አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ: ያለ ይቅርታ እራሴን መሰየምን መማር

ከስር ያቀረብንላችሁ  <<አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ>> ከኩዊር ማህበረሰብ በፍቃድ ከሚላኩልን የግል መልእክቶች፣ የግል ማስታወሻዎች እንዲሁም ግለ ታሪኮች ላይ እየቀነጫጨብን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል። እነዚህ የፅሁፍ ቅንጭብጫቢዎች ልክ ህይወታችን አስልተን እንደማንኖራት ሁሉ የቆምንበትን የህይወታችንን ትክክለኛ ገፅ  የሚያመላክቱ  አንዳንዴ መግቢያ፣ ሌላ ግዜ ተሟልተው ያልተፃፉ እንዲሁም የተዘበራረቁ ፅሁፎች ናቸው።

 ይሄን ፅሁፍ ከምታነቡ ማንኛችሁም የኩዊር ቤተሰቦች የእናንተንም ማስታወሻ እንደምንቀበል በደስታ እያሳወቅን በetqueerfamily@gmail.com ኢሜይል እንድትልኩልን እንጠይቃለን። .

ከታች ያለው ቅንጭብጫቢ ከአንድ የረዥም ኢሜል ልውውጥ የተወሰደ ነው:: “ጌ ለመሆን የወሰንሽው መቼ ነው?” ለሚል ጥያቄ የተሰጠ ምላሽ ነው::

“ጥያቄሽን በመመለስ ልጀምር… “ወደ ጌ መቀየር” የሚል ውሳኔ አላደረኩም:: እኩዮቼ የተቃራኒ ፃታ ተማርኮ በጀመሩበት እድሜ ላይ እኔ የነበረኝ ተማርኮ ለተመሳሳይ ፃታ ነበር:: እኔ ያደረኩት ውሳኔ አይደለም:: በቀላሉ ተማርኮዬን ተቀብዬ ነው:: “ወደ ጌ መቀየር” አላስፈለገኝም ፣ የነበረኝን ተማርኮ ስዬሜ መስጠት እና ለኔ በገባኝ መልኩ የነበረኝን ስሜት መረዳት ነበር:: ይሄ ማለት እንዳንድ ሰዎች ከተቃራኒ ፃታ ጋር ከሆኑ በኅላ አያውቁትም ማለት አይደለም ወይም ለሁለቱም ፃታ ተማርኮ የላቸውም ማለት አይደለም ወይም ከሴት እና ወንድ ግድብ ውጪ ላሉ ሰዎች:: “ትክክለኛ” ወይም “ብቸኛ” የተቃራኒ ፃታ አፍቃሪ ወይም ተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪነት ወይም ባይሴክሽዋል የመሆን መንገድ አለ ብዬ አላስብም፤ ሁላችንም ተማርኳችን ለተለያዩ ሰዎች እንደመሆኑ የሚሰማንን እና ትክክል ነው ብለን እንደምናስበው ነው መሆን ያለብን::

Leave a Reply