የዚህ ወር ፖድካስታችን በአንድ የክልል ከተማ የምትኖረውን ዮርዳኖስን ይዛላችሁ መጥታለች። ዮርዳኖስ በተለምዶ “ወንዳወንድ” የምትባል ሌዝቢያን ናት፥ ስርዐተ ፆታን ለእርሷ ትርጉም በሚሰጥ መልኩ እንደገና በመተርጎም ፥ የስርዐተ ፆታ ማንነቶችንን ወይም የስርዐተ ፆታ አገላለጾችን ዋጋ በማይሰጥ ሀገር ውስጥ መኖር፥ በሰፊው ማህበረሰብ እና በኩዊር ማህበረሰብ ውስጥ እንዴት መንቀሳቀስ እንዳለባት ትልቅ ትምህርት አስተምሯታል።
ካነሳናቸው ሃሳቦች መሃል ጥቂቱን ቀንጨብ አድርገን አስቀምጠነዋል፤ ሕዳር 1፥ 2014 ላይ ሲለቀቅ እንደምትሰሙት ተስፋ እናደርጋለን።
“[ተመሳሳይ ፆታን ማፍቀር] ሰዎች ኖርማል የሚሉት ነገር እንዳልሆነ አውቃለሁ። ስለዚህ ኤለመንተሪ እያለሁ ይሄ ነገር ልክ አለመሆኑን ዲፌንድ የማደርግበት መንገድ ያስፈልግኛል። እና ለዚህ መፍትሔ ያስብኩት እንደወንድ ብሆንስ ብዬ ነበር። … ነገሩ እየቀለለኝ መጣ።”
“’ወንዳወንድ’ መሆን በጣም ጉዳቶችም አሉት። ለምሳሌ ማንም መንገደኛ ሊሆን ይችላል። ማንም መንገደኛ ያንን ሰው ትርፍ ቃል ለመናገር የመጋበዝ የመቅለል አይነት ነገር እንደውም ከመነጋገር ያለፈ violence ድረስ የመድረስ ነገር፣ በቀላሉ ለመገመት … በጣም አጋልጦ ይሰጥሻል።”
“እኛ [ኩዊር] ማህበረሰብም ውስጥም ያሉ ከበፊት ከወንዶች የተማርናቸው ነገሮች “ወንዳወንድ“ሴቶች ላይ የመፈለግ ነገር [አለ]። ለምሳሌ በቀላል ነገር ብነግርሽ ነገሮችን የመስራት ነገር ሊሆን ይችላል ምናልባት ብዙ “ወንዳወንድ“ሴቶች ሊሰሩት ይችላሉ፤ እኔም ደስ ይለኛል መስራት ግን “ወንዳወንድ“ ስለሆንሽ ብቻ ነገሮችን መስራት አለብሽ፤ ይሄን ነገር ወንድ ልጅ የሚሰራውን ነገር በተለምዶ መስራት አለብሽ። ከሱ አልፎ በባህሪ እራስሽን አጋልጠሽ ላለማሳየት ኢሞሽናል ላለመሆን ወንድ ልጅ አክት እንደሚያደርገው አድርጊ የምትባይበት ሁኔታ አለ። ይሄ ነገር ከውጪ ክማይረዳሽ ሰው ብቻ ሳይሆን ውስጥ የራሰሽ ከምትያቸው ከነገርሻቸው ኮሚኒቲ እና ፋሚሊ ካልሻቸው ሰዎችም የሚመጣብሽ ነገር ነው።”
Like this:
Like Loading...
Related
Published by Queer Ethiopia
"Queer family" is an alternative space created by a group of queer Ethiopian women. It is designed to be a space for a diverse group of Ethiopian queer women whose sexual and gender identifications vary. It includes cis and trans women who may be lesbian, bisexual or asexual. This is a space where the experiences of queer people takes center stage. We hope to include personal experiences from our daily lives as queer people, various stories, interviews, original artwork and poetry. We hope it will also serve as a place where Ethiopians in Ethiopia and Ethiopians in the diaspora come as themselves to explore and create an online community.
If you would like to send us something, please send us an email via etqueerfamily@gmail.com
«ኩዊር ኢትዮጵያ» የተለያዩ ፆታዊና ወሲባዊ ዝንባሌ ላላቸው ኢትዮጵያዊ ኩዊር ሴቶች እንዲሆን ታስቦ በኩዊር ሴቶች የተመሠረተ አማራጭ ምኅዳር ነው። ይኽውም ሌዝቢያን፣ ባይሴክሽዋል ወይም ኤሴክሽዋል የሆኑ ሴቶችንንና ትራንስ ሴቶችን ያካትታል። ይህ ምኅዳር የኩዊር ማኅበረሰብ ታሪክ እና የሕይወት ልምድ ትልቅ ሥፍራ የሚይዝበት ነው። እንደ’ኩዊር ማኅበረሰብ የዕለት ተዕለት ሕይወታችንን ገጠመኞች፤ የተለያዩ ሰዎችን የግል ታሪኮች፤ ቃለ-
መጠይቆች እንዲሁም ሥነ-ጥበባትን እንደምናካትት ተስፋ እናደርጋለን። ከነዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ እና በዳያስፖራ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ራሳቸውን ሆነው
የሚመጡበት የበይነ-መረብ ማኅበረሰብ መድረክ ሆኖ እንዲያገለግል ማስቻል ፍላጎታችን ብቻ ሣይሆን ጥረታችንም ጭምር ነው።
etqueerfamily@gmail.com
View all posts by Queer Ethiopia