ፖድካስት፥ ባይሴክሽዋሊቲ በኢትዮጵያ LGBTQ+ ማህበረሰብ ውስጥ

የዚህ ወር የኢትዮ ኩዊር ፖድካስት እንግዳችን ባይሴክሽዋል የሆነችውና አዲስ አበባን የምትኖረው ሄለን ናት። ከሄለን ጋር ባይሴክሽዋል ሰዎች በLGBTQ+ ማህበረሰብ ውስጥ ስላላቸው የለት ተለት ኑሮ ላይ የነበረን ቆይጣ በጣም አስፈላጊ ነበር ምክንያቱም በባይሴክሽዋል ጠልነት ምክንያት የሚደርስባቸውን ተግዳሮቶች ጠቁሞናል። ሄለን የባይሴክሽዋል ማንነት “ትክክለኛ” ወሲባዊ ዝንባሌ እንዳልሆነ ተደርጎ ስለሚታይባቸው የተለያዩ መንገዶች ትናገራለች። ሁላችንንም እንደየማንነታችን የሚቀበል እና  ያ ቦታ ሁላችንም እውነተኛ ማንነታችንን ወደ ፊት እንድናመጣ የሚያስችለንን የLGBTQ+ ማኅበረሰብ መፍጠር አስፈላጊነ እንደሆነ ጎላ አድርጋ ገልጻለች።

ከታች ያለው ከፖድካስት ውይይቱ የተቀነጨበ ነው፥

“ባይሴክሽዋሊቲን ብዙ ሰው የሚወስደው እንደ መደበሪያ እና እንደ ጊዜ ማቃጣያ ነው።”  

“ሰው በሚለን ሳይሆን እኛ መስማት የምንፈልገውን እየሰማን እንሄዳለን። …  አይ ልትሆን አትችልም፣ አይ መስሏት ነው፣ አይ ጠጥታ ነው።… በብዙ ምክንያት ግን ብቻ “አይደለችም” ይቀድማል። ብላለች ስለዚህ ናት ከሚለው ብላለች ግን መስሏት ነው ይቀላል። ትንሽ እብደትም ይመስለኛል። …  እንደ ፌም ሴት ያ ነገር በጣም በጣም በብዙ መንገድ ሰው ስታናጋሪም ይሁን፣ ሰው እያናገረችም ይሁን በግሩፕ ሴቲንግ ላይም [ማህበረሰቡም] ውስጥ ሆኜ አይቼዋለሁኝ። ተባርሬም አውቃልሁ ማለት ውጪ ተብዬ ሳይሆን፥ ፎጋሪ አይነት ነገር ተሰጥቶኝ ይሄ ቦታማ አይሆነኝም በቃ ልውጣ፣ የሰው ቦታ [እየረበሽኩኝ] ነው አይነት ስሜት እስኪስማኝ ድረስ … [ከማህበረሰቡም] ቦታዎች ለቅቄ ውጥቼ አውቃለሁ። ኮሚኒቲው ውስጥ ባያስ አለ።”

“የትም አገር ላይ ብትሄጂ የትም ቦታ ላይ ብትሆኚ የበለጠ የተጨቆኑ ሰዎች አሉ አይደል፧ እዛ ቦታ ላይ እስከኖርን ድረስ ቢያንስ እርስ በራሳችን መተያየት መቻል አለብን።  …  አንድ ሰው በራሱ [ማንነት] እኔ ነኝ ባለው መኖር መቻል እንዳለበት ነው፥ እኔም ደሞ መኖር መቻል እንዳለብኝ ነው።”

Leave a Reply