ስንጥቆች

የሚያስፈልገንን ሽፋን ይሰጠናል ብለን በማሰብ እውነተኛ ስሞቻችን ያልሆኑ ስሞችን ልንጠቀም እንችላለን። በድረገፆቻችን የት እንዳለን እንዳንታወቅ በይነመረብ ላይ ስንሆን እንደ ቪፒኤን ያሉ የደህንነት እርምጃዎች ልንጠቀም እንችላለን። እንዲያውም ስማችንን ፣ የስርዖተ ፆታ እና ወሲባዊ ዝንባሌያችንን በቅርብ የምናውቃቸው ሰዎች ብቻ እንዲያውቁ በማድረግ እንቅስቃሴያችንን ልንገድብ እንችላለን ።

የሚያሳዝነው ግን መቶ በመቶ የሚሆን ጥበቃ የለም ። ራሳችንን የምንጠብቅበት ብቸኛው መንገድ ማንነታችንን ከሁሉም ሰው መደበቅ ነው። ወይም ደግሞ ራሳችንን ከራሳችን መደበቅ። ይህ ደግሞ በመታፈንና በፍርሃት ምክንያት የሚመጣ የዝግታ ሞት ነው ። ስለዚህ መጽናት አለብን ። ስንጥቆቹ የእኛ ሞት ሊሆን እንደሚችሉ ብናውቅም ነገር ግን የምንተነፍስባቸው ቦታዎችም መሆናቸውን በማወቅ ስንጥቆቹ ውስጥ ብርሃንን መፈለግ አለብን። 

ማንነታችንን ካለፈቃዳችን ለሌሎች ከሚናገሩ ክፉዎች ይጠብቀን። በፍርሃት ምክንያት ከመሞት ይጥብቀን። ከማያቋርጠው የተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪ እና ትራንስ ጠልነት ለአፍታ እረፍት የምናገኝበት ቦታ ይስጠን ። ሊቋቋሙት የማይቻል ስጋት ቢያጋጥመንም እንኳን መኖርን እንምረጥ ።

Leave a Reply