የሚያካትት የአፍሪካ ቀንን በዓይነ ሕሊና መመልከት

የአፍሪካ ቀን በአፍሪካዊያን እና በመላው አለም በሚገኙ አፍሪካውያኖች በሙሉ የሚከበር ቀን ነው።

ግንቦት 17 የሚከበረው ይህ የአፍሪካ ቀን የአፍሪካን አንድነት ህብረት ምስረታን አስቦ ይውላል። እኛ አፍሪካውያንም ባለንበት ቦታ ሁሉ ሆነን ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ባህላችንን፣ ታሪካችንን እና ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ስኬታችንን አስበን የምንውልበት ቀን ነው።

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለኢትዮጲያውያኖች ትልቅ ትርጉም አለው። ቀዳማዊ ሃይለስላሴ የአፍሪካ አንድነት ህብረትን ለመጀመር ቀደምት መሪ ነበሩ። ድርጅቱም እስካሁን ድረስ ተወልጄ ባደግኩበት አዲስ አበባ ኢትዮጲያ ውስጥ ዋና መቀመጫውን አድርጎ አለ።

በትናንትናው ዕለት አፍሪካዊነት ደምቆ ሲከበር ማየቴ የአህጉራችንን አቅም በጥልቅ እንድገነዘብ አድርጎኛል። ከአቡጃ እስከ ዊንድሆክ ድረስ እኛ አፍሪካውያን ድምፃችንን ከፍ አድርገን በህብረት አክብረናል። የባህል ስብጥራችንን እና አፍሪካን በጥልመት ብቻ የተቀመጠ ተረኳን አጥፍተን አሳይተናል።

አፍሪካዊ በመሆኔ ካለኝ ኩራት ባሻገር ግዜው ማንነቴንም ማንፀባረቂያም ነው ብዬ አስባለሁ። ኩዊር ነኝ። ቢሆንም ተወልጄ ባደግኩበት እና የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ በሆነችው ከተማዬ ማንነቴን ተቀብዬ እንድኖር የሚያስችል ነፃነት ግን የለኝም።

በፍቃድ ላይ ለተመሰረተ የተመሳሳይ ፆታ ወሲብ ከ እስከ አመት ድረስ እስራት ሊጠብቀኝ ይችላል። 1 15

እንደውም እኔ እድለኛ ነኝ። ጎረቤት ሃገር ሶማሊያ ብኖር ደግሞ ቅጣቱ ሞት ነበር። ከግማሽ በላይ የአፍሪካ

ሀገራት ይህንን ህግ በተመሳሳይ ይተገብሩታል።

እንደኔ ኩዊር ለሆነ ሰው አፍሪካዊነት ምን ማለት ነው በፆታ እና በጀንደር ማይኖሪቲ ተገፍተው እንደሚኖሩት ? ሌሎች ሁሉ ተወልጄ ባደግኩበት ሀገር እኔም በፍርሃት ነው የምኖረው። በማህበረሰብ ተሳትፎዎች ላይ ማንነቴን ሆኜ የምፈልገውን ያህል የማልሳተፍ ስለሆንኩ አፍሪካዊነቴ ጥያቄ ውስጥ የሚጥል ህልውና ውስጥ ነው ያለሁት። ራሴን በምደብቅበት እና በማንነቴ በምሳደድበት ማህበረሰብ  ውስጥ ሆኜ በአፍሪካዊነቴ መኩራት ያቅተኛል። በዚህ ጉዳይምብዙ አፍሪካውያን በየእለቱ በፆታዊ ማንነታቸው እና ፆታዊ ዝንባሌያቸው ምክንያት ጥቃት ይደርስባቸዋል።

ሺላ አዲሃምቦ ሉሙምባ የ አመት ነን ባይነሪ ሌዝቢያን ስትሆን ከወር በፊት በጎረቤት ሀገር ኬንያ ተገድላ 25 የተገኘች ነች። የጥበቃ ሃይሎች በአክራ የሚገኘውን የ ቢሮ የዘጉት ሲሆን የደቡብ አፍሪካ ኩዊሮችም LGBTQ+ እንዲሁ እየተገደሉ እና እየተደፈሩ ህገመንገስታዊ መብታቸው እየተጣሰ ይገኛል።

በሚታወቅ መልኩ ሁላችንም የዚህ ጥቃት ሰለባ ሆነን መሪዎቻችን ግን የጥቃቱ ደጋፊዎች እና የእኩይ ተግባር ተባባሪ ሆነው እናገኛቸዋለን። እዚሁ ኬንያ ፕሬዘደንት ኡሁሩ ኬንያታ ጉዳዮችን ጥቅም የሌለው አላስፈላጊና LGBTQ + የሰብአዊ መብት ጥያቄ ሊሆን እንደማይችል አድርገው ተናግረዋል። የዩጋንዳው ፕሬዘደንት ዮወሪ ሙዜቬኒ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን በሙሉ ይቀፋሉ ሲሉ በድፍረት ተናግረዋል። ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ደግሞ ከውሾች ጋር ፣ ጉዳት ከሚያደርሱ የዱር እንስሳ እና እንዲሁም ወባዎች ጋር አመሳስለውናል።

የዚህ ሁሉ ጥላቻ እና ጥቃት መሰረት መሆን አፍሪካዊነት አይደለም ተብሎ ስለሚታሰብ ነው። LGBTQ+ ከምእራባውያን የመጣ ብሂል ነው ብለው ቢደመድሙም እውነታው ግን የተመሳሳይ ፆታን ግንኙነት መጥላት ከምእራባውያን የተወረሰ መሆኑ ነው። በቅኝግዢ ውስጥ ያላለፈችው ኢትዮጲያ እንኳን ይሄንን ጥላቻ ተቀብላ ህግ መስርታበታለች።

በእርግጥ አንዳንዴ በትንሹም ቢሆን ተስፋ ይታያል። የዛሬ አመት አካባቢ የቦትስዋና ዳኛ ማይክል ለቡሩ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ጥላቻ በተመለከተ ሲከራከር ጥላቻው ከእንግሊዞች ተውሰን እንደወረደ ያመጣነውና ያለ ሀገራችን ዜጋ “ምክክር ህግ አፅድቀናል ሲል ተናግሯል። “

እንደ አፍሪካዊ ኩዊር እንደ ዳኛ ማይክል ለቡሩ ያለ ሰው ያኮራኛል። አፍሪካዊ ነኝ ኩዊርም። በራሴ ማንነት ላይ ማንኛውም አይነት መከፋፈልን የምጠላ ኩሩ አፍሪካዊ ኩዊር ነኝ። የአፍሪካ ቀን ለእኔና መሰሎቼ ቦታን ሊሰጠን እና ትኩረትን ልናገኝ ይገባል ብዬ አስባለሁ።

Leave a Reply