የኩራት ቀን በኢትዮጵያ

በየአመቱ የኩራት በዓል ሲመጣ ልጅ እያለሁ ተደብቄ ሌዝብያን ማለት ምን ማለት እንደሆነ በኢንተርኔት ስመረር ያገኘሗቸው የሰዎች ፎቶ እና የህይወት ተሞክሮዎች፣ በማንነታቸው ተገፍተው የተገደሉ እንዲሁም እስከህይወታቸው ፍፃሜ ለመብታቸው የታገሉ ብዙዎችን ያገኘሗቸውን ያስታውሰኛል:: ክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ እንዳደገች ልጅ ደግሞ ለክርስቲያን ተመሳሳይ አፍቃሪያን መብት የታገሉ ብዙዎችን አስባለሁ:: ኢትዮጵያ ውስጥ ባድግም ባህል እና ቋንቋችን ባይገጣጠምም..ኩዊር በመሆናችን ብቻ የሚፅፉቸው ፅሁፎችና ሰርተዋቸው ያለፉቸው ስራዎች ያስተሳስሩኛል:: የእነርሱን ስራዎች ባላነብ.. እውነት ለካ እንደኔ ሌሎችም አሉ ማለት ባልችል ምን አይነት ህይወት እየመራሁ እገኝ እንደነበር እኔንጃ! ያኮሩኛል እኔም በራሴ እንድኮራ አድርገውኛል:: 

በዚህ ጥላቻ በሞላው ሃገር ላይ ታዲያ እንዲህ አይነቱን ማህበረሰብ ፈጥረን በማህበራዊ ሚዲያው ንስንስ ብለን ከመታየት በላይ ምን ኩራት አለ?!

ወደሃገራችን ስንመጣ ድብቅ የፌስቡክ አካውንቶችን ከፍተው ቀን ከለሊት አይዞን የሚሉን፣ ብቻችሁን አይደላችሁም ያሉን ጓደኞች ሆነው መሸሸጊያ የሆኑን ብዙ አሉ:: የኩራት ቀንን በአደባባይ ባንዲራ ማውለብለብ ባንችልም፣ የቃልኪዳን የጋብቻ ፎቶዎቻችንን እያጋራን በነፃነት መውጣት ባንችልም፤ በዚህ ጥላቻ በሞላው ሃገር ላይ ታዲያ እንዲህ አይነቱን ማህበረሰብ ፈጥረን በማህበራዊ ሚዲያው ንስንስ ብለን ከመታየት በላይ ምን ኩራት አለ?!

2 thoughts on “የኩራት ቀን በኢትዮጵያ”

    1. Enameseginalen Beteal.
      Egnam endeza new yemiseman. Kebefitu beteshale ahun lay sefi yehone dimts ale. Yibelt degmo endeminichemir tesfa Alen. Melkam ken! Melkam Yekurat wer 🏳️‍🌈

Leave a Reply