በቅርብ ቀን፡ የንስንስ ፕራይድ እትም

ከአንካራ እስከ ዛግረብ ድረስ በብዛት በጎዳና ላይ ፈሰስን። የሁላችንም ጎዳና ላይ ራሳችንን የማግኘትና መግለጡ ሁኔታ ይለያያል። አንዳንዶቻችን ትልቅ ቀስተ ዳመና ባንዲራ እያውለበለብን፣ አንዳንዶቻችን ፊታችንን እየደበቅን፣አንዳንዶቻችን በፖሊስ ጥበቃ ተደርጎልን፤ አንዳንዶቻችን ከፖሊስ ጥበቃ አስፈልጎን፣ አንዳንዶቻችን እያንዳንዱን እርምጃችንን ከሚደግፉን አድማጮቻችን እና ተመልካቾቻችን  ጋር ሆነን፣ ሌሎቻችን ደግሞ ሊገድሉን ከሚተኩሱ ሰዎችን ጋር። ሁላችንንም አንድ የሚያደርገን የመወከል፣ የመታየት፣ የማክበር፣ የመቃወምና ማህበረሰብ የማግኘት አስፈላጊነት ነው። 

መኖሪያቸው  ከኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ዳርቻ ላይ ለሆኑ LGBTQ ኢትዮጵያውያን ለፕራይድ (ኩራት) አዲስ ትርጉም መስጠት አስፈልጎናል። ድብቅ ነገር ግን ግልፅ፣ ፍርሃት ቢኖረውም ድፍረቱን ማግኘት እና ሁልጊዜም አስተማማኝ ቦታዎችን ለመፍጠር ዝግጁ መሆን። ፕራይድ ዝግጅት እንዳልሆነ አውቀናል፤ ምንም እንኳን አንዳንዶች በዓሉን በግልጽ ለማክበር ጥረት ቢያደርጉም ። የቀስተ ደመና ባንዲራ እያውለበለቡና ኩራታችንን እያሳዩ ወደ ጎዳናዎች ቢወጡ የሞት ትዕዛዛቸውን እንደመፈረም  ለሆነ ኢትዮጵያውያን ኩራት ምን ማለት ነው?

በቅርቡ ልንለቅ  ባቀደው ሁለተኛው የንስንስ  እትማችን ላይ የምናስሰው  ይህንኑ ነው ። ኩራት ማለት ምን ማለት ነው? በበዓሉ ላይ ለመገኘት አጋጣሚ ለነበራቸው ሰዎች ምን ይመስል ነበር? ኩራት ይበልጥ ሰፋ ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል? በኢትዮጵያ የኩራት በዓል ሲከሰት በዓይነ ሕሊናችን ማየት እንችላለን? የኩራት በዓል ለእኛ አስፈላጊና ጠቃሚ ነው? 

እነዚህ በኩራታችን ጉዳይ ላይ ከተነሱት ጉዳዮች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው ። በኢትዮጵያም ሆነ በዲያስፖራ ከሚገኙ በርካታ የኢትዮጵያ LBTQ ሰዎች ጋር መነጋገራችን አስደሳች ሆኖ አግኝተነዋል። በውይይቱም ተበረታትተናል።

የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አስገድዶ ወደጓዳ መደበቁና እዚያው ማቆየት ተሳክቶለት  ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ብዙዎች የሚያሳዩትን የመቋቋም እና የወኪልነት ደረጃ መመልከት መንፈስን የሚያነሳሳ ነው። በብዙ ስጋት ፊት ብንሆንም እንኳ በማንነታችን ላይ ያለን ኩራት አሁንም መብራቱን ይቀጥላል ። 

ሁለተኛውን እትም ለማሳተም እንደተደሰትነው ሁሉ እናንተም ለማንበብ እንደምትደሰቱ ተስፋ እናደርጋለን። እስክናካፍላችሁ ቸኩለናል!

(የመጀመሪያውን የንስንስ እትም እዚህ ማውረድ ይችላሉ – አማርኛ እና እንግሊዝኛ)

Leave a Reply