ፈቃድ መጠየቅ: ስርዐተ ፆታ ጥቃት ይቁም 

በየአመቱ ከህዳር 16 – ታህሳስ 1 ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ  ”ስርዐተ ፆታ ጥቃት ይቁም” በሚል የተለያዩ ዘመቻዎች እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ይዘጋጃሉ። ነገር ግን ሃገራችን ላይ ያለው ዘመቻ እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም በፍፁም  ኩዊር ማህበረሰብን አካታች አይደለም። 

ከዚህ ጋር ተያይዞ ዛሬ ላይ ማንሳት የፈለኩት የማህበረዊ ሚድያ አጠቃቀማችን ላይ ነው።  በምንኖርበት ሃገር እንደተቃራኒ ፃታ አፍቃሪያን በቀላሉ የፍቅር ጋደኝነትን መመስረት ቀላል አይደለም፤ በዚህም ምክንያት ዋነኛው የመገናኛ ቦታ ማህበራዊ ሚድያው ነው። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ፈቃድ መጠየቅ ምን ይመስላል?

በፌስቡክ ጓደኛ ስለሆንን ብቻ በማንኛውም ሰዓት መልዕክት መላክ እንችላለን ማለት አይደለም። ለመፃፍ የፈለግነው ሰው ለማውራት ፈቃደኛ ነው? ሰላምታ ሰጥተን ምላሽ ሳይኖር ሲቀር ፍላጎት የላቸውም ወይም በራሳቸው ጊዜ ይፅፋሉ እንላለን ወይስ እንወተውታለን?

 የፌስቡክ መልዕክት ስንልክ ለማውራት ፈቃደኝነታቸውን መጠየቅ

ምንም እንኳን አንድን ሰው ለመተዋወቅ ጉጉት ቢኖረንም የሰዎችን ፈቃደኝነት መጠየቅ የመጀመሪያው ስራ ነው ብዬ አምናለሁ። በፌስቡክ ጓደኛ ስለሆንን ብቻ በማንኛውም ሰዓት መልዕክት መላክ እንችላለን ማለት አይደለም። ለመፃፍ የፈለግነው ሰው ለማውራት ፈቃደኛ ነው? ሰላምታ ሰጥተን ምላሽ ሳይኖር ሲቀር ፍላጎት የላቸውም ወይም በራሳቸው ጊዜ ይፅፋሉ እንላለን ወይስ እንወተውታለን? አንድ ጓደኛዬ በአንድ ወቅት ከውትወታ ባለፈ “ማንነትሽን አውቃለሁ ካላነገርሽኝ አጋልጥሻለሁ” የሚል ዛቻ እና ማስፈራሪያ ደርሶባት እንደሚያውቅ አጫውታኛለች። የሴቶች ጥቃት ሲነሳ አብዛኛውን ጊዜ አካላዊ ጥቃት እና መደፈር ላይ ቢያተኩርም እነዚህ ትንሽ የሚመስሉ ነገር ግን ትልቅ ዋጋ ሊያስከፍሉ የሚችሉትን ጥቃቶች በኩዊር ማህበረሰባችን መካከል መወያየት እንዳለብን ይሰማኛል።  የ”አልፈልግም”ን ምላሽ በትህትና መቀበል አዋቂነት ነው። ፍላጎቶቻችን እንዲጠበቁልን እንደምንፈልገው ሁሉ የሌሎችንም ፍላጎት መጠበቅ ይኖርብናል። 

ሌላው በተደጋጋሚ ከሚላክ ሰላምታ ውጪ ሳይጠየቁ የሚላኩ ፎቶዎች ናቸው። እነዚህ ፎቶዎች የግል ፎቶ ሊሆኑ ይችላሉ አንዳንዴም ደግሞ ፖርኖግራፊ። (cyberflashing) ለሰዎች ያለፈቃዳቸው ምንም አይነት ፎቶግራፎችን መላቅ ፎቶን ያማከለ ጥቃት ላይ ይመደባል። አብዛኛውን ጊዜ ኩዊር ሴቶች ከተቃራኒ ፆታ አፍቃሪ ወንዶች እነዚህን ፎቶዎች በመልዕክታቸው ያገኛሉ፤  ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ሴቶችም ሌላ ኩዊር ሴቶች ላይ ይህንኑ  ይህንኑ ጥቃት ይፈፅማሉ። ፈቃድ ሳይጠየቅ ለምን መላክ አስፈለገ? መልዕክቱ ምንድን ነው? ያለችንን ትንሽዬ የኩዊር ኦንላይን መንደር እንዴት ተከባብረን መኖር እንችላለን? 

የህግ ከለላ ባይኖረንም አንዳችን ላንዳችን ከለላ መሆን ብንችልስ?!

ይህቺ አጭር ፅሁፍ ከቅርብ ጓደኞቻችን ፣ ከፍቅር አጋሮቻችን እንዲሁም ከፌስቡክ ጓደኞቻችን ጋር የመወያያ ርዕስ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።

Leave a Reply