ኢትዮኩዊር ፖድካስት፥ የአንደኛውን ክፍለ ጊዜ ክለሳ

የመጀመሪያውን ፖድካስት ያወጣነው ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት ነበር። የመጀመሪያው ፖድካስት አስደሳች ውይይት በኢትዮጵያ ከሚገኙ ሌዝቢያን ፍቅረኛሞች ጋር ነበር ያደረግነው፤ እኔና ባልደረባዬ በነበረው ምላሽ በጣም ተደንቀን እንደነበር አስታውሳለሁ።

አንድ ጓደኛዬ ይህን ካዳመጠችው በኋላ እንዲህ ብላ ፣ “ገና እየሰማሁት ነው፣ እና ምንኛ አስደናቂ ሥራ ነው! በጣም አሪፍ – የኢትዮጵያውያን የኩዊር ተሞክሮ ሰብዐዊ ያደርገዋል። ሶስታችሁም አስደስታችሁኛል!” አለችኝ በመቀጠል “ምን አለች በይ- ይህ ቃለ መጠይቅ በኢትዮጵያ የኩዊር ታሪክ ውስጥ ትልቅ ትውስታ ይሆናል” አለችኝ። 

ያንን መስማት አስደሳች ነበር። ሌላ ጓደኛዬም እንዲህ አለች፣ “ይህን ውይይት እዚህ ከሚኖሩ ኩዊር ሰዎች በአማርኛ መስማት ምን ያህል ማረጋገጫ እንደነበር ልነግርሽ አልችልም።” 

ተፅዕኖ ይኖረናል ብለን ተስፋ አድርገን ነበር፣ ነገር ግን ብዙ ሰዎች ከውይይቱ ጋር የተዛመዱበት እና በሌሎች የLBTQ ማህበረሰብ ውስጥ “እንደተሰሙ” እና “እንደታዩ” የተሰማቸውን መንገድ ለማየት ዝግጁ አልነበርንም።

ወደ መጨረሻው ክፍል እንደመድረሳችን ብዙ የምንለው አለን። ባለፈው ዓመት ያደረግናቸው የፖድካስት ቃለ ምልልሶች  ላይ ያደረግነውን ውይይት እስክትሰሙት ቸኩለናል።  በሚቀጥለው ሳምንት ልንለቅ ባቀደው ፖድካስት ላይ እኛ – መስራቾች – እራሳችንን እና ኢትዮኩዊር ፖድካስትን የምታዘጋጀውን ኩዊር ኢትዮጵያን እናስተዋውቃለን።

በተጨማሪም ኢትዮኩዊር ፖድካስትን ጠለቅ አድርገን  እናስተዋውቃችኋለን እናም ይህንን የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ የመጨረሻ ውይይት እንደምታዳምጡት ተስፋ እናደርጋለን።

Leave a Reply