ኢትዮ ኩዊር ፓድካስት: እምነትና ወሲባዊነትን ማስታረቅ

አብዛኛውን ጊዜ እንደ LBQ ኢትዮጵያውያን ቤተ እምነቶች እና የእምነት ሰዎች እምነትን ለወቀሳ እና ጥላቻ ሲጠቀሙብን ተገለን ወይም ውጪ ሆነን እንመለከታለን። በተከታታይ ተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪነት ከምዕራብ የመጣ እንዲሁም የሃይማኖት መሪዎች እንደየእምነቱ ቢለያይም ጊዜ ወስደው ተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪነት የሚያስከትለውን “ክፉ ነገር” ይሰብካሉ። 

እናም ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ኩዊር ማህበረሰብ ራስን የመቀበል ችግር እምነት እና ወሲባዊነትን ለማስታረቅ ያለው ትግል መሆኑ አይገርምም። 

ይህንን ትልቅ ትግል ድምፅ ለመስጠት ኢትዮኩዊር ፖድካስት ከተለይዩ ሃይማኖት የተወጣጡ LBQ ሰዎች ጋር ውይይት አድጓል:: የየግል ጥንካሬን የሚያሳይ  ድንቅ ውይይት ብቻ ሳይሆን በግላችን ለመርመር ዝግጁ ከሆንን ምን ያህል ነገሮችን ማድረግ እንደሚቻል ያስተዋለ ነበር። ሁለት ጉዞዎች ተመሳሳይ እንዳልሆኑ ግን በፅናት፣ የማያቋርጥ ግምገማ እና ድጋፍ ፍለጋን ለመቀጠል የሚያስችል ጥንካሬ እንዳለን የሚያስታውስም ጭምር ነው። 

እንደኢትዮጵያውያን እምነት እና ወሲባዊነታችንን አስታርቀን ራሳችንን ልንቀበል እንችላለን? መልሶቻቸው ያስደንቋችሗል፤ ውይይቱም በሳቅ የታጀበና እና ተስፋ የሚሰጥ ነው።

Leave a Reply