አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ: የቀድሞ ፍቅረኛዬ እና እኔ

ከስር ያቀረብንላችሁ  <<አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ>> ከተሰኘ ተከታታይ ፅሁፍ የመጀመሪያው  ሲሆን በዚሁ መልክ ከኩዊር ማህበረሰብ በፍቃድ ከሚላኩልን የግል መልእክቶች፣ የግል ማስታወሻዎች እንዲሁም ግለ ታሪኮች ላይ እየቀነጫጨብን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል። እነዚህ የፅሁፍ ቅንጭብጫቢዎች ልክ ህይወታችን አስልተን እንደማንኖራት ሁሉ የቆምንበትን የህይወታችንን ትክክለኛ ገፅ  የሚያመላክቱ  አንዳንዴ መግቢያ፣ ሌላ ግዜ ተሟልተው ያልተፃፉ እንዲሁም የተዘበራረቁ ፅሁፎች ናቸው። 


ይሄን ፅሁፍ ከምታነቡ ማንኛችሁም የኩዊር ቤተሰቦች የእናንተንም ማስታወሻ እንደምንቀበል በደስታ እያሳወቅን በetqueerfamily@gmail.com ኢሜይል እንድትልኩልን እንጠይቃለን። .

እኔና እና የቀድሞ ፍቅረኛዬ የነበረን የፍቅር ግንኙት ባስነሳው ሹኩሹክታ ምክንያት ፍቅረኛዬ ከቤተሰቦቿ ጋር ጥሩ ሁኔታ ውስጥ አልነበረችም። በዛም ከቤተሰቦቿ ጋር መልካም ግንኙነትን በድጋሚ በመገንባት ውስጥ የእኔ በእሷ ህይወት ውስጥ መኖር አጠያያቂ እየሆነ መጣ። ቤተሰቦቿ በእኔና በእሷ መሀል ያለው የፍቅር ግንኙነት እግዚአብሄርን በቁጣ እንደሚያስነሳ በተደጋጋሚ መንገራቸው በህይወቷ እንደ ሰው ልጅ ያላትን ዋጋ እንድትጠይቅ አደረጋት። አጣብቂኝ ነበር። በአጣብቂኝዋ ውስጥ መምረጥ ነበረባት።   ምርጫዎቿም፤ የመጣችበት ቤተሰብ እና በእነሱ አልያም በእኔ አማካኝነት የምታገኘው የአምላክ ትርጉም የሚሰጣት የአእምሮ እረፍት ነበር።   እኔን ለመምረጥ ትግል ነበራት። እኔ ደግሞ ትግል ልሆንባት አልወደድኩም፤ ማረፊያ ቤቷ እና መጠለያዋ እንጂ። አሁን እሷ ምን እንደሚሰማት አላውቅም ፤ እኔ የሚሰማኝ ጓደኛ ለመሆን ከባድ እና ገና እንደሆነ ነው። 
መጨረሻ ያወራን ግዜ ፍቅሯን ከህይወቷ እንድትገፋ ባደረጓት ቤተሰቦቿ፣ እንዲሁም በአምላኳ ብስጭት እና ከባድ ህመም ውስጥ ነበረች።  የከፈለችው መስዋዕት ቤተሰቦቿ እና አምላክ በእውነት ይገባቸዋል? የእሷ ደስታ ማጣት እነሱን ያስደስታቸዋል? በእኔ ህይወቷ ውስጥ አለመኖር ምክንያት የተፈጠረው ባዶነት የወሰነችውን ውሳኔ ይስተካከለዋል? የአምላክን ፈተና አልፋ ይሆን? እሷ ብቻ ናት የምታውቀው። 

Leave a Reply