ፍቅር ከቅርብ ጓደኛ

ከአንድ ታሳታፊ የደረሰንን ጥያቄ ለአንባቢያን በላክነው መሰረት አንድ አንባቢ እንዲህ መልሳዋለች። 

“እንዴት ናችሁ ኩዊር ኢትዮጵያ

የሆነች ነገር ላማክራችሁ ነበር። በጣም ከምቀርባት ጓደኛዬ ፍቅር ይዞኛል ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም። ሴት እንደምትወድ አውቃለሁ ግን ከነገርኳት ጓደኝነታችንን ቢያሳጣኝስ ብዬ ስለምፈራ ስሜቴን መግለፅ ፈራሁ። ምን ላድርግ?”

– አፍቃሪ  ከአዲስ 

ምላሽ፡

እንደ እኔ እንደእኔ ተናግሮ ቁርጥን ማወቅ ይሻላል ባይ ነኝ::እስከመቼ ጓደኛ ብቻ ነን ብለሽ እያሰብሽ ትቆያለሽ? አይከብድም? በይበልጥ ደግሞ በሆነ አጋጣሚ ከሆነ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት ብትጀምር ልትጎጂ እና ጓደኝነቱን ሊያከፋው ይችላል:: እንዳልሽው ምላሿ አዎንታዊ ብቻ ላይሆን ስለሚችል አሉታዊ ምላሿን እንዴት ነው የምቀበለው የሚለውንም ቀድሞ ማሰብ ነው::  ደግሞ አሉታዊ ምላሽ ከሆነ ቀረባታ! 

እንግዲህ በዚህ ተስማምተናል ብዬ ላስብና እንዴት ልንገራት ወደሚለው ልሂድ፥ 

1. ሻይ ቡና እንበል ብለሽ ያለሽን ስሜት በግልፅ መንገር:: ሀሳቡ ገና አስፈራሽ አይደል? ይሄ ካልሆነ ስሜትሽን መቼም ልታውቅ አትችልም:: መገላገል አይሻልም?

2. በአካል ቁጭ ብለሽ ለማውራት ከፈራሽ ምናልባት በቴክስት ያለውን ነገር ሁሉ ፅፈሽ መላክ

ሌላኛው አማራጭ ደግሞ

3. ሁለቱም በጭራሽ አይሆነኝም ካልሽ በጊዜ ሂደት ያላትን ስሜት ለመረዳት መሞከር እና መጠበቅ?

የትኛውንም ብትመርጪ መልካም እድል 

Leave a Reply