ቴሌግራም ላይ ይቀላቀሉን (@t.me/queeret)

የቴሌግራም ቻናላችንን በመክፈታችን በጣም ደስ ብሎናል!

ኩዊር ኢትዮጵያ በኢትዮጵያም ሆነ በዲያስፖራ ለኢትዮጵያውያን LBQ ማህበረሰብ የተለያዩ ይዘቶችን ስታዘጋጅ ቆይታለች:: ብሎጎች፣ ፖድካስት፣ መፅሄትና የተለያዩ ይዘቶችን እንደ ፌስቡክ፣ ትዊተር እና ኢንስታግራም ባሉ ማህበራዊ ሚድያ አዘጋጅታለች::

የቴሌግራም ቻናል መክፈታችንም ከማህበረሰባችን ጋር ያለንን ግንኙነት ለማስቀጠል ካለን ፍላጎት የተነሳ ነው:: የኢትዮጵያ LBQ ሰዎች ተለይተው ሳይታወቁ በLBQ ጉዳዮች ላይ ይዘቶችን የሚያገኙበት በግልፅ የማይታወቅ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ለመስጠት ነው።

የLBQ ማህበረሰብ ኢትዮጵያዊ LBQ ስለመሆን ህይወት ልምድ፣ ታሪኮች እና ሀሳቦች መረጃ የሚገኙበትን ቦታ ለመፍጠር የተለያዩ መድረኮችን መጠቀም አስፈላጊ ነው ብለን እናምናለን። በተጨማሪም ይህ ቻናል በሁሉም አስደሳች እና ፈታኝ ጊዜያት ማህበረሰቡ እርስ በርስ የሚተሳሰርበት እና የሚደጋገፍበትን መንገድ እንደሚሰጥ ተስፋ እናደርጋለን።

ለተሳትፎዎ እናመሰግናለን እና ተሳትፎዎን በጉጉት እንጠባበቃለን!

 t.me/queeret ላይ ይቀላቀሉን::

Leave a Reply