መልካም የኩራት ወር

“ኩራት በእናንተ እድሜ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚከበር ይመስላችሗል?” ይሄ ጥያቄ በሶስት ወር አንዴ በሚታተመው ንስንስ መፅሄታችን ላይ የጠየቅነው ጥያቄ ነው። አብዛኞቹ ምንም አይነት የኩራት በዓል በእድሜያቸው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደማያዩ ነበር የመለሱት። 

“የኩራት በዓልን እዚህ ሃገር የማይ አይመስለኝም። ግን በሆነ ተአምር ቢካሄድ ራሱ፥ ሰው በድንጋይና እንጨት ይመጡብናል። ሰዎች እኛ ላይ ትልቅ ጥላቻ ነው ያላቸው፥” ይላል ናቲ። በህይወታችን ያለውን የሆሞ እና ትራንስ ጥላቻ የሚያብራሩ ምላሾችን ማንበብ ልብ ይሰብራል። ይሄ ግን አትዮጵያ ውስጥ ላለን ኩዊር አስደናቂ አይደለም። 

ይልቅ የሚደንቀውስ ትንሽ የሚመስለው ግን ደግሞ ትንሽ ያልሆነው ኩዊር ሰዎች የሚያስገኙትና የሚያሸንፉት ድል ነው።

ህብስት በኩራት በፖሊስ ጣቢያ በኩል የቀስተደመና ማስኳን አድርጋ ማለፍ አንድ ድል ነው። ብቻዋን በመስቀል አደባባይ ፕራይድን ያከበረችውም ሴት ሌላ ድል ነው። በብዙ አመት የሃይማኖታዊ ጫና ውስጥ ሆነን ራስን መምረጥ መቻል ትልቅ ድል ነው። 

አለመንበርከክ ወይም መቆም መቻል ትልቅ ጥንካሬ ነው። ይሄም አንደኛው የኩራት አከባበር ላይ በንስንስ ያነሳነው ነው።

የኩራት ወርን እያከበርን የንስንስን የኩራት እትም ማንበብ እንደኩዊር ማህበረሰብ በፅናት የቆምን እንደሆንን አንድ ጥሩ ማስታወሻ ይሆናል ብለን አሰብን።  

ኩራት አብዮታዊ ነው፤ እኛም አንዱ ትንሽ ምሳሌ ነን። 

መልካም የኩራት ወር

Leave a Reply