ኢትዮ ኩዊር ፓድካስት: ከLBQ ማህበረሰብ የሚመጣ የ”ሴታሴት” (femme) ኩዊር ሴቶች ድምሰሳ እና መዘዞቹ

“የእኛ ማንነት ሌሎችን መንጠቅ የለበትም:: ለሁላችንም በቂ ቦታ አለ::” ሌክሲ አዲሱ የፖድካስት ውይይታችንን ታብራራለች:: ከLBQ ማህበረሰብ የሚመጣ የ”ሴታሴት” (femme) ኩዊር ሴቶች ድምሰሳ ላይ ያተኩራል:: 

የ”ሴታሴት” (femme) ኩዊር ሴቶች ድምሰሳ ማለት LBQ የሆኑ ሴቶች ኩዊር ለመባል ግዴታ ራሳቸውን በ”ወንዳወንድ” ማንነት ወይም አቀራረብ መምጣት አለባቸው የሚል አስተያየት ነው:: “Femme” የምንለው በተለምዶ የ”ሴታሴት” ገፀ ባህርይ ያለው ሰው ማለት ነው:: 

ይህ ውይይት ከ “ሴታሴት” ሴቶች ህይወት ልምድ እና የእለት ተእለት ኑሮ በመነሳት የ”ሴታሴት” (femme) ኩዊር ሴቶች ድምሰሳን እንድንረዳ እና ያሏቸውን ተደራራቢ ተግዳሮቶች ያሳየናል:: 

“ሴታሴት” ሴቶች ብዙ ተግዳሮቶች አሏቸው:: ምንም እንኳን በአቀራረባቸው ምክንያት ተለይተው ኢላማ የመደረግ አደጋ ባይገጥማቸውም “ሴታሴት” በመሆናቸው የሚመጡባቸው ብዙ ችግሮች አሉ:: ከነዚህም መካከል ኩዊር ነን ሲሉ አለመታመን፣ በLBQ ማህበረሰብ በቀላሉ እንደኩዊር አለመታየት፣ “ማንነቴን ለሌሎች ማሳመን አለብኝ” የሚል ስሜት፣ በLBQ ማህበረሰብ ተቀባይነት አለማግኘት እና እንደ “ኩዊር አትመስሉም” የሚልን አላስፈላጊ አስትያየት መስማት ናቸው:: 

ይህ ድምሰሳ የብቸኝነት ስሜት እና በተቃራኒ ፃታ አፍቃርያን ላይ ያለን የስርዓተ ፃታ ክፍፍል ወደመቀበል ይገፋፋል:: እንግዶቻችን ከፍቅር እስከወሲብ፣ እኛ እንደማህበረሰብ እንዴት ይህንን ችግር መፍታት እናዳለብን እና ለሁላችንም ቦታ ማዘጋጀት እንዳለብን በጥልቅ ያወያዩናል::

ተጋበዙልን 

ምንጭ: https://www.verywellmind.com/what-is-femme-invisibility-5187233

Leave a Reply