ዩጋንዳ ከሚገኘው SMUG ጋር ከጎን እንቆማለን

ዛሬ አፍሪካ ውስጥ ላለን ኩዊር ሰዎች በጣም የሚያሳዝን ቀን ነው፤ ይበልጥ ደግሞ ምስራቅ አፍሪካ ላለን:: በኩዊር ጉዳዮች ላይ የሚሰራው <<ሴክሽዋል ማይኖሪቲ ዩጋንዳ>> (SMUG) መንግታዊ ያልሆነ ሃገር በቀል ድርጅት በመንግስት ታግዶ እንቅስቃሴ በአፋጣኝ እንዲያቆም ትዛዝ ወጥቷል::  

SMUG ከተመሰረተበት 2004 ጀምሮ ለዩጋንዳ ኩዊር ማህበረሰብ ቃልቅ ድምፅ በመሆን ለብዙ ኩዊር ሰዎች ህይወት ላይ ትልቅ ሚና ተጫውቷል:: የጤና አገልግሎቶችን ያስተዋውቃል፣ ኩዊር ሰዎች በነፃነት እንዲኖሩ ያበረታታል፤ ይደግፋል::

SMUG እና ግድያ እንደተፈፀመበት ዴቪድ ኬቶ ያሉ አባላት የጀግንነት  እና እንደማህበረሰብ ስንደራጅ ምን ማምጣት እንደምንችል የሚያሳዩ ምሳሌዎች ናቸው:: በኩዊር ዙሪያ ዩጋንዳ ብዙ ርቀት የተጓዘችው ያለፍርሃት እና ይቅርታ ለራሳቸውና ለማህበረስባቸው በቆሙ የማህበራዊ አንቂዎች ነው::

የSMUG መዘጋት በአንድ አፍሪካ ሃገር ኩዊር አፍሪካውያንን ለመጨቆን ወይም ዝም ለማሰኘት የተደረገ ሙከራ ነው:: የSMUG ዳይሬክተር ፍራንክ ሙጊሻ እንዳለው “ስር በሰደደ የተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪያን ጠልነት ስርዓት ላይ ፣ በፀረ ጌ እና ፀረ- ስርዓተ ፃታ እንቅስቃሴዎች ላይ የተመረኮዘ አደን እንደሆነ ግልፅ ነው”::

ይህ ለSMUG በጣም ትንሽ ነገር እንደሆነ ኩዊር ኢትዮጵያ ታምናለች:: SMUG ያሏቸውን ስራዎች እና ለኩዊር ሰዎች ምምፅ የመሆንን ስራ የመቀጠያ መንገድ እንደሚያገኙ አንጠራጠርም:: SMUG ዝም እንደማይሉ አንጠራጠርም::

ከSMUG እና ኩዊር አፍሪካውያን ጎን እንቆማለን::

Leave a Reply