ቤትን ማግኘት በፅሁፍ –  የሳምራ ሐቢብን “We have Always Been Here” ምልከታ

“ምናልባት ቤት ማለት የታያችሁበትና ጥሩ መቀበል ያገኛችሁነት ቦታ ሊሆን ይችላል።” 
– ሳምራ ሐቢብ፥We Have Always Been Here “ከተሰኘው መፅሃፍ የተወሰደ

ስለ ቤት ያለኝ አመለካከት ከአገር ጋር የቅርብ ትስስር ያለው ሰው እንደመሆኔ መጠን “ቤት የትም ቦታ መኖር ነው” የሚለው አስተሳሰብ ነፃ አውጥቶኛል ። የሳምራ ሐቢብን መፅሐፍ We Have Always Been Here በማንበቤ በርግጥም ቤቴን የፈጠርኩት ከተወለድኩበት ሀገር ለይቼ መሆኔን የሚያረጋግጥ ሌላ ምክኒያት ነበር። እርስ በርስ የተያያዙት ማንነቶቿ ማለትም ሙስሊም፣ ኩዊር ፣ ስደተኛ ከእኔ ፈጽሞ የተለዩ ናቸው ።

ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ መሆን ሕገ ወጥ ባልሆነበት ቦታ ትኖራለች፥ ምንም እንኳ ሁልጊዜ በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ እና በእስልምና ጥላቻ ላይ መጓዝ የራሱ አነስተኛ ሞት አለው። ይሁን እንጂ ያጋጠማት ትግልና ያጋጠማት ተሞክሮ የእኔን ሁኔታ በጣም የሚያንጸባርቁ ከመሆኑ የተነሳ እኔ፥ ኤቲይስት ፣ ኩዊር  ፣  የትውልድ ቦታ ላይ የምትኖር ራሴ በእሷ ተሞክሮ መመልከቴን ቀጠልኩ ።

ኩዊርነት ኢትዮጵያዊ ከመሆን ጋር የማይጣጣም ሆኖ ይታያል – የእኔን የተሳሰረ ማንነቴን በተፈለገ ጊዜ መክፈትና መዝጋት የምችል ይመስል። ማንነቴን “ንጹህ ኢትዮጵያዊ” የሚለውን አንዳንድ አስተሳሰብ እንዲስማማ ማድረግ ይቻል ይመስል። ራሴን አንድ ሚሊዮን ቦታ ለመከፋፈል እምቢ ስለምል ይሄ እምቢተኝነት ከኢትዮጵያ ያርቀኛል፣ ቤት መሆን ካለበት ቦታ ማለት ነው። ቤተሰቦቿ የአህመድያ ማኅበረሰብ አባል በመሆን በፓኪስታን ያጋጠማቸውን የመንግሥት ማእቀብ ስታሰላስል፤ ሃቢብ ሙስሊም እና ኩዊር በመሆኗ በምታደርገው ትግል ውስጥ ራሴን ተመለከትኩ ።  ያ ማሰላሰሏ በኢትዮጵያ አሁን ያለውን ጦርነት እና የአንዳንድ የብሄር ቡድኖችን ስደት እንሳስብ አደረገኝ እና ይህ ደግሞ እንደ ኩዊር ሰው ይበልጥ ለአደጋ የተጋለጥኩ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ አደረገኝ።

ነገር ግን ከሁሉ የበለጠ ከፅሁፏ የተሰማኝ ሃቢብ ያለማቋረጥ መቃወሟ ሳይሆን አይቀርም። ሌሎች እሷን እንዲገልጹላትና ለእሷ የሚበጀውን ነገር እንደሚያውቁ አድርገው እንዲያስቡባት አትፈቅድም ። ሁሉንም ነገሯን ሆና፣ ራሷን ተቀብላ እሷን ከሚደግፏት ሰዎች ጋር በመሆን፤ እያንዳንዱን እርምጃ  ትታገላለች ። ምንም እንኳን “መረጋጋትና ማበረታቻ ፣ እንደ ግለሰብ ለመማር እና ለማደግ የሚያስችል ቦታ” የሚያቀርብ ቤት ባይኖራትም ራሷን ሆናለች። 

Leave a Reply