ኢትዮኩዊር ፖድካስት፥ ምስጋና

የኢትዮጵያ ፖድካስት የመጀመሪያውን ክፍለ ጊዜ ስናጠናቅቅ፣ የተሳተፉትን ሁሉ ማመስገን እንፈልጋለን። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ጠልነት ጋር ተያይዞ እንዳለ ሆኖ ማንነትን በመግለጥ ሊመጣ የሚችል መጋለጥ አንዱ አደጋ ቢሆንም ፥  እንግዶቻችን ላሳዩን እምነት በጣም ልናመሰግናቸው እንወዳለን ። እኛ ራሳችን ኩዊር እንደመሆናችን መጠን ቃለ መጠይቅ እንድናደርግላቸውና ውይይቱን ቀድተን ለአድማጮች እንድናደርስ በመፍቀዳቸው ምን ያህል አደጋ እንደወሰዱ እናውቃለን።

ማንነትን ከመግለጥ እስከ “የወንዳወንድ” ሴት ተግዳሮት እና በኢትዮጵያ ያሉ ሰዎች በኩዊር ማህበረሰብ የሚያጋጥማቸው የባይሴክሽዋል ጠልነት በጣም ጠቃሚ ውይይቶችን አድርገናል። ማህበረሰብን ለመገንባት የሚደረገው ማንኛውም ጥረት ሁላችንም አንድ ላይ ተሰባስበን የበኩላችንን እንድንወጣ ይጠይቃል። ኢትዮኩዊር ፖድካስት (እና አዘጋጅ ኩየር ኢትዮጵያ) እውን የሆነው በLBTQ ማህበረሰብ ተሳትፎ ብቻ ነው።

ኢትዮኩዊር ፖድካስት እንደ አንድ ዓይነት ስብስብ እና  እንደ ማህበረሰብ ደግሞ የናንተ ነው። ይህን ስራ መስራት የቻልነው በእንግድነትና በአድማጭነት በመሳተፍ ጥረታችንን በልግስና ስለደገፋችሁ ነው።  ለዚህም እጅግ አመስጋኞች ነን፤ ወደ ሁለተኛ ክፍለ ጊዜ ስንሻገርም ድጋፋችሁ አደማይለየን ተስፋ እናደርጋለን። 

ለዚህ ክፍል የመጨረሻ ውይይታችን ኢትዮ ኩዊር ለእነርሱ ምን ትርጉም እንዳለው፣ እነማን እንደሆኑ፣ ከመጀመር በስተጀርባ ስላለው ምክንያት እና ለመጪው ያላቸውን እቅድ በመስራቾቹ መካከል የተደረገ ውይይት ነው።

Leave a Reply