ስለማስታወሻ  ለመጀመሪያ ፍቅሬ

ንስንስ የመጨረሻው እትም ላይ አንደኛውን ፅሁፍ የፃፈችው ከአንድ ሰው ጋር እንዲሁ ስለፅሁፉ ቻት አደረጉ። ይሄ አጭር ቻት እኛ በንስንስ ዙሪያ ከእናንተ ጋር እንዲኖረን የምንፈልገውና ተስፋ የምናደርገው ውይይት ነው። ለማደግ የሚተጋ እና ድንቅ የኩዊር ማህበረሰብን ለማምጣጥ እንዲህ ያሉ ግልፅ ውይይቶች ያስፈልጉናል ። አስተያየቶቻችሁን ለመስማት እንወዳለን። (ፅሁፉ ማሻሻያ ተደርጎበታል)

ፀሃፊ፡ ፅሁፉ እንዴት ነበር?
በጣም ደስ ይላል  ፣ ቀለል ያለ ነው  ፣ ከራስ ጋር በቀላሉ ተገናኝቶ የራስን የመጀመሪያ ፍቅር እንድታስቢ ያደርጋል። 

ፀሃፊ፡ ፍቅር በፍቅር የሆንኩ መስሎኝ ነበር፥ ሆኛለሁ?
አልሆንሽም። እና እውነትም ነው። ሰዎችን የምንመዝነው እውነተኛ እና ትርጉም ያለው ግንኙነት በነበሩን ሰዎች ነው። 

ፀሃፊ፡ ግን ግንኙነት ለመመስረት ለምንተዋወቃቸው ፍትሃዊ አይደለም፥ የበፊት የፍቅር አጋሬ በምንም እዛ ሚዛን ላይ ልትደርስ አልቻለችም
የፍቅር ግንኙነት ብቻ አይደለም የቅርብ ጓደኝነኘትም ጭምር። እንደቅርብ ጓደኛዬ ፍቅር እና እንክብካቤን ከማትሰኝ ጋር አዲስ የቅርብ ግንኙነትን መጀመር አልችልም። 

ወደንና ተምረንበት የነበረውን አይነት ፍቅር ያንን ብቻ በመጠበቅ እስካልተገደብን ድረስ መፈለግ ችግር አለው ብዬ አላስብም፤ አንቺም ያንን እያደረግሽ አይመስለኝም። ከመጀመሪያውም ከበፊት የፍቅር አጋርሽ ጋር የተለየ ልምድ ነበር፤ ሚዛን ከሆነችው ከመጀመሪያዋ የፍቅር አጋርሽ በጣም ትለያለች ነገር ግን ራስሽን አልገደብሽውም። 

የመጀመሪያ የፍቅር አጋርሽን ምርጥ ባሕርያት እየተዋወቅሻት ላለችው ሴት በተደጋጋሚ ማንሳት ጥሩ አይሆንም። ሁልጊዜ ስለእሷ መናገር ተገቢ ባይሆንም ነገር ግን ያንን የፍቅር ግንኙነት እንደ ሞዴል መውሰድ ፤ እውነት ለመናገር ምንም ችግሩ አይታየኝም።  

የሚያሳዝነው ግን የመጀመሪያ ፍቅር ወይም በትዝታ ውስጥ የምንኖርበት ልዩ የፍቅር ግንኙነት አንድ ብቻ ነው።  ያሳዝናል ግን ደግሞ እንዲህ አይነት ፍቅርን በዚህ ብጥብጥ ባለና በተመታ አለም ላይ ማሳለፍ መቻል በጣም  ደስ የሚልም ነገር ነው። 

 

Leave a Reply