ስለባይሴክሽዋሊቲ የተሳሳተ አፈታሪክን ማስተካከያ

የባይሴክሽዋሊቲ ቀንን ስናከብር፥ ባይሴክሽዋሊቲ ማለት አንድ ስርዓተ ፃታ ተማርኮ ላይ ብቻ ያልተወሰነ እንደሆነ ማስታወስ ይኖርብናል:: ማህበረሰባችን ውስጥም ሁሉም ማንነቶች እኩል ቦታ ሊሰጣቸውና ሊከበሩ እንደሚገባ መተዋወስ ይኖርብናል:: 


ስለባይሴክሽዋሊቲ የተሳሳቱ አተያዮች እና እውነታዎቻቸው፡

አፈ ታሪክ: “ባይሴክሽዋሊቲ የአንድ ሰው ጌ እና ሌዝቢያን ሆኖ ለመውጣት መንደርደሪያ እንጂ የእውነት አይደለም::” 
እውነታ: እውነት ነው አንዳንድ ሰዎች በሌላ ማንነት ከመውጣታቸው በፊት ለራሳቸው ባይሴክሽዋል ማንነትን ይሰይማሉ፤ ልክ አንዳንድ ሰዎች LGBTQ+ ነን ብለው ከመውጣታቸው በፊ ተቃራኒ ፃታ አፍቃሪያን ነን እንደሚሉት ማለት ነው:: ሌሎች ደግሞ ባይሴክሽዋል ነን ከማለታቸው በፊት ጌ ወይም ሌዝቢያን ማንነትን ይጠቀማሉ::  ባይሴክሽዋሊቲን ለየት የሚያደርገው የፍቅርን፣ ስሜትን እና ተማርኮን ከተገደበው ተፈጥሮ ውጪ ማየቱ ነው:: ለብዙዎች መንደርደሪያ ወይም መቆያ አይደለም:: 

አፈ ታሪክ: “ባይሴክሽዋል ነን የሚሉ ሰዎች ተቃራኒ ፆታ አፍቃሪ ናቸው፣ ዝም ብለው እየሞከሩ ወይም እንደፋሽን እያዩት እንጂ” 
እውነታ: ይህ ባይ የሆኑ ሰዎች የሚደርስባቸው የተለመደ ጭፍን ጥላቻ ነው:: ሰዎች ወሲባዊነታቸውን የመመርመር እና የመሞከር መብት አላቸው ይህን ደግሞ አጉል አራዳ እንሁን ሲሉ ነው ብሎ ማቃለል ልምዳቸውን ማጥፋት ነው:: ሙከራ እያደረጉ ያሉ ተቃራኒ ፃታ አፍቃሪያን ቢሆኑ እንኳን እየሞኩሩ ያሉ ባይሴክሽዋሎችን ልምድ ሃሰት አያደርገውም:: 

አፈታሪክ:“ባይሴክሽዋሎች እንደጌ ወንዶች እና ሌዝቢያኖች የተጨቆኑ አይደሉም ምክንያቱም የተቃራኒ ፃታ ልዩ መብት አላቸው/ ግማሽ ተቃራኒ ፃታ አፍቃሪ ናቸው::” 
እውነታ: ባይሴክሽዋል ሰዎች በተቃራኒ ፃታ አፍቃሪም ሆነ በተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪ ማህበረሰብ ውስጥ ለመታየት ወይም ለመቀላቀል ብዙ ይቸገራሉ:: አብዛኛውን ጊዜም ከባይሴክሽዋል ጣላቻ በተጨማሪ በጌ እና ሌዝቢያን ማህበረሰብ ውስጥ መድልዖ ይደርስብቸዋል:: ከጌ እና ሌዝቢያን ሰዎች የተለየ ባይሴክሽዋል ሰዎች ማንነታቸውን በተቃራኒ ፆት ማንነት ውስጥ ለመደበቅ አይሞክሩም::

አፈታሪክ: ባይ ሰዎች ለወንድም ለሴትም እኩል ተማርኮ ያሳያሉ:: 
እውነታ: አንዳንድ ባይሴክሽዋል ሰዎች ሃምሳ ሃምሳ የሆነ ተማርኮ ለተለያዩ ስርዓተ ፃታዎች ይሳያሉ:: ነገር ግን ብዙዎች ደግሞ እኩል የተከፈለ የተማርኮ ስርዓት የላቸውም:: ፍላጎት በየጊዜው ሊለያይ ይችላል፣ እንደ ወሲባዊ ተማርኮ ውስብስብ የሆነን ነገር በፐርሰንት መከፋፈል በጣም ደካማ የሆነ ምርምር ነው::

(ምንጭ:- https://www.glaad.org/blog/celebrate-bisexuality-glaad-dispels-common-myths-and-stereotypes and https://www.lgbthero.org.uk/busting-bisexuality-myths)

Leave a Reply