ሐሳቦች፡  ”ተባዕታይ ስርዐተ ፆታ”ን መኖር 

ይህ ፅሁፍ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በሚገኝ ትንሽ ከተማ  ከምትኖረው፤ የ”ተባዕታይ ስርዐተ ፆታ” (ማህበረሰባችን “ወንዳወንድ” የሚሏቸው ሴቶች)  ካላት ሌዝቢያን ጋር ከተደረገ ውይይት የተወጣጣ ነው። 

“በግሌ ከሌሎች እኩዮቼ በተለየ መልኩ ለተመሳሳይ ፆታ የተለየ አይነት መሣብ እንዳለኝ ልጅ በነበርኩበት ግዜ ለማወቅ ችዬ ነበር። ከፍ እያልኩ ስመጣም ይህ የተለየና መልስ ያላገኘሁለት ስሜት ጥሎኝ እንዳልሄደ ሳይ እና በተለምዶው የወንድ የሚባሉ ጨዋታዎችና አለባበሶች ምርጫዬ እንደሆነ ለመረዳት ስችል በወቅቱ በተወሰነ መልኩ ከራሴ ጋር  በነበረው የመግባባት ሁኔታ ሰላም እንዳገኝ አግዞኛል።”

ማህበረሰባችን Typically ሌዝቢያን ብሎ በአዕምሮው ስሎ ያስቀመጠው የኔ አይነት በተለምዶው ወንዳወንድ የሚባሉ ሴቶችን ስለሆነ በቀላሉ እይታ ውስጥ የሚገቡ ነገሮች ስለሚበዙ በራስ የመተማመን አቅሜን ፈትኖብኛል።

“ከሀይማኖት አኳያም አብዛኛው ኩዊር እህት ወንድሞቼ እንዳሳለፉት እኔም ከሀይማኖተኛ ቤተሰብ ሀይማኖታዊ በሆነ መንገድ ነው ያደግኩት። ነገር ግን  የሚሰማኝን ስሜት በጥሩ መልኩ እስኪገባኝና የተሻለ የአዕምሮ ብስለት እስኪኖረኝ ድረስ ለራሴ ከሚሰማኝ ስሜት ንፁህነትና የማንም ተፅዕኖ የሌለበት እንደመሆኑ መጠን በግዜው ብዙ ያልተረበሽኩ ቢሆንም የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ ከነበርኩበት የዕድሜ ክልል ተፅዕኖ አኳያ የሚሰሙኝ ስሜቶች ይበልጥ በጠነከረ መሳብና ፆታዊ ፍላጎቶች  ማደግና መሞላት ሲጀምሩ ብዙ ለፍቻለሁ። ምክንያቱም ማህበረሰባችን Typically ሌዝቢያን ብሎ በአዕምሮው ስሎ ያስቀመጠው የኔ አይነት በተለምዶው ወንዳወንድ የሚባሉ ሴቶችን ስለሆነ በቀላሉ እይታ ውስጥ የሚገቡ ነገሮች ስለሚበዙ በራስ የመተማመን አቅሜን ፈትኖብኛል። ምንም ያህል ውስጤ ያለው ስሜት ተፈጥሯዊ እንደሆነ ቢገባኝም ማህበረሰቤ በጫነብኝ ሀይማኖታዊ አስተምህሮ ግዝፈትም ተጎትቼ ከፈጣሪ የራቅኩና መመለስ እንዳለብኝ አስቤ በግል እስከ መፆምና መፀለይ ደረጃ ደርሼም አውቃለሁ። ያንን ማድረጌ በስሜት ደረጃ የቀየረልኝ ነገር ግን አልነበረም። “

“በኛ ማህበረሰብ ውስጥ Masculine ሌዝቢያን መሆን ከFeminine ሌዝቢያን በላይ ጥላቻውና ለአደጋ የመጋለጡ ሁኔታ የሰፋ ነው። እኔም በዚህ ሳብያ ከብዙ የጥላቻና የዘለፋ ንግግሮች እስከ አካላዊ ጉዳት የደረሰ ጥቃትን አስተናግጃለሁ።”

“እናም አሁን ቆም ብዬ ሳስበው እያንዳንዱ አልፌ የመጣሁበት መሰናክል ዛሬ ላይ ነፃ ሆኜ የፍቅረኛዬን እጅ ይዤ ካለስጋት በመንገድ የምጓዝበትን በራስ መተማመኔን ወስዶታል እንጂ ማንነቴን ከውስጤ ፈልቅቆ የሚያስወጣበት ጉልበት እንዳልነበረው ተረድቻለሁ።”

Leave a Reply