
“የሆነ ጊዜ ላይ ዐለፍ ብዬ ሄድሁና ስቅስቅ ብዬ ዐለቀስኩ፤ ከደስታዬ የተነሣ እንደ ሕፃን ልጅ ነበር ያለቀስኩት። ልክ አዲስ እንደተወለድኩ ነበር ስሜቴ። ይመስለኛል ሁላችንም እየቦረቅን ነበር፤ ምክንያቱም በጎዳናው ላይ ወጥተን “አለን፤ ኩዊር ነን፤ በሁሉም ቦታ አለን!” በማለታችን።”
ቤቭለሪ ዲጽ
Gay and Lesbian Organization of the Witwatersrand (Glow) ተቋም መሥራች ናት። ያም ብቻ አይደለም የመጀመሪያው የአፍሪካ የኩራት ቀንን ካስተባበሩት ውስጥም ይጠቀሳሉ።

“አንድ ሰው ይህን ማድረግ አለበት፤ ጥቁር ነኝ፣ ሴት ነኝ፣ ጠበቃ ነኝ እናም ጮክ ብዬ እናገራለሁ። እኔ ያለፈው ትውልድ እኔን ነፃ ለማድረግ የተጋፈጠው ተጋድሎ ውጤት ነኝ። እናም ይህ ከባድ ውለታ ነው ለመጪው ትውልድ ልከፍልው የሚገባ።”
አሊስ ኔኮም
ካሞሮናዊ ጠበቃ ስትሆን፤ ካሜሮን ውስጥ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነት ወንጀል መሆኑን በመታገል ትታወቃለች።

“ለማኅበረሰቤ መብት ለመታገል ስል ራሴን በግልፅ ሌዚቢያንነቴን ማወጄ ተጽዕኖው በማኅበራዊ ትሥሥር ገፆች አማካኝነት ከኒዮርክ ተመልሶ ኡጋንዳና በዓለም ዙሪያ ይሰማል።”
ለይላ ባብሬ
ኡጋንዳዊ የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያ ስትሆን፤ እሷነቷን በግልፅ በሀገሪቱ ጋዜጣ ካሳየች በኋላ በ2007 ዓ.ም ከኡጋንዳ ተሰዳለች።

“በማኅበረሰቡ ውስጥ ለውጥ እያየሁ ነው እናም አሁን ለብቻቸው እንዳልሆኑ መረዳቱ አለ። አሁን ማንም [የLGBT ማኅበረሰብ] የሉም ሊለን አይችልም።”
ካሻ ጃኩሊን ናባጌስራ
ኡጋንዳዊ የLGBT መብት አራማጅና የLGBT rights organization Freedom & Roam Uganda ዋና ዳይሬክተር ናት።

“ትራንስ የሆኑ ሰዎች ለፖለቲካው ትኩረት ካልሰጡት፤ እንዴት የተለመደ ሕይወታቸውን ለመኖር ከባድ ስላደረገው ሕግና እንዴትስ መቀየር እንዳለባቸው ሊያውቁ ይችላሉ?”
ማላክ አል ካሺፍ
ግብጻዊ የመብት አራማጅ ስትሆን፤ የትራንስ ሰዎች መብት ተሟጋችነትና የትራንስ ጭቆናን በመታገል ትታወቃለች።

“ስለራሴ ግልጽ ሳደርግ፤ ያደረኩት ራሴን ነፃ ለማውጣት ነው። እንጂ የመብት አራማጅ ለመሆን አልያም የሆነ ነገር ማሳካት መቻሌን ለማረጋገጥ አልነበረም። በርግጥም ለራሴ ስል ነበር።”
ፓሜላ አዲ
ናይጄሪያዊት የመብት አራማጅ፤ የዐደባባይ ምሁር፣ የስክሪፕት ፀሐፊና የፊልም ባለሞያ ናት። ፓሜላ Ìfé የተሰኘው የሌዝቢያን የፍቅር ፊልም ዋና አዘጋጅ ስትሆን፤ ፊልሙ በNollywood ታሪክ ውስጥ የሌዜቢያን ፊልም በመሆን ተጠቃሽ ነው።

“ህልውናዬን እንዲያረጋግጥልኝ ሌላ ሰው ከጠበኩ፤ ይህ ማለት ራሴን እያታለልኩ ነው እንደማለት ነው።”
ዛነል ሞሂ
በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነችና በደቡብ አፍሪካ ውስጥም ቀደምት የሌዝቢያን መብት አራማጅ ስትሆን፤ በፎቶ አንሺነትም እንዲሁ የሽልማት አሸናፊ ናት።
Thank you for your efforts to make the world a better place
Thank you, Betty, for engaging with us.