ከፍቅረኛሞች ቀን ባሻገር

የፍቅረኛሞች ቀንም የአበባም አድናቂ አይደለሁም:: ምንም እንኳን የፍቅረኛሞች ቀን ካፒታሊስት እና ተቃራኒ ፃታ አፍቃሪነትን ብቻ ልክነትን የሚስል ባህል ነው ብዬ ብከራከርም፥ ጓደኛዬ ለፍቅረኛዋ አበባ እንዳደርስላት ጠየቀችኝ:: 

በተላላኪዎች መላክ አልቻለችም ምክንያቱም ሴት ለሴት ቀይ አበባ መላክ አዲስ አበባ ላይ የቀስተ ደመና ባንዲራ እንደማውለብለብ ነው::

ምንም እንኳን ጓደኛዬ በገዛችልኝ ምሳ ብደሰትም፤ እንዲህ አይነቱን ፍቅር ለመገላለፅ ድብብቆሹ እና ፍርሃቱ አሳዝኖኛል:: ይሄ ሁኔታ ለኩዊር ሰዎች  ፍቅር በብዙ መንገዶች በህይወታችን እንዳለ እንዳስታውስ አድርጎኛል:: ከዚህ በታች ያሉት አባባሎች ፍቅር እንደሚፀና በኩዊር ሰዎች እና ደጋፊዎች የተፃፉ ጥሩ ማስታወሻዎች ናቸው::

 

“ፍቅር ፆታ የለውም፣ ርህራሄ ሃይማኖት የለውም ፤ ባህሪይ ዘር የለውም::” – አብሂጃት ናስካር

“ፍቅር በፍፁም በፍርሃት መኖር ማለት የለበትም::” – ዳሻኔ  ስትሮክስ 

“ሌዝቢያን መሆን ማለት ያልተለመደን መውደድ እድል ማለት ነው፤ በዚህም ግድ የለኝም:: ፍቅር ነው የሚለውን እውነታ ስለተቀበልኩ በምመራው ህይወት ምክንያት አልናደድም፤ አላለቅስም።” – ጄና አን

“የትኛውም መንግስት ዜጎቹ መቼ እና ማንን መውደድ እንዳለባቸው የመናገር መብት የለውም።” – ሪታ ሜ ብራውን

“ለኔ ሴት መውደድ ቦታ ያልነበረው አለም መኖር የምፈልግበት ወይም የምታገልበት አለም አልነበረም::” – ኦድሬ ሎርድ

“የምታፈሪው ስርዓተ ፆታን ሳይሆን ሰውን ነው::” – ሳንድራ አልቫሬንጋ

“መጨረሻውን ቁረጥ:: ፅሁፉን አሻሽል:: የህልሟ ወንድ ሴት ነች::” – ጁሊ አን ፒተርስ 

“ለኤለን ያለኝ ስሜት ሌዝቢያን ሆኖ የመውጣትን ፍርሃት አሸንፏል። ከእሷ ጋር መሆን ነበረብኝ፣ እና በኋላ ላይ ሌሎች ነገሮችን እንደማስተናግድ አሰብኩ።” – ፖርሽያ ደ ሮሲ

“እኛ ሌሎች ሰዎች እንደሚሉን አይደለንም። እኛ እራሳችንን መሆን  እንደምናውቀው ነን  እና እኛ የምንወደው ነን:: ይህ ደግሞ ምንም ችግር የለውም::  ” – ላቬርኒ ኮክስ

Leave a Reply