ንስንስ በቅርቡ ይወጣል፡ “የመረጥናቸው ቤተሰቦች” እትም

“ጓደኞቻችንን መምረጥ እንችላለን ነገር ግን ቤተሰቦቻችንን መምረጥ አንችልም” ይላል የድሮው አባባል።

እድል ካለልን ሊረዱን የሚችሉ፣ ፍቅርን ሰጥተው የሚቀበሉና የሚያበረታቱ ቤተሰቦች ውስጥ ነው የተወለድነው። ለአብዛኞቻችን LGBTQ+ ኢትዮጵያውያን ግን ይህ የኛ እውነታ አይደለም። አብዛኛውን ጊዜ ቤተሰቦቻችን ለእኛ ይሻላል ብለው ቢያስቡም እኛን ሊጎዳን የሚችል እርምጃ ለመውሰድ ቀዳማዊ ናቸው።

ለእኛ ኩዊር ሰዎች በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥመንን የማያቋርጥ ጥላቻና መገለልን እንድንቋቋም የሚያስችሉንን ብዙ መንገዶችን ለመማር ተገደናል። ከነዚህ መንገዶች ዉስጥ አንዱ የራሳችንን ማህበረሰቦች መፍጠር ነው። በአለም ላይ እንዳሉት ኩዊር ሰዎች ሁሉ እኛም ኢትዮጵያውያን ኩዊሮች እራሳችን የመረጥናቸውን ቤተሰቦች እየመሰረትን ስንኖር ቆይተናል።

የመረጥናቸው ቤተሰቦች – “የደም ዝምድና የሌለን፣ ነገር ግን ለጋራ መደጋገፍና ፍቅር ዓላማ ተብለው የተመረጡ፣ በህጋዊ እውቅና ያገኙም ሆነ ያላገኙ የዝምድና ትስስሮች” ተብሎ ይተረጎማል።

በመረጥነው ቤተሰባችን ውስጥ ማን አለ? እነዚን ዝምድኖችን እንዴት ነው የምንመሰርታቸው? በምን ይጠቅሙናል? እነሱን የበለጠ ጠንካራ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? እንዴትስ እናከብራቸዋለን? እነዚህ ጥያቄዎች እና ሌሎችም በበዚህ ሳምንት ለመታተም የታቀደው የንስንስ እትም ትኩረት ይሆናሉ።

አዝናኝና አበረታች እንደሚሆንላችው ተስፋ እናደርጋለን!

ላለፉት የንስንስ እትሞች እባክዎን ይህን ሊንክ ይከተሉ፡- ዕትም 1, ዕትም 2, ዕትም 3, ዕትም 4

Leave a Reply