ከእህቶቼ ልጆች ጋር በአንድ የአዲስ አበባ ካፌ ውስጥ እየተዝናናን ነው። የምግቡን መምጣት እየጠበቅን በድንገት አንደኛዋ የእህቴ ልጅ ወንድ እንደሆንኩ ነገረችኝ። ብዙ የእህትና ወንድም ልጆች ስላሉኝ እነዚህን ጥያቄዎች ለምጃቸዋለሁ። “ሴት ነኝ” አልኳት። ፀጉሬ አጭር ስለሆነና “የወንድ ሸሚዝ” ስለለበስኩ ወንድ ልጅ እንደሆንኩ አጥብቃ ተከራከረችኝ። ፀጉሯን ብትቆርጠው ወንድ እንደምትሆን ጠየዃት። የሚያምረውን ሹሩባዋን እየነካካች ፀጉርሽ ቢቆረጥስ ያልኩት ሐሳብ በጣም አስደንግጧታል ። ከዚያም ጠረጴዛችን አጠገብ ተቀምጣ የነበረችን አንዲት ሴት ጠቁማ አንድ ሰው እንደ ሴት ለመታየት የዓይን ኩል ማድረግ አለበት ብላ አስረዳችኝ። እየተመላለስን እና እንደወንድ እየጠራችኝ እንዴት ሴት መባል እንደማልችል የተለያዩ ምክንያቶችን ዘረዘረችልኝ። “እሷ” የሚለውን መለያ ከመጠቀሟ በፊት እንደሴት እናእንደወንድ እየቀያየረች መጥራቷ ስለማይቀር ተውኩት።
በአዲስ አበባ እንደምትኖር በተለምዶ “ወንዳወንድ” ሌዝቢያን ፆታ ከስርዐተ ፆታ ጋር እኩል አለመሆኑን በሆነ መንገድ መረዳት እንችል ይሆን ብዬ ሁሌም አስባለሁ።
ይሄ ውይይት ግን ከሌላኛው የእህቴ ልጅ ጋር በእሷ እድሜ እያለ የነበረኝን ውይይት አስታወሰኝ። አንዳንድ ነገሮችን ስለብስ እንዴት ሴት መሆን እንዳለብኝ፣ ነገር ግን አንዳንድ ነገሮችን ስለምለብስ እንዴት ወንድ መሆን እንደሚገባኝ ያብራራልኝ ነበር። ከብዙ ህፃናት ልጆች ጋር እነዚህን ውይይቶች አድርጌያለሁ ወላጆች እንደ የእህቴ ልጅ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን በመጠየቃቸው ወይም እንደወንድ በመርዳታቸው ወላጆች ልጆቻቸውን ይገሥጻሉ።
በእነዚህ ስርዐተ ፆታ ጉዳዮች ዙሪያ ከአዋቂዎች ጋር መነጋገር ብዙ ጊዜ አድካሚ ቢሆንም ከልጆች ጋር መነጋገር መንፈስን የሚያድስ ሆኖ አገኘዋለሁ ። ጥያቄዎቹ በዜሮ ፍረጃ እና በዙሪያቸው ከሚመለከቱት ጋር ፆታዬን ማስማማት ከመፈለግ የሚመጡ ናቸው። እንደ አንድ ኅብረተሰብ በስርዐተ ፆታ ማንነት እና በስርዐተ ፆታ መግለጫ መካከል ስላለው ግንኙነት ጥብቅ አመለካከት አለን እናም ልጆቻችን ከኅብረተሰቡ በሚሰሙት እና በአካባቢያቸው በሚሰሙት ላይ ተመሥርተው ይህን አመለካከት ቀስ በቀስ በውስጣቸው ያሳድራሉ።
ከልጆች ጋር በምወያይበት ጊዜ እንደ ማህበረሰብ ለእነዚህ ጥያቄዎች ትርጉም ባለውና ገንቢ በሆነ መንገድ መልስ መስጠት ምን ማለት ሊሆን እንደሚችል ሁልጊዜ አስባለሁ ። ይልቁንም እነዚህን ጥያቄዎች ከወንድ/ሴት ሁለትዮሽ ስርዐተ ፆታ ነፃ የሆነ ዓለም በማቅረብ እንዲጠይቋቸው ማድረግ ብንችል ምን ይመስል ነበር። በአዲስ አበባ እንደምትኖር በተለምዶ “ወንዳወንድ” ሌዝቢያን ፆታ ከስርዐተ ፆታ ጋር እኩል አለመሆኑን በሆነ መንገድ መረዳት እንችል ይሆን ብዬ ሁሌም አስባለሁ።