
ሁለት የኩዊር ኢትዮጵያ አንባብያችንን በዚህ ዙሪያ ታሪካቸውን እንዲያካፍሉን ጠይቀናቸው ነበር። እነሆ:-
ራሷን በቅርብ ግዜ ውስጥ እንደተቀበለች ሌዝቢያን ከባድ የአይን ፍቅር የነበረብኝ አሁን አብራኝ ካለችው ፍቅረኛዬ ነበር። እናም ለመጀመርያ ግዜ ሶሻል ሚድያ ላይ ሳያት ደስ ብላኝ ስለነበር የጓደኝነት ጥያቄ በመላክ ነበር እሷን መከታተል የጀመርኩት። ፖስቶቿ በስህተት አያመልጡኝም በእያንዳንዱ በምትለጥፈው ነገር ላይ ቢያስቀኝም ባያስቀኝም ሪአክት ከማድረግ አልመለስም ነበር። ለተከታታይ 6 ወራት አንድም ቀን አንድ ነጠላ መልዕክት ሳልፅፍላት እንዲሁ በሪአክት ብቻ ፍቅሬን ስገልፅላት ቆይቻለሁ … ምንም ነገር ባናወራም online መሆኗን ሳይ ሰላም ይሰማኝ ነበር አንዳንድ ሰሞን በደምብ አስታውሳለሁ ወደ ፌስቡክ የምገባው እሷን online መሆኗን ለማየት ነበር። ከተለምዶው በተለየ መልኩ ስትጠፋ በጣም እረበሽ ነበር ምን ሆና ነው እላለሁ ። በገጿ ላይ ከምትለጥፈውና በኮሜንት ከጓደኞቿ ጋ በምታወራው ነገር ብቻ ግማሽ በግማሽ የሚሆነውን የምትወደውን ነገር ለመረዳት ተችሎኛል ብል አላጋነንኩም። ለመጀመርያ ግዜ ፎቶዬ ላይ ❤️ ሪኣክት ያደረገችልኝ ቀን የፍቅር ጥያቄዬን የተቀበለች እስኪመስለኝ ድረስ ነበር ቀኔ አምሮልኝ የዋልኩት😂 ቀጥሎ ደሞ story ላይ ላስቀመጥኩት ፎቶ reply ስታረግልኝ ከደስታዬ ብዛት ለመመለስ ከግማሽ ሰአት በላይ ልቤ ላይ የሚሰማኝን የደስታና የድንጋጤ ድብልቅ ስሜት ማስታረቅ አቅቶኝ ቆይቼ ነበር የመለስኩላት። ይኸው ከዛች የአድናቆት የstory ላይ ወሬ የተጀመረ conversation ወደ ፍቅር ተቀይሮ ለ1አመት ያህል አብረን ነው ያለነው።
– ሃ
አንድ ሰፈር ብንሆንም የተለያየ ትምህርት ቤት ነበር ምንማረው እና የሚወዳት ልጅ ቅዳሜ ቅዳሜ ለማኝ ሳያራ በጠዋት ሰፈር እየመጣ እንደጦስ ዶሮ ሲንቀዋለል ውሎ ይመለሳል። ስንቴ 🗡 ግራ ቂጡ ላይ ሰክቼ ንቀለው ብዬ ማለት አሰኝቶኝ ነበር 🙄 የነበረኝ አማራጭ ለወንድ እያስመሰልኩ ግጥም እየፃፍኩ አነብላት ነበር ( “ደስ ሲል በማርያም” ስትለኝ አቤት ደስ ሲለኝ 😂) በጣም እወዳት ስለነበር ቦይፍሬንድ ይዛ እንኳን ውጭ ስታመሽ እኛ ቤት መጥታ ከኔጋ እንደነበረች እንድዋሽላት ስትጠይቀኝ ምንም ብናደድም ጥርሴን ነክሼ ሳላመነታ ነበር የምዋሽላት። ለሷ ሲሆን የማይመጣልኝ የውሸት አይነት አልነበረም። ክረምት ክረምት ወደ አያቶቼ ጋ ክፍለሀገር መሄድ የማልወደው እሷን ስለማላገኛት ብቻም ሳይሆን በ2ወር ውስጥ አዲስ ጓደኞች አፍርታ ስለምትጠብቀኝ ጭምር ነበር 😂
ዛሬ ላይ ስለኔ ከሚያውቁ ጥቂት የቅርብ ሰዎች መሐል አንደኛዋ ነች 🥰 እኔም እሷ ስታገባ ማዘጋጃ ቤት ከነበሩት ምስክሮቿ መሐል አንዷ ነኝ 😐
– ኤ
እናንተም የምታካፍሉን ካለ በ etqueerfamily@gmail.com ልትፅፉልን ትችላላችሁ።