አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ: አባቴ እና እኔ

ከስር ያቀረብንላችሁ  <<አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ>> ከኩዊር ማህበረሰብ በፍቃድ ከሚላኩልን የግል መልእክቶች፣ የግል ማስታወሻዎች እንዲሁም ግለ ታሪኮች ላይ እየቀነጫጨብን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል። እነዚህ የፅሁፍ ቅንጭብጫቢዎች ልክ ህይወታችን አስልተን እንደማንኖራት ሁሉ የቆምንበትን የህይወታችንን ትክክለኛ ገፅ  የሚያመላክቱ  አንዳንዴ መግቢያ፣ ሌላ ግዜ ተሟልተው ያልተፃፉ እንዲሁም የተዘበራረቁ ፅሁፎች ናቸው።

 ይሄን ፅሁፍ ከምታነቡ ማንኛችሁም የኩዊር ቤተሰቦች የእናንተንም ማስታወሻ እንደምንቀበል በደስታ እያሳወቅን በetqueerfamily@gmail.com ኢሜይል እንድትልኩልን እንጠይቃለን። .

አንዳንዴ ቤተሰቦቼ ያውቁ ይሆን ብዬ አስባለሁ:: ምናልባት ቋንቋው ባይገባቸው ነገሩን ይረዱት ይሆን እላለሁ:: ኩዊር ማንነቴ በእርግጥ ከቤተሰቤ ጋር ያለኝን ግንኙነት በትንሹም ቢሆን ለውጦታል:: በነፃነት ራሴን መሆን ስለማልችል፥ አብሬ የማሳልፈው ጊዜ ውስን ነው:: 

ይበልጥ ደግሞ ከአባቴ ጋር ብዙ ጊዜ አላሳለፍኩም:: በሞት ከተለየኝ ጥቂት ወራት በኋላ ማስታወሻዬ ላይ ጫር ጫር አድርጌ ነበር::

“ውድ አባቴ 

… የነበረን ግንኙነት እንደሌላው ቤተሰብ የአባት እና የልጅ የሚባለው ፍቅር ስላልነበረው አዝናለሁ:: አልፈርድብህም! ምናልባት አንተም የራስህ የውስጥ ትግል ኖሮህ ይሆናል:: ስለእኔ ብዙ አታውቅም፣ ኩዊር ነኝ:: ኩዊርነቴንም ገና ልጅ እያለሁ ነው ያወቅኩት:: ለሴት ልጅ ያለኝን ተማርኮ በግልፅ ማውራት ባልችልም፤ ራሴን ሆኜ ግን እየኖርኩ ነው:: ምን ይሰማህ ይሆን? ብታውቅ ትጠላኝ ነበር ብዬ ማሰብ አልፈልግም:: ምንም እንደማይመስልህ ተስፋ አደርጋለሁ::

እወድሃለሁ”

Leave a Reply