ስለፍናፍንት ግንዛቤ መፍጠሪያ ቀን

ስለፍናፍንት ግንዛቤ መፍጠሪያ ቀን በየዓመቱ ጥቅምት 16 ቀን በዓለም ዙሪያ የሚከበረው ፍናፍንት የሆኑ ሰዎች የገጠሟቸውን የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ለማጉላት ነው።

ፍናፍንት ማለት ምን ማለት ነው?

ፍናፍንት ሰዎች ፆታ ገፀ ባህሪያትን (የመራቢያ አካላት፣ ክሮሞዞሞች ፣ ሆርሞኖች) ይዘው የሚወለዱ እና በሴት እና ወንድ ጾታዎች የማይገለፁ ናቸው። 

ፍናፍንት የተለያዩ የተፈጥሮ አካላዊ ልዩነቶችን ለማመልከት የሚሠራበት ጃንጥላ ነው። አንዳንድ ጊዜ በውልደት ጊዜ የሚታይ ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ እስከ ጉርምስና ጊዜ ድረስ በግልጽ አይታይም። አንዳንድ ክሮሞዞማዊ ፍናፍንት በአካል ላይታዩ ይችላሉ።

ባለሙያዎች እንደሚሉት ከ0.05% እስከ 1.7% የሚሆነው ህዝብ የሚወለደው ፍናፍንት ነው – የላይኛው ግምት ከቀይ ፀጉር ያላቸው ሰዎች ቁጥር ጋር ተመሳሳይ ነው። 

ፍናፍንት መሆን ከባዮሎጂያዊ የፆታ ባህሪያት ጋር ይዛመዳል  እንጂ ከአንድ ሰው ወሲባዊ ማንነት ወይም የስርዐተ ፆታ ማንነት የተለየ ነው። አንድ ፍናፍንት የሆነ ሰው ተቀራኒ ፆታ አፍቃሪ ፣  ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ፣ ሁለት ስርዐተ ፆታ አፍቃሪ ፣ አሴክሹኣል  ፣   ሴት  ፣ ወንድ  ወይም ከሁለትዮሽ ስርዐተ ፆታ የተለየ ሊሆኑ ይችላሉ። 

ፍናፍንት የሆኑ ህፃናትና አዋቂዎች ማንነታቸው የተለያየ ሆኖ ስለሚታይ ይገለላሉ፤ የተለያዩ የሰብዐዊ መብት ጥሰትም ይደርስባቸዋል። የጤና እና የአካል ብቃት መብት ጥሰት ፣ ከስቃይና ከግፍ ነፃ አለመሆን፣ እንዲሁም እኩልነትና መድሎ አለመኖር ከጥቃቶቹ ውስጥ ይገኙበታል።

(ምንጭ: https://www.unfe.org/wp-content/uploads/2018/10/Intersex-English.pdf)

Leave a Reply