አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ: የሁለት ኩዊር ሴቶች አጭር ትውውቅ በአዲስ አበባ

ከስር ያቀረብንላችሁ  <<አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ>> ከኩዊር ማህበረሰብ በፍቃድ ከሚላኩልን የግል መልእክቶች፣ የግል ማስታወሻዎች እንዲሁም ግለ ታሪኮች ላይ እየቀነጫጨብን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል። እነዚህ የፅሁፍ ቅንጭብጫቢዎች ልክ ህይወታችን አስልተን እንደማንኖራት ሁሉ የቆምንበትን የህይወታችንን ትክክለኛ ገፅ  የሚያመላክቱ  አንዳንዴ መግቢያ፣ ሌላ ግዜ ተሟልተው ያልተፃፉ እንዲሁም የተዘበራረቁ ፅሁፎች ናቸው። 


ይሄን ፅሁፍ ከምታነቡ ማንኛችሁም የኩዊር ቤተሰቦች የእናንተንም ማስታወሻ እንደምንቀበል በደስታ እያሳወቅን በetqueerfamily@gmail.com ኢሜይል እንድትልኩልን እንጠይቃለን። .

መወከል እና በግልጥ መታየት ለራሳችንና ለደህንነታችን ምን ያህል ወሳኝ ነገር እንደሆነ መዘንጋት ቀላል ነው ። ከዚህ በታች በአዲስ አበባ በተገናኙ በተለምዶ  “ወንዳወንድ” ሴቶች መካከል የተደረገ አጭር የኢሜይል ልውውጥ ነው። አንደኛዋ የምትኖረው አዲስ አበባ ውስጥ ሲሆን ሌላኛዋ ደግሞ በምዕራብ አለም ናት። እነዚህ የኢሜይል ግንኙነቶች በጣም አጭር ቢሆኑም ሁለቱም የተሰማቸውን የነፃነት ስሜት እንድናይ ያስችለናል። በተጨማሪም አስተማማኝ በሆነ ስፍራ ከሌሎች ጋር ለመገናኘት ቦታ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ያስታውሰናል ።

ሃይ ላ 
ስለኩዊርነት ለመጨረሻ ጊዜ ብዙ ያወራሁበት ጊዜ ትዝ አይለኝም። “የተለመደ” ስሜት ስለሰጠሽኝ አመሰግናለሁ። … ከተማዬ ከሌላ ኩዊር ሴት ጋር ስዘዋወርባት በጣም አስተማማኝ እንደሆነች ተሰማኝ።

መልካም መንገድ 

ሰላም ፈ
ይህ ኢሜል በሰላም ያገኝሻል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።  እኔም በዚያን ጊዜ ካንቺ ጋር ስዘዋወር የነበረው ደህንነት መቸም ተሰምቶኝ አያውቅም።  በሌላ ሰው ላይ በተለይ ደግሞ ብዙም የመታየት እድል በሌለበት ቦታ ራስን ማየቱ ትልቅ ተሞክሮ ነው ።  ለዚህ አመሰግንሻለሁ።  አብረን ያሳለፍነው ጊዜ ነፍሴን አስደስቶታል። ይህ እንዲሆን ስላመንሽኝ  አመሰግናለሁ።
 

መልካም፥

Leave a Reply