ሥቃይን ማቅለል

ስለ ጦርነት እና በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች የአፍሪካ አገሮች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የውስጥ ተፈናቃዮች ጉዳይ ላይ ዝም ብለን በዩክሬን ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ መፃፍ እንግዳ ነገር መሆኑን እናውቃለን። ይህ በከፊል ወደ ራሳችን ተገቢ ያልሆነ ትኩረት ላለመስጠት እና በዚህም በኢትዮጵያ ያሉ የLBTQ ማህበረሰብን ማገልገሉን ለመቀጠል የተሰላ ውሳኔ ነው። 

በሰዎች ላይ የሚደርሰው ሥቃይ ምንጊዜም አሳሳቢ ጉዳይ ነው ። የጥቁር ስደተኞች ከዩክሬን ጦርነት ሲሸሹ እያጋጠማቸው ያለው ዘረኝነት እንዲሁም በዩክሬን ያሉ LGBTQ+ ማህበረሰብ በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ፣  ትራንስ እና ኩዊር ጠልነት ምክያት ያላቸው ፍራቻና ሰቀቀን  ልብ ይሰብራል ። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለን ሰዎች ሰቆቃውን ለማቅለል ማድረግ የምንችለው ብዙ ነገር የለም። ነገር ግን ይህ ምናልባት በፆታ፣ በወሲባዊ ማንነታቸው፣ በሃይማኖታቸው እና/ወይም በዘራቸው ምክንያት በመካከላችን ለሚሰቃዩ ሰዎች የምንችለውን ማድረግ እንዳለብን ማስታወሻ ሊሆን ይችላል።

ሁልጊዜ ፍትሐዊ ለሆነ ነገር መቆም አለብን። በማንኛውም ትንሽ መንገድ።

Leave a Reply