ፖድካስት: “አዲስ አበባ የመጣሁት ሌዝቢያን በመሆኔ ነው”

የኢትዮ ኩዊር የቅርብ ጊዜ ፖድካስት በሶስት ቀናት ውስጥ ሊወጣ የታቀደ ሲሆን ከአዲስ አበባ ውጪ የሚኖሩ የLBTQ ማህበረሰብ የሚገጥማቸውን ፈተና አስመልክቶ አስደናቂ እና ጠቃሚ ውይይት ነበረን።

አዲስ አበባ ለLBTQ ማህበረሰብ ምቹ ቦታ አለው ብሎ ማሰብ ይከብዳል ነገር ግን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በክልል ከተማ ትኖር ከነበረችው ዮሃን ጋር ያደረግነው ውይይት ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ ክልል ከተሞች ላይ LBTQ መሆን ይበልጥ ከባድ እንደሆነ የመገንዘብን አስፈላጊነት አጉልቶ ያሳያል። ከዚህ በታች ከዮሃን ጋር ካደረግነው ውይይት የተቀነጨቦ ሃሳቦችን አካተናል። በሶስት ቀናት ውስጥ የሚለቀቀው   ፖድካስት https://soundcloud.com/ethioqueer  ላይ ሊደመጥ ይችላል።

“እራሴን አስራ አንደኛ ክፍል ላይ እራሴን ተቀበልኩኝ። ክፍለ ሃገር ላይ ብዙም ሰው የለም እና ብቸኝነት በጣም ነበር የሚሰማኝ። ቤተክርስቲያን ስሄድ በራሱ ሁሉም ሰው የሚያውቅብኝ ነበር የሚመስለኝ ገና ሲያዩኝ ስለኔ እያሰቡ ይሆን እንዴ ብዬ እጨናነቅ ነበር።”

“አዲስ አበባ እና ክልል ከተሞች ላይ ትልቅ ልዩነት አለው።  ክልል ከተሞች ላይ ሰው ኣታገኚም በተለይ እኔ የነበርኩበት ቦታ ሰው አለ ይባላል ግን እኔ እንደሚመስለኝ ሰው ካለ ሁሉ እዛ መኖር አይፈልግም ምክንያቱም ብዙ ኮኔክሽን የለም፣ ብዙም ልትገናኚም ስለማትችዪ ሰው ማንነቱን ፍልጋ እና ለመኖር ብሎ ክክልል ከተሞች ይውጣል። ብዙ ይኛ ኮሚዩኒቲ የሚገኘው በአዲስ አበባ ነው። አብዛኛው ሰው ወደ አዲስ አበባ የሚምጣ ይመስለኛል። አዲስ አበባ የመጣሁበት አንደኛ ምክንያቴ በማንነቴ ነው፣ ሌዝቢያን በመሆኔ ነው።” 

“ባልረፈደ ግዜ ነው ራሴን የተቀበልኩት ግን እዚህ [አዲስ አበባ]ቢሆን ግን ያንን ሁሉ ስቃይ አላሳልፍም ነበር። እዛ [የክልል ከተማ]እያለሁ ብቸኝነት በጣም ይሰማኝ ነበር እዚህ ቢሆን ግን የዛን ያህል አይሰማኝም ነበር ብዬ አሰባልሁ። ለጎደኛዬም መጨረሻ ላይ ያነገርኳት የመታፈን ስሜት ስለተሰማኝ ነው።“

Leave a Reply