የ”አሴክሽዋሊቲ” ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት: “‘አሴክሽዋል’ መሆን ትክክለኛ ማንነት ነው፤ መደገፍ እንጂ ማቃለል የለብንም”

ኢትዮጵያ ውስጥ “አሴክሽዋሊቲ” ብዙም የማይነሳ ርዕስ ነው:: ሲነሳ ደግሞ ቦታ ባለመስጠት እና በመፍረድ ስሜት ነው። በየአመቱ ጥቅምት 10 እስከ 16 ተከብሮ የሚውለው የአሴክሽዋሊቲ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት ራሳችንን ለማስተማር እና በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉትን የአሴክሽዋል ሰዎች ድጋፍ ለማሳየት ጥሩ አጋጣሚን ይፈጥራል። 

“አሴክሽዋል” ማለት ሰፊ የወሲባዊነት ማንነቶችን ጠቅልሎ የያዘ ስያሜ ነው:: የሰዎች ከትንሽ የወሲባዊ  ተማርኮ እስከ ለሌሎች ምንም አይነት የወሲባዊ ስሜት አለመኖር  እውነታ ነው። ይህ ማለት “አሴክሽዋል” ሰዎች የወሲብ ህይወት የላቸውም ወይም የወሲብ ተነሳሽነት የላቸውም ማለት አይደለም:: ይህ ማለት በአንድ ሰው ላይ ያላቸው የፍላጎት ደረጃ ምንም ይሁን ምን”አሴክሽዋ” የሆነ ሰው ለእነሱ ወሲባዊ ፍላጎት አይሰማውም ማለት ነው። በዚህ ማንነት ራሳቸውን የሚገልፁ ሰዎች “አሴክሽዋል” ለመሆን ከወሲብ መራቅ አለባቸው ማለት እንዳልሆነ ልናስተውል  ይገባል። 

የ“አሴክሽዋሊቲ” ሬንጅ ከዚህ በታች ያሉትን ያካትታል: 

“አሴክሽዋል”
አንዳንድ “አሴክሽዋል” ሰዎች ወሲባዊ ፍላጎት ይኖራቸዋል፥ አንዳንዶች ደግሞ ምንም አይነት የወሲብ ፍላጎት አይኖራቸውም።

“ግሬይሴክሽዋል” 
አንዳንድ ጊዜ “grey aces” ወይም “gray a” ተብሎ ይጠራል:: “ግሬይሴክሽዋል” በቀዳሚነት “አሴክሽዋል” ናችው ነገር ግን በጣም ልዩ በሆነ ሁኔታዎች ወሲባዊ ባህሪይ ሊያስደስታቸው ይችላል:: ወይም አልፎ አልፎ የወሲብ ፍላጎት ሊኖራቸው ይችላል። 

“ደሚሴክሽዋል”
“ደሚሴክሽዋል” የሆኑ ሰዎች የወሲብ ተማርኮ የሚኖራቸው ከዛ ሰው ጋር በጣም ጠንካራ ስሜታዊ ግንኙነት ከፈጠሩ በሗላ ነው:: ምንም እንኳን የ “ደሚሴክሽዋል” ማንነት በ “አሴክሽዋል” ጥላ ውስጥ ቢሆንም ከ “አሴክሽዋል” እና “ግሬይሴክሽዋል” በበለጠ የወሲብ ህይወት ይኖራቸዋል። 

“አሴክሽዋል” መሆን ትክክለኛ ማንነት ነው፤ መደገፍ እንጂ ማቃለል የለብንም:: ራሳችንን በዚህ ዙሪያ በማስተማር ለኢትዮጵያ LBQ ሰፊ የወሲብ ማንነቶች  የተሻልን ደጋፊዎች መሆን አለብን።

Leave a Reply