ኢትዮኩዊር  ፓድካስት: ሁለተኛው ምዕራፍ

ሁለተኛውን ምዕራፍ የኢትዮ ኩዊር  ፓድካስት መጀመራችንን ስንገልፅ በደስታ ነው:: በጠየቃችሁን መሰረት በየወሩ ይለቀቅ የነበረውን ቃለ መጠይቅ በየሳምንቱ ለ12 ሳምንታት ለመልቀቅ ተስማምተናል::

እዚህ የሚገኘው የመጀመሪያው ክፍል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለን የLBQ ዴቲንግ ላይ ያጠነጥናል:: የLBQ ማህበረሰብ ቁጥር እንደማነስና የተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪይን ጠልነት እንደመኖሩ ዴቲንግ ለኩዊር ሰዎች ተግዳሮት እና አደጋ አለው:: 

በዚህ ዙሪያ ከአራት LBQ ኢትዮጵያውያን ጋር ያደረግነውን ውይይት ያድምጡ፤ በቃለ መጠይቁ ላይ እንዴት LBQ ማህበረሰቦች እንደሚገናኙ ፣ የአጭር ጊዜ ግንኙነት ባህል ፣ የረዥም ጊዜ የፍቅር ግንኙነት እና ግንኙነቶች ላይ ያሉ አድሎዎችን ተወያይተናል:: 

ይህ ውይይት የግንኙነት ደስታዎችን እና እንቅፋቶቻችን ይዟል እንዲሁም የኢትዮጵያ ውስጥ ዴቲንግ ላይ ጠቃሚ ምክሮችን ያካፍላል:: 

እንደምትወዱት አንጠራጠርም፤ እንደሁልጊዜው አስተያየቶቻችሁን እንጠብቃለን::

Leave a Reply