አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ: የረመዳን ትውስታዎች

ከስር ያቀረብንላችሁ  <<አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ>> ከኩዊር ማህበረሰብ በፍቃድ ከሚላኩልን የግል መልእክቶች፣ የግል ማስታወሻዎች እንዲሁም ግለ ታሪኮች ላይ እየቀነጫጨብን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል። እነዚህ የፅሁፍ ቅንጭብጫቢዎች ልክ ህይወታችን አስልተን እንደማንኖራት ሁሉ የቆምንበትን የህይወታችንን ትክክለኛ ገፅ  የሚያመላክቱ  አንዳንዴ መግቢያ፣ ሌላ ግዜ ተሟልተው ያልተፃፉ እንዲሁም የተዘበራረቁ ፅሁፎች ናቸው። 


ይሄን ፅሁፍ ከምታነቡ ማንኛችሁም የኩዊር ቤተሰቦች የእናንተንም ማስታወሻ እንደምንቀበል በደስታ እያሳወቅን በetqueerfamily@gmail.com ኢሜይል እንድትልኩልን እንጠይቃለን። .

“ከጓደኛዬ ቤት አፍጥር ተካፍዬ መምጣቴ ነው እና ውይይቱ ስለኦባማ እና ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ጋብቻ ላይ ሆነ:: የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያንን ጋብቻ ከልቡ ይቃወማል ያልኩት ጓደኛዬ “አላህ ለራሳችን ልንወስን ነፃነትን ሰጥቶናል፤ ፍርድም የአላህ ነው” አለ፥ ብዙ አይቃወሙም ብዬ ያሰብኳቸው ወጣቶች ደግሞ ሁሉንም ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያንን መግደል እንደሚሹ ተናገሩ:: ምናልባት መገመት አይኖርብን ይሆናል:: ምርጥ ምግብ በተመታ አስተሳሰብ ተበላሸ 🙂 “

Leave a Reply