መፅሄቱን እንዴት አየሽው?
በመጽሔቱ በጣም ነው የተደሰትኩበት ምክንያቱም ብዙዎች አለን በዚህ ህይወት ውስጥ ተደብቀን ምንኖረው ማለትም ከራሳችን ጋር ትልቅ ክርክር ውስጥ የገባን እኔ ከሰው የተለየው ነኝ እንዴ ብለን እስከማሰብ ድረስ የደረስን። ከባህላችንም ሀይማኖታችንም ከማህበረሰቡም ያለው ተቀባይነት አናሳ መሆኑ ብቻም ሳይሆን እስከ ሞትም የሚያደርስ ስለሆነ። ስለዚህ በዚህ መፅሔት ማህበረሰቡ ያለውን የመቀበል አቅም ለመጨመር ያግዛል። እንዲሁም በዚህ ህይወት ውስጥ ላለነው ደግሞ ጥንካሬን ሰቶናል።

የወደድሽው ወይም ውስጥሽ የቀረው ፅሁፍ እና ታሪክ የትኛው ነው? ለምን?
የብዙዎቹንም ታሪክ ወድጄዋለው ለምን ቢባል ሁላችንንም የሚነካ ስለሆነ በተለይ እንደኛ ሀገር ባህሌ እምነቴ ከሚል ማህበረሰብ ወተው ፍቅር ፆታ እንደማይመርጥ አሳይተውናል በተጨማሪም ፍቅር ሕግም ስርዐትም አይገድበውም።
መፅሄቱ በሀገር ውስጥና በዳይስፓራ ያሉ LBTQ ሰዎችን በተለየ አተያይ እንድታይ አድርጎሻል? እንዴት?
በሀገር ውስጥ ያሉትን ሳላደንቅ አላልፍም ምክንያቱም ቅድም እንዳልኩሽ ብዙ ነገሮችን አልፈው ታሪካቸውን በድፍረት ለኛ ስላካፈሉን አሁን እኔ ከራሴ ጋር ብዙ ጊዜ ተጣልቻለው እራሴን አምኜ ለመቀበል በዋናነት ምክንያቴ ምለው ኘሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነኝ ሁል ጊዜ ለራሴ ምሰጠው ግምት ሀጥያተኛ እንደሆንኩ ነበር አስታውሳለሁ በዚህ ምክንያት ከቸርች የቀረሁባቸው ረዥም ቀናቶችን ባለማወቄ ና ባለመረዳቴ እንዲሁም በጣም ማፈቅራትን ልጅ አጥቻለሁ እናም በመፅሔቱም ላይ የሰፈሩት ሰዎች ህይወት አብዛኛው ይሄ ነው።
ወደ ዲያስፖራዎቹ ስመጣ ለነሱ ቀለል ይላል ብዬ አስባለው ማለትም እዛ ያለው ማህበረሰብ በእውቀትና በመረዳት እዚህ ካለው የቀደመ ስለሆነ።
ከመፅሄቱ አንድ የገረመሽ ወይም ያስደነቀሽ ነገር ምንድን ነው?
የገረመኝ ነገር ምንድነው ይህን መጽሔት አዘጋጅታችሁ ለኛ ተደራሽ ለማድረግ ሀሳቡ በራሱ እንዴት መጣላቸው የሚለው ያስደንቀኛል። ምክንያቱም ብዙዎች አለን ህጉንና ስርዓቱን ለመጠበቅ ብቻ ስንል ሳንፈልግ ወደሌላ መንገድ ምንሄድ ስለዚህ ይሄ መፅሔት እኛን ከማስደነቅ አልፎ እራሳችንን እንድናወጣ በጣም እየረዳን ነው።
ኩዊር አትዮጵያ ወደፊት በስራዎቻቸው እንዲያነሱ የምትፈልጊያቸው ርዕሶች ምንድን ናቸው? ወይም ስለዚህም ቢፃፍ የምትይው ካለ?
ከሰዎች ታሪክ ጋር እያያዛቹ ምታወጡት ነገር በጣም አሪፍና መቀጠል ያለበት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ለተደራሹ ይበልጡኑ ግልፅ በሆነ መልኩ ስለ LGBTQIA+ ግንዛቤ እንዲያገኝ ብታደርጉበት እላለሁ።
እወዳችኋለሁ በርቱ ቀጥሉበት 💛 Maki Alex