አለም አቀፍ የሴቶች ቀን፥“አድሏዊነትን እናቁም (#BreakTheBias”)

በየአመቱ የካቲት 29 የሴቶች ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ይከበራል። ቀኑ የሴቶችን ስኬት እንዲሁም የሴቶች እኩልነትን ለማምጣት የሚቀሩትን ስራዎች በማንሳት ሲከበር ይውላል።

በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች ፕሮግራሞች ቢዘጋጁም ሁሉንም ሴቶች አያካትትም። ምንም እንኳን የአመቱ መሪ ቃል “አድሏዊነትን እናቁም” ቢሆንም እኛን በLBTQ ማህበረሰብ ያለንን አያካትትም። እንደአንድ በስርዐተ ፆታ እና በወሲባዊ ማንነታችን ምክንያት እንደተገፋን ማህበረሰብ ብንካተት፣  የኑሮ እውነታዎቻችንና ጉዳዮቻችን ቢነሱ መልካም ነበር። በሃገራችን እንደሁለተኛ ዜጋ እንደመታየታችን ይህ ነገር ቢቀትጥልም የካቲት 29ን  በማህበረሰባችን መካከል ውስጣዊ ውይይቶችን ማድረግ አለብን።  

የዚህ አመቱን መሪ ቃል በመያዝ ወሳኝ ውይይቶችን መጀመር ወይም መቀጠል ጥሩ አጋጣሚ ነው። ማንሳት ካሉብን ጥያቄዎች መካከል የሚካተቱት፥ በማህበረሰባችን መካከል ያሉትን ልዩነቶቻችንን እንዴት እናያቸዋለን? በተሻለ መልኩ አካታች መሆን እንዴት እንችላለን? የተሻለ የኩዊር መብት ደጋፊ እንዴት መሆን እንችላለን? ከመድልኦ፣  መገለልና አድሏዊነት የፀዳ አለምን ለመፍጠር በምን መልኩ አስተዋፆ ማድረግ እችላለን? አካታች፣ ፍትሐዊና ሁሉን ምህዳራዊ የሆነ ዓለምን የምንሠራው እንዴት ነው? ልዩነት ዋጋ የሚሰጥበትና የሚከበርበት አለም እንዴት መፍጠር እንችላለን? 

ኦድሬ ሎርድ  “ማንኛዋም ሴት ነጻ ሳትሆን እኔ ነፃ አልሆንም። የእሷ ማሰሪያ ከኔ በጣም የተለየ ቢሆንም እንኳን” ያለችውን እያንዳንዳችን ልናስታውስ ይገባል። 

መልካም የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን

Leave a Reply