ስርዓተ ፃታ በኩራት ሲዳሰስ

“ምን ይመስላል?” በተለምዶ “ወንዳ ወንድ” ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለመኖሬ ነበር የጠየቀችኝ::

ጥያቄውን ለመመለሽ ትንሽ ጊዜ ወሰደብኝ: 

“ይከብዳል” በስተመጨረሻ መለስኩኝ::

ሰዎች ያፈጣሉ:: በራሳቸው መንገድ ብቻ እንድሄድ ወይም ስርዓተ ፃታ አቀራረቤ በተቀመጠው “ሴት” እና “ወንድ” ሁለትዮሽ ለማዛመድ ያላቸውን ፍላጎት ይሻማባቸዋል::

ይከብዳል::

የነሱ ማፍጠጥ ከኔ ምንም አይነት ምላሽ ስለማያገኙ በተለያየ መንገድ ምቾት እንደነሳኋቸው ለማሳየት ይጣጣራሉ:: ቃላትን ይወረውራሉ:: “ከቤ” ብለው ይጠሩኛል፤ “ከበደ” ሲያጥር ነው:: የተለመደ የወንድ አማርኛ ስም ሲሆን አልፎ አልፎ “ወንዳዊ” አቀራረብ ያላቸውን ሴቶችንም ለመጥራት ይጠቀሙበታል:: ይሄ ሁሌ ምላሽን እንድሰጥ ያደርገኛል:: እንዲሰብረኝ ወይም “ቦታዬ ላይ እንድቀመጥ” ማድረጋቸው ነው::

ይከብዳል

ምክንያቱም “ቦታዬን እንዳውቅ” ተደርጌ አላደኩም:: ሁሌም እንደፈለኩ ሆኜ ነው ያደኩት፣ ቤተሰቤ በምንም አይነት ገፍተውኝ እና አስገድደውኝ ማህበረሰቡ “አግባብ ያለው” በሚለው መንገድ እንሄድ አላደረጉኝም:: ሁሌም ስርዓተ ፆታን ድብዝዝ እና ድብልቅልቅ ባለ መንገድ ነው የምረዳውም የምኖረውም።

ይከብዳል
ምክንያቱም ሰዎችን ለማስደሰት ራሴን እያደራደርኩ እንድኖር ተደርጌ አላደኩም::

ይከብዳል
ምክንያቱም የኢትዮጵያ ማህበረሰብ የተለመደው አካሄድ በምንም አይነት ዋጋ ተመሳስሎ መኖር ነው:: ልዩነት የሚያስጠምድ ነገር ነው::

ይከብዳል
ምክያቱም መጥመዳቸውን በምን መንገድ እንደሚገልፁ ሁልጊዜ ማወቅ አልችልም:: ወደኔ የሚወረወረው ቃላት ይሁን ቡጢ አላውቅም::.

ይከብዳል
ምክንያቱም የማያቋርጥ ፍርሃት እና ፍርሃት የሚያስከትለው ጉዳት ቢኖርም የራስን እውነት ለመኖር ሁልጊዜ መዋጋት አድካሚ ነው ፡፡

ኩሩ
ምክንያቱም ለራሴ እውነትን በመኖር ቀጥያለሁ ፤ ይቅርታ የማይጠይቅ ድብዝዝ እና ድብልቅልቅ ያለ ስርዓተ ፃታን የያዝኩ ኩዊር ሴት ነኝ::

Leave a Reply