የትራንስ ማንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ እና ማክበሪያ ቀን:  ተራማጅ ማህበረሰብ ለመፍጠር መስራት

ተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪ ሴት ተራማጅ እና አካታች ያልሆነ የኩዊር ማህበረሰብ ውስጥ መካተት እንደማልፈልግ ሁሌም አውቅ ነበር:: ይህም ማለት ማህበረሰባችን ትራንስ፣ ተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪ ሴት እና ወንድ፣ ኩዊር፣ ባይሴክሽዋል፣ ፓን፣ ኤሴክሽዋል፣ ፍናፍንት እና የተለያዩ ስርዓተ ፃታ እና ወሲባዊነትን ማካተት አለባቸው ማለት ነው:: 

ከነን ባይነሪ ኢትዮጵያዊ ጋር የነበረን ውይይት ላይ የኢትዮጵያ ኩዊር ማህበረሰብ ትራንስ ፣ ነን ባይነሪ እና ሌላንም አካታች አለመሆናቸው በጣም አሳዝኖኛል:: 

“የተቃራኒ ፃታ አፍቃሪነትን እንደትክክለኛው የያዙ ፅንሰሃሳቦች በኩዊር ሰዎች መካከል ይከራሉ:: ያም ተስፋአስቆራጭ ነው ምክንያቱም ውይ አንድ ነን ብለሽ ታስቢያለሽ:: ታይኛለሽ አይሻለሁ እና ሰዎች በማንነታቸው እንቀበላለን ብለሽ ታስቢያለሽ::”

በውይይታችን ላይ ቀጥለውም “በኩዊር ሃበሻ መካከል እንኳን ስለስርዓተ ፃታ እና ከሁለትዮሽ ውጪ ስላሉ መቀበል ላይ ገና እንደሚቀራቸው ነው የሚታየኝ::”

በቀላል መንገድ የትራንስ መብትን እና የአካታችነትን አስፈላጊነት “ትራስን ኢትዮጵያውያን አሉ አይደል? ሴት እና ወንድ ብቻ አይደለንም::” ብለው ይገልፃሉ::

ለትራንስ መብትና ተካታችነት መሟገት አለብን ምክንያቱም ኩዊር ማህበረሰባችን ሁሉንም ይይዛል:: በሚያሳዝን ሁኔታ አንዳንዶቻችን  እንደማህበረሰብ ምን እንደሚያያይዘን ማየት ያቅተናል፤ ለሎችም ቦታን አንሰጥም:: ሁሉንም መቀበል እና አካታችነት እራሳችንን ለመቀበል ግዴታው መስመር እንደሆነ መረዳት ይሳነናል:: ለእያንዳንዳችን መቆም ማለት ለሁላችም ዘላቂ ለውጥ ማምጣት ማለት እንደሆነ እንዘነጋለን:: አንዳንዶቻችን በእንቅስቃሴዎቻችን የትራንስን ጉዳይ እንደሁለተኛ አድርገን እንይዛለን፤ ልክ ችግርን በተራ መቅረፍ ያለብን ይመስል::  ለሁለም ማንነቶች ቦታ መስጠት አለብን ምክንያቱም የሁላችንም ልምድ ነው የተሻለ፣ ጠንካራ እና የበለጠ ተራማጅ ማህበረሰብ የሚያደርገን:: 

ትራንስ ቪዚቢሊቲ ቀን የሁላችንም ጉዳይ ነው:: የትራንስ ሰዎች ጥንካሬ፣ ቁርጠኝነት፣ እና ፅናትን የሚያስታውሰን ቀን ነው:: እናም ከትራንስ፣ ከሁለትዮሽ ስርዓተ ፃታ ምድብ ውጪ እና በስርዓተ ፃታ ካልተገደቡ ሰዎች ጋር ለመቆም ራሳችንን ደጋግመን ለመስጠት ልንጠቀምበት የሚገባ ቀን ነው::

Leave a Reply