ በመሆኑ ኩራት ይሰማኛል:: በየዕለቱ::

Leave a Reply