አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ: ምቹ ቦታዎችን መፍጠር ፥ ድልድዮችን መገንባት

ከስር ያቀረብንላችሁ  <<አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ>> ከኩዊር ማህበረሰብ በፍቃድ ከሚላኩልን የግል መልእክቶች፣ የግል ማስታወሻዎች እንዲሁም ግለ ታሪኮች ላይ እየቀነጫጨብን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል። እነዚህ የፅሁፍ ቅንጭብጫቢዎች ልክ ህይወታችን አስልተን እንደማንኖራት ሁሉ የቆምንበትን የህይወታችንን ትክክለኛ ገፅ  የሚያመላክቱ  አንዳንዴ መግቢያ፣ ሌላ ግዜ ተሟልተው ያልተፃፉ እንዲሁም የተዘበራረቁ ፅሁፎች ናቸው።

 ይሄን ፅሁፍ ከምታነቡ ማንኛችሁም የኩዊር ቤተሰቦች የእናንተንም ማስታወሻ እንደምንቀበል በደስታ እያሳወቅን በetqueerfamily@gmail.com ኢሜይል እንድትልኩልን እንጠይቃለን። .

የኩዊር ፍቅር ግንኙነቶችና የቅርብ ጓደኝነቶች ራሳችንን ለመቀበል እና ትራንስ እና ተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪ ጠል የሆነውን የኢትዮጵያ ሁኔታ እንድንውጣ ይረዳናል:: ከታች ያለው ቅንጭብጫቢ በሁለት ኩዊር ኢትዮጵያውያን መሃል የተደረገ ነው::

እንዴት ነሽ፥

ኢሜልሽን ስራ ቦታ ሆኜ ስለከፈትኩት እንደምፉልገው ብዙ አልፅፍልሽም፤ ሰላም ነሽ ወይ እና አመሰግናለሁ ልበልሽ ብዬ ነው::

እና ራስን መቀበል ትልቅ ድፍረት እንደሚጠይቅም ላስታውስሽ ነው:: ሴት ሆነን ስናድግ ወሲባዊነታችንን እና የወሲብ ፍላጎቶቻችንን እንደመጥፎ እና ነውር እንድናይ ተደርገናል:: በእንደዚህ አይነት ባህል ውስጥ እንዳደገ “የተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪ ነኝ” ማለት መቻል በጣም ትልቅ ነገር ነው:: ድፍረት እና ፅናትሽን ሁሌም አስታውሺ! ማያ አንጄሎ እንደምትለው “ድንቅ ሴት ነሽ” ብዙ ኢትዮጵያዊ ዳያስፓራ በሚኖርበት ከተማ እንደሚኖር እና ቅርበት እንዳለው ሰው ቅድመ ጥንቃቄ መውሰድ ይኖርብሻል፤ ግልፅ ነው:: ቢሆንም ይመችሽ!

በቅርቡ በደንብ እፅፍልሻለሁ! በአጭሩ ስለቆረጥኩት ይቅርታ ፤ ጥሩ ጓደኛ አይጥፋ 😉

– እንዳቺው ሆሞ!

Leave a Reply